አንዳንድ አስተያየቶች በእርስዎ ቪድዮ ወይም ሰርጥ ላይ ከመታየታቸው በፊት ለመያዝ መምረጥ ይችላሉ። እንዴት የአስተያየት ቅንብሮችዎን መለወጥ እንደሚቻል ይወቁ።
ለቪድዮዎች የአስተያየት ቅንብሮች
ለአንድ የተወሰነ ቪድዮ አስተያየቶችን ለማብራት፣ ባሉበት ለማቆም ወይም ለማጥፋት መምረጥ ይችላሉ። አስተያየቶች ሲበሩ የሚያዙ ካሉ የትኛዎቹ እንደሆኑ መወሰን ወይም አስተያየት መስጠትን ለደንበኝነት ተመዝጋቢዎች እና አባላት ብቻ መገደብ ይችላሉ።
በርቷልአስተያየቶችን ለማብራት ሲመርጡ የሚያዙ እንደሆኑ ለመምረጥም አማራጭ ይኖርዎታል። አማራጮችዎን ለመመልከት የአስተያየት አወያይ ተቆልቋይ ምናሌ ላይ መታ ማድረግ ይችላሉ፦
- ምንም፦ ማናቸውንም አስተያየቶች አትያዝ።
- መሠረታዊ፦ አግባብ ላይሆኑ የሚችሉ አስተያየቶችን ያዝ።
- ጥብቅ፦፦ ሰፋ ያሉ አግባብ ላይሆኑ የሚችሉ አስተያየቶችን ያዝ።
- ሁሉንም ያዝ፦ ሁሉም አስተያየቶችን ያዝ።
የተያዙ አስተያየቶች፦
- እስከ 60 ለሚደርሱ ቀናት YouTube ስቱዲዮ ውስጥ ይቆያሉ።
- ካላጸደቋቸው በስተቀር በይፋ አይታዩም።
- ከ100 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ለግምገማ ይገኛሉ።
እንዲሁም ማን አስተያየት መስጠት እንደሚችል ለደንበኝነት ተመዝጋቢዎች እና የሰርጥዎ ከፋይ አባላት ብቻ ለመገደብ መምረጥ ይችላሉ። አስተያየቶችዎን ካበሩ በኋላ ማን አስተያየት መስጠት ይችላል ተቆልቋይ ላይ መታ ያድርጉ እና የደንበኝነት ተመዝጋቢዎች እና አባላት የሚለውን ይምረጡ። ከዚያም ዝቅተኛ የደንበኝነት ምዝገባ ጊዜ ተቆልቋይ ላይ መታ በማድረግ ዝቅተኛ የደንበኝነት ምዝገባ ጊዜን ማቀናበር ይችላሉ። አማራጮቹ፦ ማንኛውም የቆይታ ጊዜ፣ 1 ሰዓት፣ 1 ቀን እና 1 ሳምንት ናቸው።
ባለበት አቁም አማራጭን ሲመርጡ ነባር አስተያየቶችዎን ያቆያሉ፣ ነገር ግን አስተያቶችን መልሰው እስከሚያበሩ ድረስ በዚያ ቪድዮ ላይ ማናቸውም ተጨማሪ አይደርሱዎትም።
በተለያዩ ምክንያቶች አስተያየቶችን ባሉበት ለማቆም ሊመርጡ ይችላሉ። ለምሳሌ አዳዲስ አስተያየቶች ሳይመጡ በቪድዮ ላይ ድንገተኛ የአስተያየቶች ጭማሪን ለመገምገም ተጨማሪ ጊዜ ሊፈልጉ ይችላሉ። በድጋሚ አዳዲስ አስተያየቶችን ማግኘት ለመጀመር የሚፈልጉ ከሆነ በማንኛውም ጊዜ ላይ አስተያየቶችን ማብራት ይችላሉ።አጥፋ
የሰርጥ ደረጃ የአስተያየት ቅንብሮች
የተደበቁ ተጠቃሚዎች
የጸደቁ ተጠቃሚዎች
ነባሪ የአስተያየት ቅንብሮች
ስለ የአስተያየት ቅንብሮች የሚነሱ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች
የተወሰኑ ቃላትን፣ አገናኞችን ወይም ተጠቃሚዎችን ከአንድ የተወሰነ ቪዲዮ ማገድ እችላለሁ?
