ቪድዮዎች ማውረድ አልቻልኩም

ማስታወሻ፡- YouTube Premium ከሌለዎት ወይም ማውረድ ለእርስዎ የሚገኝ ካልሆነ የአውርድ አዝራሩ ለልጆች በተዘጋጁ ቪድዮዎች ላይ የማይገኝ እና የደበዘዘ ይሆናል። የYouTube Premium አባልነትዎ ካበቃ እርስዎ ላወረዷቸው ቪድዮዎች መዳረሻ አይኖርዎትም።

ወደ YouTube Premium መግባትዎን ያረጋግጡ

ከYouTube Premium አባልነትዎ ጋር ወደተጎዳኘው የGoogle መለያዎ መግባትዎን ያረጋግጡ፡-
  • ከYouTube Premium ጋር ከተጎዳኘው መለያ ዘግተው ለመውጣት እና መልሰው በመለያ ለመግባት ይሞክሩ።
  • የYouTube Premium አርማ የሚታየዎት መሆኑን ያረጋግጡ (ከYouTube አርማ ይልቅ)። በYouTube የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያ ውስጥ ወይም በኮምፒውተርዎ ላይ የYouTube Premium አርማን በመተግበሪያዎ ወይም በአሳሽዎ የላይኛው ግራ ጥግ ውስጥ ሊያዩ ይገባል።
በዘመናዊ ቲቪ ላይ YouTubeን እየተጠቀሙ ነው?
  • በYouTube Premium አባልነትዎ አማካኝነት ከእርስዎ TV ጋር ወደተጎዳኘው መለያ መግባትዎን ያረጋግጡ።
  • ወደ ቲቪ እየወሰዱ ከሆነ በቴሌቪዥኑ እና በሁለቱም በሚጠቀሙበት ኮምፒውተር ወይም መሣሪያ ላይ መግባትዎን ያረጋግጡ። 
  • Google Home እየተጠቀሙ ከሆነ በGoogle Home መተግበሪያ ውስጥ ወደ ትክክለኛው መለያ መግባትዎን ያረጋግጡ።

«»አባልነትዎ ጊዜው ያላለፈበት መሆኑን ያረጋግጡ

የYouTube Premium አባልነትዎ ጊዜው እንዳላለፈበት ያረጋግጡ።

በYouTube መተግበሪያው ውስጥ የእርስዎ የመገለጫ ፎቶ እና በመቀጠል ቅንብሮች እና በመቀጠል ግዢዎች እና አባልነቶች የሚለውን መታ ያድርጉ።

  • በቅርቡ የYouTube Premium መዳረሻዎን ካጡ እና በድጋሚ ለደንበኝነት ተመዝግበው ከሆነ፣ እንደገና ለደንበኝነት ከተመዘገቡ በኋላ የተቀመጡ ቪድዮዎች እስኪታዩ ድረስ ጥቂት ሰዓታትን ይወስዳል።
  • አንድን ቪድዮ ወዲያው ማየት ካለብዎት ምናሌ Three-dot menu vertical ላይ መታ ያድርጉ እና እንደገና ለማውረድ ሞክር የሚለውን ይምረጡ።
  • የYouTube Premium አባልነትዎ ካበቃ እርስዎ ላወረዷቸው ቪድዮዎች መዳረሻ አይኖርዎትም። ለውርዶችዎ መዳረሻን ዳግም ለማግኘት ለPremium አባልነት ይመዝገቡ

«»በአካባቢዎ ውስጥ የYouTube Premium ተገኝነትን ያረጋግጡ

YouTube Premium benefits only work in countries/regions where YouTube Premium is available. Check that you're in a location where YouTube Premium is available.

