የእርስዎን የYouTube መለያ ደህንነት ይጠብቁ

ከኖቬምበር 1፣ 2021 ጀምሮ ገቢ በመፍጠር ላይ ያሉ ፈጣሪዎች YouTube ስቱዲዮን ወይም የYouTube ስቱዲዮ ይዘት አስተዳዳሪን ለመድረስ ለYouTube ሰርጣቸው በሚጠቀሙበት የGoogle መለያቸው ላይ ባለ 2-ደረጃ ማረጋገጫን ማብራት አለባቸው። የበለጠ ለመረዳት

የእርስዎን የYouTube መለያ ደህንነት መጠበቅ የእርስዎን መለያ ወይም ሰርጥ እንዳይጠለፍ ወይም እንዳይነጠቅ ለመከላከል ያግዛል።

ማስታወሻ፦ የእርስዎ መለያ የተጠለፈ ከመሰልዎት፣ እንዴት ደህንነቱን መጠበቅ እንደሚችሉ ይረዱ።

የእርስዎን የYouTube መለያ ደህንነት ያስጠብቁ

ጠንካራ የይለፍ ቃል ይምረጡ እና በምስጢር ይያዙት

ጠንካራ የይለፍ ቃል ይፍጠሩ

ጠንካራ የይለፍ ቃል የእርስዎን የግል መረጃ ደህንነቱ እንደተጠበቀ እንዲቆይ ያግዛል እንዲሁም ሌላ የሆነ ሰው ወደ የእርስዎ መለያ እንዳይገባ ይከላከላል።

ጠንካራ እና ውስብስብ የሆነ የይለፍ ቃል ይፍጠሩ፦ 8 ቁምፊዎችን ወይም ከዚያ በላይ ይጠቀሙ። የፊደላት፣ የቁጥሮች እና የምልክቶች ማናቸውም ቅንብር ሊሆን ይችላል።

የእርስዎን የይለፍ ቃል ልዩ እንዲሆን ያድርጉት፦ የእርስዎን የYouTube መለያ የይለፍ ቃል በሌሎች ጣቢያዎች ላይ አይጠቀሙበት። ሌላው ጣቢያ ከተጠለፈ፣ የይለፍ ቃሉ ወደ የእርስዎ የYouTube መለያ ለመግባት ሊያገለግል ይችላል።

የግል መረጃን እና የተለመዱ ቃላትን ከመጠቀም ይቆጠቡ፦ እንደ የእርስዎ የልደት ቀን፣ እንደ «ይለፍ ቃል» ወይም እንደ «1234» የመሳሰሉ የተለመዱ ሥርዓተ ጥለቶችን አይጠቀሙ።

የእርስዎን የይለፍ ቃል ከጠላፊዎች ይጠብቁ

ለChrome የይለፍ ቃል ማንቂያን በማብራትየእርስዎን የይለፍ ቃል ወደ የGoogle ጣቢያ ያልሆነ ጣቢያ በሚያስገቡበት ጊዜ ማሳወቂያ እንዲደርስዎት ይድርጉ። ለምሳሌ፣ Google እንደሆነ በሚያስመስል ጣቢያ ላይ የእርስዎን የይለፍ ቃል ካስገቡ ማሳወቂያ እንዲደርስዎት ይደረጋል በመሆኑም የእርስዎን የYouTube መለያ የይለፍ ቃል መለወጥ ይችላሉ።

የይለፍ ቃልዎችዎን ያስተዳድሩ

የይለፍ ቃል አስተዳዳሪ ጠንካራ፣ ልዩ የይለፍ ቃላትን እንዲፈጥሩ እና እንዲያስተዳድሩ ሊያግዝዎት ይችላል። የChromeን ወይም ሌላ የታመነ የይለፍ ቃል አስተዳዳሪ ለመጠቀም ይሞክሩ።
ጠቃሚ ምክር፦ በእርስዎ የGoogle መለያ ውስጥ የተቀመጠ ማናቸውም የይለፍ ቃል ምናልባት የተጋለጠ፣ ደካማ ወይም በበርካታ መለያዎች በተደጋጋሚ ጥቅም ላይ የዋለ መሆኑን ለማወቅ የይለፍ ቃል ፍተሻን ይጠቀሙ።

የእርስዎን በመለያ መግቢያ መረጃ በጭራሽ ለሌላ አያጋሩ

በጭራሽ የይለፍ ቃልዎን ለሌላ አይስጡ። YouTube በጭራሽ የእርስዎን የይለፍ ቃል በኢሜይል፣ በመልዕክት ወይም በስልክ ጥሪ አይጠይቅዎትም። YouTube በጭራሽ እንደ የመታወቂያ ቁጥር፣ ገንዘብ ነክ መረጃ ወይም የይለፍ ቃል የመሳሰለ የግል መረጃን የሚጠይቅ ቅጽ እንዲሞሉ አይልክልዎትም።

