በዳራ ማጫወት እይሰራ አይደለም

በዳራ ማጫወት የሚሰራው በYouTube ሞባይል መተግበሪያዎች ውስጥ ብቻ ሲሆን የYouTube Premium አባልነት ያስፈልገዋል። አንዳንድ ቪድዮዎች ለዳራ ማጫወት ወይም ከመስመር ውጭ ለመውረድ አይገኙም፣ የሰርጥ አባልነት ቢኖረዎትም እንኳ። ችግርዎን ለመፍታት ለማገዝ ከታች ያሉትን ደረጃዎች ይገምግሙ።

የተለመዱ የመላ ፍለጋ ደረጃዎች

 የYouTube መተግበሪያውን ዳግም ያስነሱት ወይም መሣሪያዎን እንደገና ያስጀምሩት

የYouTube መተግበሪያው ወይም የእርስዎ ተንቀሳቃሽ መሣሪያ ለተወሰነ ጊዜ እያሄደ ከነበረ የዳራ ማጫወት በተለሳለሰ ሁኔታ እንዲሰራ በቂ ግብዓቶች ላይኖሩ ይችላሉ። የYouTube መተግበሪያን ዘግተው ወይም ስልክዎን ዳግም አስነስተው ይሞክሩ።

አባልነትዎ ጊዜው ያላለፈበት መሆኑን ያረጋግጡ

የYouTube Premium አባልነትዎ ጊዜው ያላለፈበት መሆኑን ያረጋግጡ። በYouTube መተግበሪያው ውስጥ የእርስዎን የመገለጫ ስዕል እና በመቀጠል የሚከፈልባቸው አባልነቶች መታ ያድርጉና ታች ወደ አስተዳድር ይሸብልሉ።

በቅርቡ የYouTube Premium መዳረሻ ካጡ እና ከዚያ እንደገና ለደንበኝነት ከተመዘገቡ በድጋሚ ከተመዘገቡ በኋላ የተቀመጡ ቪዲዮዎች ዳግም የሚገኙ እስክሆኑ እስኪታዩ ድረስ ጥቂት ሰዓታትን እንደሚወስድ ልብ ይበሉ። አንድ ቪድዮ ወዲያውኑ ማየት ካለብዎት ተጨማሪን '' መታ ያድርጉ እና ለማውረድ እንደገና ይሞክሩን ይምረጡ።

እንደገና ወደ YouTube Premium ለመግባት ይሞክሩ

ከYouTube Premium አባልነትዎ ጋር ወደተጎዳኘው መለያ መግባትዎን ያረጋግጡ።

  • ከYouTube Premium ጋር ከተጎዳኘው መለያ ዘግተው ለመውጣት እና መልሰው ለመግባት ይሞክሩ።
  • በYouTube ውስጥ የYouTube Premium አርማ (ከYouTube አርማ ይልቅ) ማየትዎን ያረጋግጡ።

በአካባቢዎ ውስጥ የYouTube Premium ተገኝነትን ያረጋግጡ

የYouTube Premium ጥቅማጥቅሞች የሚሰሩት YouTube Premium በሚገኝባቸው አገሮች ላይ ብቻ ነው። YouTube Premium የጀመረበት አካባቢ ላይ መሆንዎን ያረጋግጡ

የዳራ መልሶ ማጫወቻ ቅንብሮችዎን ይፈትሹ

ቅንብሩን አለማሰናከልዎን ለማረጋገጥ በYouTube መተግበሪያው ውስጥ የእርስዎን የዳራ መልሶ ማጫወቻ ቅንብሮችዎን ይፈትሹ።

የYouTube መተግበሪያዎን ያዘምኑ

የቅርብ ጊዜውን የYouTube መተግበሪያ ስሪት እየተጠቀሙ መሆንዎን ያረጋግጡ። የመሣሪያዎን የመተግበሪያ መደብር ይጎብኙ እና ለYouTube መተግበሪያው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ዝማኔዎች ካሉ ይፈትሹ።

ስልክዎ አዲስ ከሆነ ወይም ስልክዎ በቅርቡ ወደነበረበት መልሰውት ከሆነ የድሮ የYouTube መተግበሪያውን ስሪት (ለምሳሌ ከ12.0 በታች የሆኑ ስሪቶች ጊዜው ያለፈባቸው ተደርገው ይታሰባሉ) ይዞ ሊሆን ይችላል።

