ያወረድኩትን ቪዲዮ ማየት አልችልም

ቪድዮዎችን እንዴት ማውረድ እንደሚችሉ ይረዱ እና ችግርዎን ለመፍታት ከታች ያሉትን እርምጃዎች ይገምግሙ።

ብዙ የተለመዱ ችግሮችን እንደሚፈታ የመጀመሪያ እርምጃ የYouTube መተግበሪያ ወይም የአሳሽ መስኮት ይዝጉት እና በድጋሚ ይክፈቱት። ቀጣይ መሣሪያዎን እንደገና ማስጀመር ይሞክሩ።

በአዲስ መሣሪያዎች ላይ ቪዲዮዎችን እንደገና ያውርዱ

በቅርቡ አዲስ መሣሪያ ይዘው ከሆነ፣ ማየት የሚፈልጓቸውን ማናቸውንም ቪዲዮዎች እንደገና ማውረድ ያስፈልግዎታል። ወደ ተመሳሳይ መለያ ገብተው ቢሆንም እንኳ ቪዲዮዎች ወደ ሌሎች መሣሪያዎች አይተላለፉም። ቪድዮዎች የሚወርዱት ለዚያው መሣሪያ ብቻ ነው።

አባልነትዎ ጊዜው ያላለፈበት መሆኑን ያረጋግጡ

የYouTube Premium አባልነትዎ ጊዜው እንዳላለፈበት ያረጋግጡ።

በYouTube መተግበሪያው ውስጥ የእርስዎ የመገለጫ ፎቶ እና በመቀጠል ቅንብሮች እና በመቀጠል ግዢዎች እና አባልነቶች የሚለውን መታ ያድርጉ።

  • በቅርቡ የYouTube Premium መዳረሻዎን ካጡ እና በድጋሚ ለደንበኝነት ተመዝግበው ከሆነ፣ እንደገና ለደንበኝነት ከተመዘገቡ በኋላ የተቀመጡ ቪድዮዎች እስኪታዩ ድረስ ጥቂት ሰዓታትን ይወስዳል።
  • አንድን ቪድዮ ወዲያው ማየት ካለብዎት ምናሌ Three-dot menu vertical ላይ መታ ያድርጉ እና እንደገና ለማውረድ ሞክር የሚለውን ይምረጡ።
  • የYouTube Premium አባልነትዎ ካበቃ እርስዎ ላወረዷቸው ቪድዮዎች መዳረሻ አይኖርዎትም። ለውርዶችዎ መዳረሻን ዳግም ለማግኘት ለPremium አባልነት ይመዝገቡ

ወደ YouTube Premium መግባትዎን ያረጋግጡ

ከYouTube Premium አባልነትዎ ጋር ወደተጎዳኘው የGoogle መለያዎ መግባትዎን ያረጋግጡ፡-

  • ከYouTube Premium ጋር ከተጎዳኘው መለያ ዘግተው ለመውጣት እና መልሰው በመለያ ለመግባት ይሞክሩ።
  • የYouTube Premium አርማ የሚታየዎት መሆኑን ያረጋግጡ (ከYouTube አርማ ይልቅ)። በYouTube የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ውስጥ ወይም በኮምፒውተርዎ ላይ የYouTube Premium አርማን በመተግበሪያዎ ወይም በአሳሽዎ የላይኛው ግራ ጥግ ውስጥ ሊያዩ ይገባል።
በዘመናዊ ቲቪ ላይ YouTubeን እየተጠቀሙ ነው?
  • በYouTube Premium አባልነትዎ አማካኝነት ከእርስዎ TV ጋር ወደተጎዳኘው መለያ መግባትዎን ያረጋግጡ።
  • ወደ ቲቪ እየወሰዱ ከሆነ በቴሌቪዥኑ እና በሁለቱም በሚጠቀሙበት ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ላይ መግባትዎን ያረጋግጡ። 
  • Google Home እየተጠቀሙ ከሆነ በGoogle Home መተግበሪያ ውስጥ ወደ ትክክለኛው መለያ መግባትዎን ያረጋግጡ።

ድጋፍን ያነጋግሩ እና የምርት ግብረመልስ ያስገቡ

አሁንም ችግር እያጋጠመዎ ከሆነ፣ ድጋፍ ክፍልን ያነጋግሩ። ድጋፍ ክፍልን በሚያነጋግሩ ጊዜ፣ የሚከተሉትን ይጥቀሱ፦

  • የስህተት መልዕክት ያያሉ?
  • ምን ያሳያል?፡ትክክለኛው ጽሁፍስ ምን ይላል? ከተቻለ ቅጽበታዊ ገፅ ዕይታን ያካትቱ።
የምርት ግብረመልስን ለYouTube ይላኩ፦
  • ስለ ችግርዎም ግብረመልስ ማስገባት ይችላሉ። ምላሽ አያገኙም፣ ይሁን እንጂ ግብረመልስዎ ለYouTube ይጋራል።
  • የምርት ግብረመልስ ለመላክ የመገለጫ ፎቶዎን ይምረጡ እና በመቀጠል ግብረመልስ Feedback YouTube ውስጥ።
  • ግችርዎን ለመረዳት ይረዳን ዘንድ የ"System logs" ሳጥን ላይ ምልክት ማድረግዎን ያረጋግጡ።

ተመለስ ወደ ለYouTube Premium አባል ጥቅማጥቅሞች መላ ይፈልጉ

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
15252179903899131171
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
59
false
false