YouTube በጎ አድራጎት ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

YouTube በጎ አድራጎት ፈጣሪዎች የሚፈልጓቸውን የበጎ አድራጎት ዓላማዎች እንዲደግፉ ያስችላል። ብቁ የሆኑ ሰርጦች በቪዲዮዎቻቸው ወይም በቀጥታ ዥረቶቻቸው ላይ ይለግሱ አዝራር በማከል ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ገንዘብ ማሰባሰብ ይችላሉ። ተጠቃሚዎች በቪዲዮ መመልከቻ ገጹ ወይም በቀጥታ ውይይት ላይ በቀጥታ መለገስ ይችላሉ።

የፈጣሪ እና የገንዘብ አሰባሳቢ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

ለYouTube በጎ አድራጎት ገንዘብ ለማሰባሰብ ብቁ የሆነው ማነው?

የበጎ አድራጎት ገቢ ማሰባሰቢያ ለማዋቀር ሰርጥዎ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት፦

ማስታወሻ: ከላይ ከተጠቀሱት የብቁነት መስፈርቶች ውጭ የገንዘብ ማሰባሰብ ሊመለከቱ ይችላሉ። ለወደፊቱ YouTube በጎ አድራጎት የበለጠ በሰፊው የሚገኝ እንዲሆን እናቅዳለን።

የትኞቹ አገሮች/ክልሎች የYouTube በጎ አድራጎት ገቢ ማሰባሰቢያ ማዋቀር ይችላሉ?

በሚከተሉት አገሮች/ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ከሆኑ፣ YouTube በጎ አድራጎት የገቢ ማሰባሰቢያን ማዋቀር ይችላሉ።

  • አርጀንቲና
  • ኦስትሪያ
  • ቤልጂየም
  • ቦሊቪያ
  • ካናዳ
  • ኮሎምቢያ
  • ከሮሽያ
  • ኤስቶንያ
  • ፈረንሳይ
  • ጀርመን
  • ጋና
  • ሆንግ ኮንግ
  • አይስላንድ
  • ኢንዶኔዢያ
  • አየርላንድ
  • እስራኤል
  • ጣሊያን
  • ኩዌት
  • ላትቪያ
  • ሊቱዌንያ
  • ሉክዘምበርግ
  • ማሌዢያ
  • ሜክሲኮ
  • ሞንቴኔግሮ
  • ኔዘርላንድ
  • ኒው ዚላንድ
  • ኖርዌይ
  • ፔሩ
  • ፊሊፒንስ
  • ፖላንድ
  • ፖርቶ ሪኮ
  • ሮማኒያ
  • ስሎቫኪያ
  • ስፔን
  • ስዊድን
  • ስዊዘርላንድ
  • ታይላንድ
  • ቱርክ
  • ዩናይትድ ኪንግደም
  • ዩኤስኤ

ለYouTube በጎ አድራጎት መዳረሻ እንዳለኝ አያለሁ እንዴት ማዋቀር እችላለሁ?

ገቢ ማሰባሰቢያ ከፈጠርኩ በኋላ ይለግሱ አዝራርን ባላይስ?

በገቢ ማሰባሰቢያዎ ላይ ይለግሱ አዝራር ላይታይ የሚችልባቸው የተወሰኑ ምክንያቶች ከታች ተቀምጠዋል፦
  • የYouTube በጎ አድራጎት ገቢ ማሰባሰቢያ ማዋቀርዎን ያረጋግጡ።
  • ገቢ ማሰባሰቢያው ማስጀመሪያ ቀን ካለው፣ የልገሳ አዝራሩ በእርስዎ መመልከቻ ገጽ ወይም በቀጥታ ውይይቱ ላይ ገቢ ማሰባሰቢው ከሚጀምርበት ቀን በኋላ የሚታይ ይሆናል።
  • በቀጥታ ዥረት ላይ ገቢ በማሰባሰብ ላይ ከሆኑና የቀጥታ ውይይት በርቶ ከሆነ፣ ይለግሱ አዝራርን በሞባይል ላይ በውይይት ውስጥ ያዩታል። የቀጥታ ውይይቱን ለመመልከት ሞባይል መሳሪያዎች በቁመት ሁነታ ላይ መሆን አለባቸው። ስለ የቀጥታ ውይይት ልገሳዎች የበለጠ ይወቁ።
  • ቪዲዮዎን ወይም ሰርጥዎን "ለልጆች የተዘጋጀ" ካደረጉት፣ ይለግሱ አዝራር ይወገዳል። 

የማኅበረሰብ ገቢ ማሰባሰቢያዎች ምንድን ናችው?