የስልክዎን የተንቀሳቃሽ ስልክ ውሂብ ቅንብሮች ይፈትሹ

ለYouTube የዳራ ውሂብን ማንቃትዎን ለማረጋገጥ በተንቀሳቃሽ መሣሪያዎ ላይ ቅንብሮቹን ይፈትሹ።

የሚሞከሩ ተጨማሪ ደረጃዎች

ሌሎች መተግበሪያዎች ኦዲዮን እያጫወቱ አለመሆናቸውን ያረጋግጡ

ሌሎች የከፈቷቸው ማናቸውም መተግበሪያዎች ኦዲዮን እያጫወቱ አለመሆናቸውን ለማረጋገጥ ይፈትሿቸው። ሌሎች መተግበሪያዎች ኦዲዮን እያጫወቱ ሳለ የዳራ ማጫወት አይሰራም።

የበይነመረብ ግንኙነትዎን ጥንካሬ ይፈትሹ

የቪድዮዎ ውርዶች ጠንካራ የበይነመረብ ግንኙነት ያስፈልጋቸዋል። መሣሪያዎ ከ3 ሜቢ/ሴ ወይም ከዚያ በላይ ፈጣን ከሆነ አውታረ መረብ ጋር የተገናኘ መሆኑን ወይም የ3ጂ፣ የ4ጂ ወይም የLTE ፍጥነቶችን ከሚደግፍ የተንቀሳቃሽ ስልክ አውታረ መረብ ጋር መገናኘቱን ያረጋግጡ። የአሁኑ የበይነመረብ ፍጥነትዎ ምን ያህል እንደሆነ እርገጠኛ ካልሆኑ መስመር ላይ ፍጥነትዎን መሞከር ይችላሉ።

የስልክዎን የማሳወቂያ ቅንብሮች ይፈትሹ

ሁሉንም የYouTube መተግበሪያው ማሳወቂያዎችን አለማገድዎን ያረጋግጡ። ይህን በመሣሪያዎ ቅንብሮች ውስጥ ማረጋገጥ ይችላሉ። ማሳወቂያዎችን ካገዱ የYouTube መተግበሪያው በተለሳለሰ ሁኔታ ማሄድ ላይችል እና/ወይም በዳራ በይነመረቡን መድረስ ላይችል ይችላል።

ይህ ከተከሰተ የYouTube ማሳወቂያዎችን በስርዓተ ክወና ደረጃው ላይ ዳግም ማንቃት ይኖርብዎታል፣ እና አሁንም ማሳወቂያዎችን መቀበል የማይፈልጉ ከሆነ ከYouTube መተግበሪያ ቅንብሮች ሆነው ሊያሰናክሏቸው ይችላሉ።

ድጋፍን ያነጋግሩ እና የምርት ግብረመልስ ያስገቡ

አሁንም እየተቸገሩ ከሆነ ድጋፍን ያነጋግሩ። ድጋፍን በሚያገኙበት ጊዜ እባክዎ የሚከተሉትን ይጥቀሱ፦
  • ድምጽ ልክ እርስዎ ከመተግበሪያው ሲወጡ የሚያቆም ወይም ለተወሰነ ጊዜ ተጫውቶ ግን ሳይጠበቅ የሚያቆም እንደሆነ እባክዎ ይግለጹ።
  • እባክዎ ወደ መተግበሪያው ሲመለሱ ማናቸውም የሚያዩዋቸውን የስህተት መልዕክቶች ይግለጹ።
  • እባክዎ የውስጠ-መተግበሪያ ግብረመልስ ያስገቡ።
የምርት ግብረመልስ ወደ YouTube ይላኩ፦
  • እንዲሁም የውስጠ-ምርት ግብረመልስ ማስገባት ይችላሉ። ምላሽ አያገኙም፣ ነገር ግን ግብረመልስዎ ለYouTube ምርት ቡድኖች ይጋራል።
  • ይህን ለማድረግ የእርስዎ የመገለጫ ፎቶን እና በመቀጠል ግብረመልስን Feedback ይምረጡ።
  • በ«የስርዓት ምዝግብ ማስታወሻዎች» ሳጥኑ ላይ ምልክት ማድረግዎን ያረጋግጡ። ይህ የእርስዎን ችግር በተሻለ ሁኔታ እንድንረዳ ያግዘናል። 

 

ተመለስ ወደ ለYouTube Premium አባል ጥቅማጥቅሞች መላ ይፈልጉ  

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
642574494051314853
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
59
false
false