ምግብ ቤቶችን በGoogle ላይ ይፈልጉ

Google ፍለጋን በመጠቀም ሆቴሎችን ማወዳደር እና ቦታ ማስያዝ ይችላሉ።

 • ሆቴሎችን በዋጋ፣ በአካባቢ፣ በደረጃ እና በሆቴል ምድብ ማጣራት ይችላሉ።
 • ፎቶዎችን እና ግምገማዎችን ጨምሮ የሆቴል ዝርዝሮችን ይመልከቱ።
 • ከእኛ የቦታ ማስያዝ አጋሮች በአንዱ ክፍል ያስይዙ።

ሆቴል ይፈልጉ

 1. ወደ google.com ይሂዱ።
 2. በፍለጋ አሞሌ ውስጥ፣ መቆየት በሚፈልጉበት ከተማ ወይም አካባቢ ውስጥ ያሉ ሆቴሎችን ያስገቡ። ለምሳሌ፣ ፓሪስ ውስጥ ያሉ ሆቴሎች
 3. በፍለጋ ውጤቶች ውስጥ፣ ወደ የሆቴል ውጤቶች ሳጥን ይሂዱ።
 4. የሁሉንም ሆቴሎች ውጤት ለማየት፣ወይ፦
  • የእርስዎን ቀን ያስገቡ።
  • ከሳጥኑ በታች በኩል፣ አገናኙን መታ ወይም ጠቅ ያድርጉ።

ዴስክቶ፦ ሆቴሎችን ይፈልጉ

ሞባይል፦ ሆቴሎችን ይፈልጉ

የሆቴል ፍለጋዎን ያጥብቡ

ሆቴል ከፈለጉ በኋላ፣ ከላይ አካባቢ፦

 • የእርስዎን ቀናት ያስተካክሉ።
 • ፍለጋዎን ለማጥበብ ማጣሪያዎችን ይጠቀሙ። በዋጋ፣ በመያዝ አቅም፣ በተጠቃሚ ምዘና፣ በሆቴል ምድብ እና በምቾት አገልግሎቶች ማጣራት ይችላሉ።
 • አካባቢውን እና ሌሎች በአካባቢው ያሉ ሆቴሎችን ለማየት ካርታውን ይጠቀሙ።

ለሆቴል ቦታ ያስይዙ

 1. ሆቴል ይምረጡ።
 2. ክፍል ያስይዙ መታ ወይም ጠቅ ያድርጉ።
 3. የእርስዎን ቀናት እና ሌሎች መረጃዎች ያረጋግጡ። ከዚያ የቦታ ማስያዝ አማራጮችን ይምረጡ።
 4. ግብይቱን በሆቴሉ ወይም የጉዞ ወኪሉ ድር ጣቢያ ላይ ያጠናቅቁ። 

ማስታወሻ፦ አንዳንድ ሆቴሎች እና የጉዞ ወኪሎች ቦታ ማስያዝዎን በቀጥታ በGoogle ላይ እንዲያጠናቅቁ ይፈቅዳሉ። በእነዚህ ጊዜያት፣ በGoogle ላይ እንዴት ቦታ እንደሚያዝ ይረዱ

የሆቴል ዋጋዎች

የሆቴል ዋጋዎች ከGoogle አጋሮች የመጡ ናቸው። የሆቴል ዋጋዎች መተግበሪያ ፕሮግራም የማድረግ በይነገጽ (ኤፒአይ) የሚባል አገልግሎት ይጠቀማሉ። አጋሮች እንዴት ዋጋ ወደ Google እንደሚልኩ የበለጠ ይረዱ

አንዳንድ ጊዜ፣ አጋሮቻችን ለሁሉም ሰው የማይገኝ የተለየ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀርባሉ። ለምሳሌ፣ አንድ ዋጋ ወደ የGoogle መለያቸው ለገቡ ወይም በተንቀሳቃሽ መሳሪያቸው ለሚጠቀሙ ሰዎች ብቻ ሊገኝ ይችላል። የተዘረዘሩት ዋጋዎች ለሁሉም ሰው የቀረቡ አለመሆናቸውን ለማወቅ፣ መረጃመረጃ ይምረጡ።