የማኅበረሰብ ገቢ ማሰባሰቢያዎች ከሌሎች ፈጣሪዎች ጋር በትብብር ለተመሳሳይ ዓላማ ገቢ ለማሰባሰብ ያስችሉዎታል። የማኅበረሰብ ገቢ ማሰባሰቢያን እንዴት መቀላቀል እንደሚችሉ ይወቁ።

ልዕለ ውይይት ለበጎ አድራጎት ምን ገጠመው?

ልዕለ ውይይት ለበጎ አድራጎት አሁን የቀጥታ ውይይት ልገሳዎች ሆኗል። ፈጣሪዎች አሁንም ቢሆን በቀጥታ ዥረቶቻቸው ውስጥ የገቢ ማሰባሰቢያ ማዘጋጀት ይችላሉ፣ እንዲሁም ተመልካቾች በቀጥታ ከውይይቱ መስኮት መለገስ ይችላሉ። ግራ ማጋባትን ለመቀነስ ልገሳዎች ላሏቸው የቀጥታ ዥረቶች ልዕለ ውይይት እና ልዕለ ተለጣፊዎች ይወገዳሉ። የተመልካች ልገሳዎችን በቀጥታ ቁጥጥር ክፍል ውስጥ በተመልካች እንቅስቃሴ ምግብር አማካኝነት መከታተል ይችላሉ።
የቀጥታ ውይይት ልገሳዎችን ለማብራት፣ የእርስዎን የጊዜ ሰሌዳ የተሰጠው የቀጥታ ስርጭት ወደ ገቢ ማሰባሰቢያዎ ያክሉ። የYouTube በጎ አድራጎት ገቢ ማሰባሰቢያ እንዴት ማዋቀር እንደሚችሉ የበለጠ ለመረዳት የቀጥታ ውይይት ያላቸው የቀጥታ ውይይቶች በውይይቱ ውስጥ ይለግሱ አዶ ይኖራቸዋል «»። የቀጥታ ውይይት የሌላቸው የቀጥታ ዥረቶች ከዥረቱ አጠገብ ወይም ከታች ይለግሱ አዝራር ይኖራቸዋል።
ከፍተኛ ምስጋና ልገሳዎች ባሉባቸው ቪዲዮዎች ላይ አይገኝም።

ገቢ ማሰባሰቢያ ያላቸውን ቪዲዮዎች እና የቀጥታ ዥረቶች አሁንም ቢሆን ገቢ መፍጠሪያ ማድረግ እችላለሁ?

በቪዲዮዎችዎ እና የቀጥታ ዥረቶችዎ ላይ የገቢ ማሰባሰቢያ በሚያክሉ ጊዜ ማስታወቂያዎች ላይ ተጽዕኖ አይኖርም። ግራ መጋባትን ለማስቀረት፣ ልዕለ ውይይት እና ልዕለ ተለጣፊዎች የቀጥታ ውይይት ልገሳዎች ባሏቸው የቀጥታ ዥረቶች ላይ አይገኙም። ፈጣሪዎች ይለግሱ አዝራር ያለው ለአባላት-ብቻ የሆነ የቀጥታ ውይይት ማስተናገድ አይችሉም። ከፍተኛ ምስጋና ልገሳዎች ባሉባቸው ቪዲዮዎች ላይ አይገኝም።

ለትርፍ ያልተቋቋሙት ድርጅቶች ልገሳዎቹን እንዴት ያገኛሉ?

Google ከNetwork for Good ጋር በGoogle ጥያቄ መሰረት ልገሳዎችን እንዲያሰባስብ እና እንዲያሰራጭ በትብብር ይሰራል። የልገሳዎ 100% ወደ ለትርፍ ያልተቋቋመው ድርጅት ይሄዳል፣ እንዲሁም የግብይት ክፍያዎችን YouTube ይሸፍናል። የዩ.ኤስ. አይአርኤስ በሚያስገድደው መሰረት፣ Network for Good ልገሳዎቹ አንድ ጊዜ ከተሰበሰቡ በኋላ በብቸኝነት የመቆጣጠር ሕጋዊ ሥልጣ አለው። Network for Good የተለገሰውን ገንዘብ ለYouTube ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ማስረከብ ካልቻለ፣ Network for Good will ገንዘቡን ለሌላ መስፈርቶቹን ለሚያሟላ የዩኤስ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ያስረክባል። Network for Good ስርጭት እንዴት እንደሚከናወን የበለጠ ለመረዳት

የእኔን ልገሳ ለመቀበል የታሰበው ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ብቁ ሳይሆን ቢቀርስ?

