የንግድ ምልክት

የንግድ ምልክት የአንድን ምርት ምንጭ የሚለይ እና ከሌሎች ምርቶች የሚለይ ቃል፣ ምልክት ወይም የሁለቱም ጥምር ነው። የንግድ ምልክት በሕጋዊ ሂደት በኩል በአንድ ኩባንያ ወይም በሌላ ሕጋዊ አካል የተገኘ ነው። አንዴ ከተገኘ በኋላ እነዚያን ምርቶች በተመለከተ ለባለቤቱ ለሚመለከተው የተወሰኑ የንግድ ምልክት አጠቃቀም መብቶችን ይሰጣል።

የንግድ ምልክት ጥሰት የምርቱን ምንጭ በተመለከተ ማምታታት ሊያስከትል በሚችል መልኩ አግባብ ያልሆነ ወይም ያልተፈቀደ የንግድ ምልክት አጠቃቀም ነው። የYouTube መመሪያዎች የንግድ ምልክቶችን የሚጥሱ ቪድዮዎችን እና ሰርጦችን ይከለክላሉ። ይዘትዎ የሌላ ሰውን የንግድ ምልክቶች ማምታታትን ሊያስከትል በሚችል መንገድ የሚጠቀም ከሆነ ቪድዮዎችዎ ሊታገዱ ይችላሉ። እንዲሁም ሰርጥዎ ሊታገድ ይችላል።

የእርስዎ የንግድ ስም ጥሰት እየደረሰበት ነው ብለው የሚያስቡ ከሆነ YouTube በፈጣሪዎች እና በንግድ ምልክት ባለቤቶች መካከል ያሉ ሙግቶችን እንደማያገላግል ያስታውሱ። በዚህም ምክንያት የንግድ ምልክት ባለቤቶች ጥያቄ የተነሳበትን ይዘት ከለጠፉት ፈጣሪ ጋር በቀጥታ እንዲነጋገሩ እናበረታታለን። ሰቃዩን በቀጥታ ማነጋገር ሁሉንም ሰው በሚጠቅም መልኩ ችግሩን በፍጥነት ሊፈታ ይችላል። አንዳንድ ፈጣሪዎች በሰርጣቸው ውስጥ ሊገኙ የሚችሉባቸውን መንገዶች ይዘረዝራሉ።

ከሚመለከታቸው የመለያ ባለቤት ጋር መፍትሄ ላይ መድረስ ካልቻሉ በእኛ የንግድ ምልክት ቅሬታ ቅጽ በኩል የንግድ ምልክት ቅሬታ ያስገቡ። 

የንግድ ምልክት ቅሬታ ያስገቡ

YouTube ምክንያታዊ የሆኑ ቅሬታዎችን በተወሰነ ደረጃ ለመመርመር ፈቃደኛ ነው እና ግልጽ በሆኑ የጥሰት ጉዳዮች ላይ ይዘትን ያስወግዳል። ሙግቶችን ለመፍታት እንዲረዳ YouTube ማንኛውንም እርምጃ ከመውሰዱ በፊት እያንዳንዱን የንግድ ምልክት ቅሬታ ወደ ሰቃዩ ያስተላልፋል። ይህ ሰቃዩ ማናቸውም ሊፈጠሩ የሚችሉ የንግድ ምልክት ችግሮችን እንዲፈቱ ያስችላቸዋል። 

እንዲሁም በኢሜይል፣ ፋክስ እና በደብዳቤ የሚገቡ ነፃ ቅጽ የንግድ ምልክት ቅሬታዎችን እንቀበላለን።

ቅሬታዎ ከሐሰት ምርቶች ሽያጭ ወይም ማስተዋወቅ ጋር የተገናኘ ከሆነ እባክዎ የአስመስሎ መሥራት ቅሬታ ያስገቡ።

ቅሬታዎ እንደ ዘፈን፣ ፊልም ወይም መጽሐፍ ካለ ጥበቃ የሚደረግለት ሥራ ጋር የሚዛመድ ከሆነ እባክዎ የቅጂ መብት ቅሬታ ያስገቡ።

 

 

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
10141860125272733832
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
59
false
false