ማስታወሻ፦ ዋጋዎች ሊቀየሩ ይችላሉ። (ተጠያቂነትን ማንሳት)

የሚታየውን የሆቴል ዋጋዎች ምንዛሬ ይቀይሩ፦ ለሆቴል ዋጋዎች የሚያዩት ምንዛሬ በGoogle የፍለጋ ቅንብሮችዎ ይወሰናል። ዋጋዎችን በተለያዩ ምንዛሬዎች ለማየት፣ የክልል ቅንብሮችዎን መቀየር ያስፈልግዎታል

የሆቴል ቅናሾች

ለሆቴል ፍለጋዎ እገዛ ለማድረግ፣ ከሆቴል ስም ጎን «ቅናሽ» የሚል ባጅ በማከል ትልልቅ ቅናሾችን አድምቀን እናሳያለን። ሁለት አይነት ቅናሾች አሉ፦

 • ከተለመደ ተመናቸው በታች ወይም በአቅራቢያ ካሉ ተመሳሳይ ሆቴሎች በታች ዋጋ ያላቸው ሆቴሎች። ከተለመደው ተመን ጋር ሲነጻጸር ያለውን የዋጋ ልዩነት ማየት ይችላሉ።
 • አንድ አጋር ሆቴሉ ካለው ወቅታዊ የገበያ ዋጋ ላይ ቅናሽ የሚያቀርብባቸው ሆቴሎች የትርፉ መጠን ይታያል።
የሆቴል ምድቦች

የመቆያ አማራጮችን በተሻለ እንዲያወዳድሩ ለማገዝ፣ Google ለሆቴሎች የምድብ ምዘናዎችን ይሰጣል። እያንዳንዱ ሆቴል በ1 እና 5 ኮከቦች መካከል ምዘና ያገኛል። ፍለጋዎን ለማጥበብ እነዚህን ምዘናዎች መጠቀም ይችላሉ።

የሦስተኛ ወገን አጋሮችን፣ ቀጥታ ፍለጋን፣የሆቴል ባለቤቶች ግብረመልስን፣ እንዲሁም እንደ ዋጋ፣ አካባቢ፣ የክፍል መጠን፣ የምቾት አገልግሎቶች የመሳሰሉ የሆቴል መገለጫዎችን የሚገመግሙ እና የሚተነትኑ የmachine learning ጥቆማዎችን ጨምሮ Google ለእነዚህ ምዘናዎች ውሂብ ከተለያዩ ምንጮች ይሰበስባል። ባለ 2-ኮኮብ ሆቴል መካከለኛ ክፍሎች እና ተመጣጣኝ ዋጋዎች ሊኖራቸው ይችላል፣ ባለ 4-ኮኮብ ሆቴል ደግሞ ውድ ጌጣጌጦች፣ ለክፍሉ የተመደበ ሰራተኛ፣ የ24 ሰዓት የክፍል ውስጥ አገልግሎት፣ እንደ የመታጠቢያ ክፍል ልብስ እና አነስተኛ መጠጦችን የመሳሰሉ የቅንጦት አገልግሎቶች ሊያካትት ይችላል። የምድብ ምዘናዎች በአንድ የሆቴል ፍለጋ ውጤት ላይ ተቀራራቢ መሆን አለባቸው።

የምድብ ምዘና የማያሳዩ ሆቴሎች እስካሁን በGoogle አልተገመገሙም። በሆቴል ምደባዎች ላይ ግብረመልስ ለመስጠት፣ እኛን ያነጋግሩን

የሆቴል ምቾት ሰጪ መገልገያዎች

በሆቴል ፍለጋዎ ላይ እገዛ ለማድረግ፣ Google በእያንዳንዱ ሆቴል የሚቀርቡ እንደ Wi-Fi ወይም የመዋኛ ገንዳ የመሳሰሉ ተጨማሪ የምቾት አገልግሎቶችን ያሳያል። ይህ መረጃ የመቆያ አማራጮችን ለማወዳደር እና ፍለጋዎን ለማጥበብ ሊያግዝዎት ይችላል።