በለጋሽ የተመከረ የፈንድ አጋር የሆነው Network for Good፣ የአንድን ፕሮጀክት ፈንድ በማንኛውም ምክንያት (ለትርፍ ያልተቋቋመው ድርጅት መስፈርቱን የሚያሟላ የዩናይትድ ስቴትስ 501(c)(3) ድርጅት አለመሆኑን ጨምሮ) ለታሰበው ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ማድረስ ካልቻለ፣ Google መስፈርቱን የሚያሟላ ተለዋጭ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ለመምረጥ ከNetwork for Good ጋር ይሰራል።
በእኔ የቀጥታ ውይይቶች ውስጥ ልገሳዎችን እንዴት አያለሁ?
ልገሳዎችን በውይይት መስኮት ውስጥ ያዩአቸዋል። በተጨማሪም ልገሳዎችን በእውነተኛ ጊዜ ውስጥ በእቀጥታ መቆጣጠሪያ ክፍል ውስጥ በተመልካች እንቅስቃሴ ምግብር አማካኝነት ማየት ይችላሉ።

ጠቅላላ መጠን እና የግስጋሴ አሞሌ ምንን ይወክላሉ?

ጠቅላላ መጠን ለዚያ ገቢ ማሰባሰቢያ ፣ ከሁሉም ሰርጦች፣ ከቪዲዮዎች እና በገቢ ማሰባሰቢያው ውስጥ ከተሳተፉ ቪዲዮዎች የተሰበሰበውን ፈንድ መጠን በጠቅላላ ይወክላል። ጠቅላላ መጠንን ወይም የግስጋሴ አሞሌን ከይለግሱ አዝራር በታች ማግኘት ይችላሉ።

ስለ ገቢ ማሰባሰቢያዬ ትንታኔ የት ማግኘት እችላለሁ?

ስለ ገቢ ማሰባሰቢያዎ ትንታኔ ለማግኘት፦

  1. ወደ YouTube መለያ በኮምፒውተር ላይ ይግቡ
  2. ወደ YouTube ስቱዲዮ ይሂዱ።
  3. ወደ ገቢ መፍጠር ይሂዱ።
  4. በጎ አድራጎትን ይምረጡ።
  5. ከ«ጠቅላላ የተሰበሰበ» ስር መሰረታዊ የገቢ ማሰባሰቢያ ውሂብ እርስዎ ከተቀላቀሏቸው ወይም ከፈጠሯቸው ዘመቻዎች አጠገብ ያገኛሉ።
  6. ስለ ገቢ ማሰባሰቢያዎ የበለጠ ዝርዝር ለማግኘት፣ የተሰበሰበው መጠን ላይ በአይጢትዎ ያንዣብቡ።

ለትርፍ ስላልተቋቋሙ ድርጅቶች ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

በYouTube በጎ አድራጎት ገቢ እንዲሰባሰብላቸው ብቁ የሆኑ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች የትኞቹ ናቸው?
ከYouTube በጎ አድርራጎት ገቢ ለማሰባሰብ ብቁ ለመሆን አንድ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የሚከተሉትን ማሟላት አለበት፦
  • በፈጣሪ የተጠየቀ መሆን።
  • በዩኤስ ውስጥ የተመዘገበ 501(c)(3) የሕዝብ በጎ አድራጎት ድርጅት የሆነ።
    • ማስታወሻ፦ ለአሁን በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ያሉ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ብቻ ብቁ የሆኑ ቢሆንም፣ በርካታ የትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች በዩኤስ ውስጥ ቅርንጫፎች ወይም እህት ድርጅቶች አሏቸው። አሁን ያሉ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ሙሉ ዝርዝር መመልከት ይችላሉ።YouTube በጎ አድራጎት ማቀናበሪያ መሳሪያ
  • በ GuideStar በኩል አማካኝነት ወደ በመስመር ላይ ገቢ ማሰባሰብ በምርጫዎ ይግቡ
  • የYouTubeን የገቢ መፍጠሪያ መመሪያዎች በYouTube ላይ እና ከዚያ ውጭ ይከተሉ። ይህ መስፈርት የYouTube የማኅበረሰብ መምሪያዎችን ያካትታል።
ማስታወሻ፦ ፋውንዴሽኖች ለጊዜው አይደገፉም። 

በመጠየቂያ መሳሪያው ውስጥ የምፈልገውን ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ካላየሁትስ?