መደበኛ የሆነ የደህንነት ፍተሻ ያድርጉ

ለእርስዎ መለያ ግላዊነት የተላበሱ ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት ወደ የደህንነት ፍተሻ ገጽ ይሂዱ እና የእርስዎን መለያ ይበልጥ ለደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን ለማድረግ የተሰጡትን ጠቃሚ ምክሮች ይከተሉ።

የመለያ መልሶ ማግኛ አማራጮችን ያክሉ ወይም ያዘምኑ

የእርስዎ መልሶ ማግኛ ስልክ ቁጥር እና ኢሜይል አድራሻ ለሚከተሉት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፦
  • የሆነ ሌላ ሰው የእርስዎን መለያ ያለ ፈቃድዎ እንዳይጠቀም ለማገድ
  • በእርስዎ መለያ ላይ አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ካለ ማንቂያ እንዲደርስዎት
  • ድንገት በሆነ ምክንያት መለያዎ ከተቆለፈብዎት መልሶ ለማግኘት

ባለ 2-ደረጃ ማረጋገጫን ያብሩ

ባለ 2-ደረጃ ማረጋገጫ ሰርጎ ገብ ወደ የእርስዎ መለያ የይለፍ ቃልዎን የሰረቀ እንኳ ቢሆን ወደ መለያዎ እንዳይገባ ለመከላከል ያግዛል። የእርስዎ አማራጮች እነዚህ ናቸው፦
የደህንነት ቁልፎች የጽሑፍ መልዕክት ኮዶችን የሚጠቀሙ የማስገር ቴክኒኮችን ለመከላከል ስለሚያግዙ ይበልጥ ጠንካራ የሆኑ የማረጋገጫ አማራጭ ናቸው።

ከእርስዎ መለያ አጠራጣሪ ሰዎችን ያስወግዱ

የእርስዎን መለያ የሚያስተዳድሩትን ሰዎች ካላወቁዋቸው፣ መለያዎ ተጠልፎ ሊሆን እና የሆነ ሌላ ሰው የሆነ ነገርን ለማግኘት የእርስዎን መለያ ባለቤትነት በማረጋገጥ ላይ ያለ ሊሆን ይችላል። እንደ መለያዎ ዓይነት የሚወሰን ሆኖ ሰዎችን መለወጥ ወይም ማስወገድ ይችላሉ።

የማይፈልጓቸውን ጣቢያዎች እና መተግበሪያዎች ያስወግዱ

ለእርስዎ የYouTube መለያ ጥበቃ ለማድረግ፣ የማይታወቁ መተግበሪያዎችን ወይም ከማይታወቁ ምንጮች የመጡ መተግበሪያዎችን ከመጫን ይቆጠቡ። ከእርስዎ የተገናኙ መለያዎች ላይ ማናቸውንም የማይፈልጓቸውን መተግበሪያዎች ያስተዳድሩ ወይም ያስወግዱ።

የእርስዎን ሶፍትዌር ያዘምኑ እና የእርስዎን መለያ በምትኬ ይያዙ

የእርስዎ መለያ፣ ሥርዓተ ክወና ወይም መተግበሪያዎች ቀናቸው ካለፈባቸው፣ ሶፍትዌሩ ከሰርጎ ገቦች ጥቃት የተጠበቀ ሊሆን አይችልም። የእርስዎን ሶፍትዌር የተዘመነ እና በመደበኛነት መለያዎ በምትኬ የሚቀመጥ እንዲሆን ያድርጉ።

አጠራጣሪ ከሆኑ መልዕክቶች እና ይዘት ይጠበቁ

ማስገር ማለት አንድ ሰርጎገብ ልክ እደሚታመን ሰው መስሎ በመቅረብ የግል መረጃን ለመውሰድ ሲቀርብ ማለት ነው። የግል መረጃ የሚከተሉትን ያካትታል፦

  • ገንዘብ ነክ ውሂብ
  • ብሔራዊ መታወቂያ/ማኅበራዊ ዋስትና ቁጥር
  • የክሬዲት ካርድ ቁጥሮች

ሰርጎገቦች ተቋማትን፣ የቤተሰብ አባላትን ወይም የሥራ ባልደረባዎችን መስሎ ለመቅረብ ኢሜይሎችን፣ የጽሑፍ መልዕክቶችን ወይም ድረ ገጾችን ሊጠቀሙ ይችላሉ።