ከተደበቁ ተጠቃሚዎች የተሰጡ አስተያየቶችን መገምገም እችላለሁ?
ለተወሰኑ ቃላት ወይም አገናኞች የታገዱ አስተያየቶችን መገምገም እችላለሁ?
አስተያየቶችን ካጠፋሁ እና እንደገና መልሼ ካበራሁ የድሮ አስተያየቶቼ ተመልሰው ይመጣሉ?
ቅንብሮቼን ከለወጥኩ ነባር እና የወደፊት አስተያየቶች ተጽዕኖ ይደርስባቸዋል?
የሰርጥ ደረጃ ቅንብሮች፣ የቪድዮ ደረጃ ቅንብሮች እና የታገዱ ቃላት፣ የተደበቁ ተጠቃሚዎች እና የታገዱ አገናኞች ላይ የተደረጉ ለውጦች በሙሉ በወደፊት አስተያየቶች ላይ ይተገበራሉ።
ነባር አስተያየቶች ተጽዕኖ የሚደርስባቸው የሚከተሉትን የሚያደርጉ ከሆነ ብቻ ነው፦
- በቪድዮ ላይ አስተያየቶችን ሲያጠፉ። በሚጠፉበት ጊዜ አስተያየቶችን መልሰው እስከሚያበሩ ድረስ ነባር አስተያየቶችን አይመለከቱም።
- ተጠቃሚን ሲደብቁ። አንድ ተጠቃሚ ተደብቀው ከሆነ እነሱ የሰጧቸው አስተያየቶች በማናቸውም ቪድዮዎችዎ ላይ አይታዩም።
በመሠረታዊ እና ጥብቅ ሁነታ ውስጥ የሚያዙት ምን ዓይነት ቪድዮዎች ናቸው?
መሠረታዊ የአስተያየት አወያይን መምረጥ YouTube ስቱዲዮ ውስጥ አይፈለጌ መልዕክት፣ ራስ ማስተዋወቂያ፣ ትርጉም የማይሰጡ ሊሆኑ የሚችሉ ወይም አግባብ ላይሆኑ የሚችሉ አስተያየቶችን ይይዛል። እነዚህ አስተያየቶች የሚታተሙት እርስዎ ካጸደቋቸው ብቻ ነው።
ለሰርጥዎ ይበልጥ ከፍተኛ ደረጃ ያለው ጥበቃ የሚፈልጉ ከሆነ ጥብቅ የአስተያየት አወያይን መምረጥ የሚያዙ የአስተያየቶች ብዛትን ይጨምራል።
እነዚህ ቅንብሮች መያዝ የሚኖርባቸውን አስተያየቶች ለይተው ለማወቅ ሰው ሠራሽ አስተውሎት የሚጠቀሙ እንደመሆናቸው አንዳንድ ጊዜ በትክክል ላያገኙት ይችላሉ። የሰርጥ ባለቤቶች በቪድዮዎቻቸው ላይ የሚታዩ አስተያየቶችን ችላ ለማለት፣ ለማስወገድ ወይም ለማጽደቅ መምረጥ ይችላሉ።
ግብረመልስ ላክ የሚለውን በመምረጥ አስተያየቶችን YouTube Studio ውስጥ ሲገመግሙ ግብረመልስን በቀጥታ በምርቱ ውስጥ ማጋራት ይችላሉ።
በጊዜ ሂደት ሥርዓቶቻችንን ለማሻሻል ስንሠራ በእነዚህ ቅንብሮች የተገኙ አስተያየቶች ትክክለኛነት እና ብዛት ሊለወጥ ይችላል።