ከታች እርስዎ የሚፈልጉት ለትርፍት ያልተቋቋመ ድርጅት በመጠየቂያ መሳሪያው ውስጥ ላይታይ የሚችልባቸው አንዳንድ ምክንያቶች ተጠቅሰዋል።
  • ለትርፍ ያልተቋቋመው ድርጅት የGoogle ለበጎ አድራጎት አካል አይደለም። ለትርፍ ያልተቋቋመው ድርጅት የGoogle ለበጎ አድራጎት መለያ መጠየቅ ይችላል
  • ለትርፍ ያልተቋቋመው ድርጅት በGuidestar የተመዘገበ መቀመጫው በዩኤስ ውስጥ የሆነ 501(c)(3) ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት አይደለም። ለትርፍ ያልተቋቋመው ድርጅት እዚያ መኖሩን ለማረጋገጥ በguidestar.org ላይ ይፈልጓቸው።
  • ለትርፍ ያልተቋቋመው ድርጅት በመስመር ላይ ገቢ ከማሰባሰብ በፈቃዱ እራሱን አግልሏል። ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ለጋሾች ለእነርሱ በመስመር ላይ ገቢ እንዲያሰባስቡ ፈቃደኝነታቸውን መግለጽ አለባቸው። በYouTube ላይ ለትርፍ ላልተቋቋመ ድርጅት ገንዘብ ስለማሰባሰብ የበለጠ ለመረዳት።

መደገፍ የምፈልገውን ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ጠይቄያለሁ። ለማከል ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል?

የእርስዎን መስፈርቱን የሚያሟላ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ካስገቡ በኋላ፣ የጥያቄዎን ሁኔታ ለእርስዎ ለማሳወቅ ኢሜይል ልንልክልዎታለን። አንዳንድ ጥያቄዎች እስከ 5 የሥራ ቀናት ይወስዳሉ። ሂደቱን ለማፋጠን እንዲረዳ፣ እርስዎ የሚጠይቁት ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት የብቁነት መስፈርቶችን የሚያሟላ መሆኑን ያረጋግጡ።

ገንዘቡ ለትርፍ ላልተቋቋሙ ድርጅቶች የሚሰራጨው እንዴት ነው?

ገንዘቡን ለመሰብሰብ እና ለትርፍ ላልተቋቋሙ ድርጅቶች ለማስተላለፍ Network for Good ከተሰኘ የዩኤስ 501(c)(3) እና በለጋሽ ከሚመከር ፈንድ ጋር በጋራ እንሰራለን። በተለምዶ Network for Good ገንዘቡን በወርሃዊ መርሐግብር ያሰራጫል። የተሰበሰበው ገንዘብ ከ$10 በታች ከሆነ፣ ገንዘቡ የሚሰራጭው በዓመታዊ መርሐግብር ይሆናል። ስለ የገንዘብ ስርጭት እና Network for Good የበለጠ ይወቁ።

ስለ Google ለበጎ አድራጎት እንዴት የበለጠ ማወቅ እችላለሁ?

ስለ Google ለበጎ አድራጎት እና ስለ ፕሮግራሙ የብቁነት መምሪያዎች የበለጠ ይወቁ። 

በYouTube ላይ ለትርፍ እንዳልተቋቋመ ድርጅት ገቢ ስለማሰባሰብ እንዴት ማወቅ እችላለሁ? 

ስለ ለጋሽ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

በቪዲዮ መመልከቻ ገጽ ላይ ይለግሱ የሚል አዝራር አያለሁ። እርሱ የሚሰራው እንዴት ነው?

የቀጥታ ውይይት ልገሳዎች ምንድን ናቸው?

አንድ ፈጣሪ የቀጥታ ውይይት ወደነቃበት የቀጥታ ዥረት ወይም ቀዳሚ የገቢ ማሰባሰቢያ በሚያክሉ ጊዜ፣ ተመልካቾች ይለግሱ አዝራርን በውይይት ውስጥ ያያሉ። አንድ ተመልካች በቀጥታ ውይይት ልገሳዎች አማካኝነት በሚለግስ ጊዜ፣ ስማቸውን እና ልገሳቸውን በቀጥታ ውይይቱ ውስጥ ለማከል መምረጥ ይችላሉ። ስለ የቀጥታ ውይይት ልገሳዎች የበለጠ ይወቁ።
የትኞቹ አገሮች/ክልሎች ለYouTube በጎ አድራጎት የገቢ ማሰባሰቢያ መለገስ ይችላሉ?