YouTube የይለፍ ቃልዎን፣ የኢሜይል አድራሻዎን ወይም ሌላ የመለያ መረጃዎን በጭራሽ አይጠይቀዎትም። የሆነ ሰው ከYouTube እንደመጣ አስመስሎ እርስዎን ሊያገኝ ሲሞክር በቀላሉ አይታለሉ።
 

ከአጠራጣሪ ጥያቄዎች ይራቁ
  • የእርስዎን የግል ወይም ገንዘብ ነክ መረጃ ለሚጠይቁ አጠራጣሪ ኢሜይሎች፣ የጽሑፍ ፈጣን መልዕክቶች፣ ድረገጾች ወይም የስልክ ጥሪዎች ምላሽ አይስጡ።
  • ከማይታመኑ የድር ጣቢያዎች ወይም ላኪዎች በኢሜይሎች፣ በመልዕክቶች፣ በድረ ገጾች ወይም በብቅ ባዮች የሚመጡ አገናኞች ላይ ጠቅ አያድርጉ።
  • የYouTube ኢሜይሎች ከ @youtube.com ወይም @google.com አድራሻዎች ብቻ ይመጣሉ።

በኢሜይል አድራሻዎች ውስጥ ቀላል የሥርዓተ ፊደል ሕጸጾችን ይፈትሹ

የአጠራጣሪ አስጋሪ ኢሜይል ምሳሌ

አጠራጣሪ ድረ ገጾችን ይራቁ

Google Chrome እና ፍለጋ ስለ አጠራጣሪ ይዘት እና የማይፈለግ ሶፍትዌር እርስዎን ማስጠንቀቅ በሚችሉበት ሁኔታ የተዘጋጁ ናቸው።
እነዚህን ማስጠንቀቂያዎች እንዴት በChrome እና በፍለጋ ላይ እንደሚያስተዳድሯቸው ይወቁ።

አይፈለጌ መልዕክትን ወይም ማስገርን ሪፖርት ያድርጉ

ራስዎን ከማስገር አደጋ ለመጠበቅ፣ የእርስዎን የየልፍ ቃል ከmyaccounts.google.com በስተቀር ሌላ ገጽ ላይ በጭራሽ አያስገቡ። አይፈለጌ መልዕክት ወይም አስጋሪ እንደሆኑ የሚጠረጥሯቸውን ቪዲዮዎች በYouTube ላይ ካገኙ፣ እባክዎ በYouTube ቡድን ግምገማ እንዲደረግባችው ይጠቁሟቸው። ስለ አይፈለጌ መልዕክት እና ማስገር ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት እባክዎ የብሔራዊ ሳይበር ደህንነት ትብብር ማዕከልን ይጎብኙ።
ጠቃሚ ምክር፦ በእኛ ማስገር ነክ ጥያቄዎች.] ተጠቅመው ስለ ማስገር የበለጠ ይረዱ።

በእርስዎ ሰርጥ ላይ ያሉትን ፈቃዶች ያቀናብሩ እና ይፈትሹ

ፈጣሪው እርስዎ ከሆኑ፣ የሆነ ሌላ ሰው የእርስዎን Google መለያ መድረስ በማይችልበት ሁኔታ የYouTube ሰርጥዎን እንዲያስተዳድር መጋበዝ ይችላሉ። የሆኑ ሰው ሰርጣቸውን እንደሚከተለው እንዲደርሱ ይጋብዙ፦

  • አስተዳዳሪ፦ ሌሎችን ማከል ወይም ማስወገድ እንዲሁም የሰርጥ ዝርዝሮችን አርትዕ ማድረግ ይችላል።
  • አርታዒ፦ ሁሉንም የሰርጥ ዝርዝሮች አርትዕ ማድረግ ይችላል።
  • ተመልካች፦ ሁሉንም የሰርጥ ዝርዝሮ ማየት ይችላል (ሆኖም አርትዕ ማድረግ ግን አይችልም)።
  • ተመልካች (ውስን መብት)፦ ከገቢ መረጃ በስተቀር ሁሉንም የሰርጥ ዝርዝሮ ማየት ይችላል (ሆኖም አርትዕ ማድረግ ግን አይችልም)።

የእርስዎን የሰርጥ ፈቃዶች እንዴት ማቀናበር እና መፈተሽ እንደሚችሉ ይረዱ.

ማስታወሻ፦ የምርት መለያ ስም ካልዎት፣ የሆነ ሰውን የእርስዎን የGoogle መለያ እና የYouTube ሰርጥ እንዲያስተዳድርልዎት መጋበዝ ይችላሉ። የምርት ልዩ ስም እንዳልዎት ያረጋግጡt እና እንዴት የምርት ልዩ ስም መለያ ፈቃዶችን ማስተዳደር እንደሚቻል ይረዱ

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
3822014230411624500
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
59
false
false