የሆቴል ባለቤቶችን እና ድር ጣቢያቸውን፣ የሦስተኛ ወገን አጋሮችን፣ የቀጥታ ጥናት እና የተጠቃሚ ግብረ መልስን ጨምሮ፣ Google ከተለያዩ ምንጮች የሆቴል ተጨማሪ የምቾት አገልግሎት መረጃ ይሰበስባል።

ትክክል ያልሆነ የተጨማሪ ምቾት መረጃ አስተውለው ከሆን፣ ⁠ያሳውቁን

የሆቴል ማስታወቂያዎች

የጉዞ ቀናትዎን ካስገቡበት በታች፣ ከፍለጋዎ ጋር ተያያዥ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ከእኛ የሆቴል አጋሮች ይመለከታሉ። እነዚህ ማስታወቂያዎች የአሁኑን የእርስዎ የፍለጋ ቃላት መነሻ ያደርጋሉ፣ እንዲሁም በGoogle መለያ መግባትዎን መነሻ ሊያደርጉም ይችላሉ።

ዋጋዎቹ ለመረጧቸው ቀናት ከአጋሮቻችን ይፋ የሆኑ ተመኖች ናቸው። ይፋዊ ያልሆኑ ዝቅተኛ ዋጋዎችን ለመመልከትም መስፈርቱን ሊያሟሉ ይችላሉ። ስለ ማስታወቂያዎች የበለጠ ይረዱ

የሆቴል ቆይታዎች

ለሆቴል ፍለጋዎ እገዛ ለማድረግ፣ ከዚህ በፊት የቆዩባቸውን ወይም ለቀጣይ ቆይታ ቦታ ያስያዙባቸውን ሆቴሎች አድምቀን እናሳያለን። በፍለጋ ውጤቶችዎ ውስጥ ከሆቴሉ ስም ስር፣ «በቅርብ እዚህ ቆይተዋል» የሚሉ አይነት ቃሎች ይመለከታሉ።

እነዚህን ሆቴሎች የመረጥናቸው በእርስዎ የGmail መለያ ያሉ የሆቴል ቦታ ማስያዝን የሚመለከቱ ኢሜይሎችን መነሻ በማድረግ ነው።

ማስታወሻ፦ ይህን ባጅ ለማየት፣ በGoogle መለያዎ መግባት ይኖርብዎታል።

እንደነዚህ አይነት ጥቆማዎችን ማየት ካልፈለጉ፣ የግል የፍለጋ ውጤቶችን ማጥፋት ይችላሉ። የእርስዎን የፍለጋ ቅንብሮች ይቀይሩ

ማስቀረቶች እና ተመላሽ ገንዘቦች

ለማናቸውም የጉዞ ለውጦች፣ ማስቀረቶች፣ ወይም ተመላሽ ገንዘቦች የቦታ ማስያዝ አጋርን (ሆቴሉን ወይም የጉዞ ወኪሉን) ያነጋግሩ።

የቦታ ማስያዝ አጋሩን የእውቂያ መረጃ በቦታ ማስያዝ ማረጋገጫ ገጽ ላይ ወይም ከአጋር በተላከው የማረጋገጫ ኢሜይል ውስጥ ማግኝት ይችላሉ። ሆቴል በGoogle በቀጥታ ቦታ አስይዘው ከነበረ፣ የአጋር የእውቂያ መረጃ ከGoogle በተላከው የማረጋገጫ ኢሜይል ውስጥ ማግኘት ይችላሉ።

ስለ የእኔ ፍለጋዎች Google የሚያስቀምጠው መረጃ

ፍለጋዎችዎን ለማየት እና ለማስወግድ፣ ወደ እኔ እንቅስቃሴ ይሂዱ

በመለያዎ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ እንዴት እንደሚያዩ እና እንደሚቆጣጠሩ ይረዱ።

ፍለጋ
ፍለጋን አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
254
false