በሚከተሉት አገሮች/ክልሎች ውስጥ የሚገኙ ከሆኑ መለገስ ይችላሉ።

  • አርጀንቲና
  • ኦስትሪያ
  • ቤልጂየም
  • ቦሊቪያ
  • ካናዳ
  • ኮሎምቢያ
  • ከሮሽያ
  • ኤስቶንያ
  • ፈረንሳይ
  • ጀርመን
  • ጋና
  • ሆንግ ኮንግ
  • አይስላንድ
  • ኢንዶኔዢያ
  • አየርላንድ
  • እስራኤል
  • ጣሊያን
  • ኮሪያ
  • ኩዌት
  • ላትቪያ
  • ሊቱዌንያ
  • ሉክዘምበርግ
  • ማሌዢያ
  • ሜክሲኮ
  • ሞንቴኔግሮ
  • ኔዘርላንድ
  • ኒው ዚላንድ
  • ኖርዌይ
  • ፔሩ
  • ፊሊፒንስ
  • ፖላንድ
  • ፖርቶ ሪኮ
  • ሮማኒያ
  • ስሎቫኪያ
  • ደቡብ ኮሪያ
  • ስፔን
  • ስዊድን
  • ስዊዘርላንድ
  • ታይዋን
  • ታይላንድ
  • ቱርክ
  • ዩናይትድ ኪንግደም
  • ዩኤስኤ

የእኔ ልገሳ ግብር ይነሳለታል?

በአካባቢ ላይ የተመሰረተ የለጋሽ ግብር መረጃን እዚህ ይመልከቱ።

ከምለግሰው መጠን ምን ያህሉ ለትርፍ ላልተቋቋመው ድርጅት ይደርሳል?

እርስዎ የሚለግሱት መጠን 100% ለትርፍ ላልተቋቋመው ድርጅት ይደርሳል። YouTube በተጨማሪም የክሬዲት ካርድ ክፍያዎችን ይሸፍናል።

ከለገስኩ በኋላ ማስመለስ እችላለሁ?

ለትርፍ ላልተቋቋሙ ድርጅቶች በፈቃደኝነት የሚጸሙ ልገሳዎች መመለስ አይችሉም። ክፍያ ለመፈጸም ችግር ከገጠመዎ፣ የድጋፍ ቡድናችንን ማነጋገር ይችላሉ።

ልገሳ በምፈጽም ጊዜ ለትርፍ ላልተቋቋመው ድርጅት ምን መረጃ ታጋላችሁ?

ልገሳ በሚፈጽሙ ጊዜ፣ የእውቂያ መረጃዎ ለትርፍ ላልተቋቋመው ድርጅትም ሆነ ለፈጣሪው አይጋራም። በቀጥታ ውይይት ላይ በሚለግሱ ጊዜ “ይፋዊ” ልገሳ የሚፈጽሙ ከሆነ፣ የቀጥታ ዥረቱን የሚያስተናግደው ፈጣሪ የመለያ ስምዎን እና የለገሱትን መጠን ማየት ይችላል። መረጃዎ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል የበለጠ ይወቁ።
የተጠቃሚ ኩባንያ እና የጣቢያ ውጭ ልገሳዎች ምንድን ናቸው?
  • የተጠቃሚ ልገሳዎች፦ በYouTube ተጠቃሚዎች የተለገሱ ፈንዶች።
  • የኩባንያ ልገሳዎች፦ ለትርፍ በተቋቋመው ድርጅት የተረጋገጡ በYouTube ወይም በሌላ ኩባንያ የተለገሱ ፈንዶች።
  • የጣቢያ ውጭ ልገሳዎች፦ እንደዚህ ዘመቻ አንድ አካል ከYouTube ውጭ በሌላ ጣቢያ ላይ በአደራጁ የተሰበሰቡ እና ለትርፍ ባልተቋቋመው ድርጅት የተረጋገጡ ፈንዶች።
የኩባንያ በእኩል መጠን መለገስ የሚሰራው እንዴት ነው?
አንድ ኩባንያ ልገሳዎችን በእኩል መጠን ለመለገስ ቃል ከገባ፣ ለገቢ ማሰባሰቢያው ለሚለገሰው እያንዳንዱ $1፣ ኩባንያው በYouTube ይለግሱ አዝራር አማካይነት $1 ይለግሳል። ይህ በእኩል መጠን መለገስ፣ ሙሉው እኩል መጠን እስከሚሞላ ወይም ዘመቻው እስከሚያበቃ፣ ከሁለቱ የሚቀድመው ድረስ ይቀጥላል።

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
9766423128904495222
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
59
false
false