የማውረድ ቅንብሮችዎን ይፈትሹ

በተንቀሳቃሽ ስልክ ውሂብ ላይ ሳሉ ማውረድ እየሞከሩ ከሆነ እና ካልቻሉ ውርዶች ለWi-Fi ብቻ ተገድበው አለመሆኑን ለማረጋገጥ በመተግበሪያው ውስጥ የእርስዎን የማውረድ ቅንብሮች ይፈትሹ

የእርስዎን የYouTube መተግበሪያ ስሪት ይፈትሹ

የቅርብ ጊዜውን የYouTube መተግበሪያ ስሪት እየተጠቀሙ መሆንዎን ያረጋግጡ። የመሣሪያዎን የመተግበሪያ መደብር ይጎብኙ እና ለYouTube መተግበሪያው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ዝማኔዎች ካሉ ይፈትሹ።

ስልክዎ አዲስ ከሆነ ወይም ስልክዎ በቅርቡ ወደነበረበት መልሰውት ከሆነ የድሮ የYouTube መተግበሪያውን ስሪት (ለምሳሌ ከ12.0 በታች የሆኑ ስሪቶች ጊዜው ያለፈባቸው ተደርገው ይታሰባሉ) ይዞ ሊሆን ይችላል።

መሞከር ያለባቸው ተጨማሪ የመላ ፍለጋ እርምጃዎች

«»የበይነመረብ ግንኙነትዎን ጥንካሬ ይፈትሹ

የቪድዮ ውርዶች ጠንካራ የበይነመረብ ግንኙነት ያስፈልጋቸዋል። መሣሪያዎ ከ3 ሜቢ/ሴ ወይም ከዚያ በላይ ፈጣን የሆነ አውታረ መረብ ጋር የተገናኘ መሆኑን ወይም 3ጂ፣ 4ጂ ወይም LTE ፍጥነቶችን ከሚደግፍ የተንቀሳቃሽ ስልክ አውታረ መረብ ጋር መገናኘቱን ያረጋግጡ። የአሁኑ የበይነመረብ ፍጥነትዎ ምን ያህል እንደሆነ እርግጠኛ ካልሆኑ በመስመር ላይ ፍጥነትዎን መሞከር ይችላሉ።

«»ምን ያህል መሣሪያዎች ላይ እንዳወረዱ ይፈትሹ

በበርካታ መሣሪያዎች ላይ ቪድዮዎችን አውርደዋል? ቪድዮዎችን ምን ያህል መሣሪያዎ ላይ ማውረድ እንደሚችሉ ገደብ አለው። አንዴ ገደቡ ላይ ከደረሱ በኋላ «ይህ ቪድዮ ከመስመር ውጭ መቀመጥ አይችልም» የሚል የስህተት መልዕክት ይደርስዎታል። አስቀድመው በተጠቀሙባቸው መሣሪያዎች ላይ አሁንም ቪድዮዎችን ማውረድ ይችላሉ። በYouTube Premium ላይ ስላሉ የመሣሪያ ገደቦች የበለጠ ይወቁ።

የስልክዎን የተንቀሳቃሽ ስልክ ውሂብ ቅንብሮች ይፈትሹ

ለYouTube የዳራ ውሂብን ማንቃትዎን ለማረጋገጥ በተንቀሳቃሽ መሣሪያዎ ላይ ቅንብሮቹን ይፈትሹ።

«»ድጋፍን ያነጋግሩ እና የምርት ግብረመልስ ያስገቡ

አሁንም ችግር እያጋጠመዎ ከሆነ፣ ድጋፍ ክፍልን ያነጋግሩ። ድጋፍ ክፍልን በሚያነጋግሩ ጊዜ፣ የሚከተሉትን ይጥቀሱ፦

  • የስህተት መልዕክት ያያሉ?
  • ምን ያሳያል?፡ትክክለኛው ጽሁፍስ ምን ይላል? ከተቻለ ቅጽበታዊ ገፅ ዕይታን ያካትቱ።
የምርት ግብረመልስን ለYouTube ይላኩ፦
  • ስለ ችግርዎም ግብረመልስ ማስገባት ይችላሉ። ምላሽ አያገኙም፣ ይሁን እንጂ ግብረመልስዎ ለYouTube ይጋራል።
  • የምርት ግብረመልስ ለመላክ የመገለጫ ፎቶዎን ይምረጡ እና በመቀጠል ግብረመልስ Feedback YouTube ውስጥ።
  • ግችርዎን ለመረዳት ይረዳን ዘንድ የ"System logs" ሳጥን ላይ ምልክት ማድረግዎን ያረጋግጡ።

 

ተመለስ ወደ የYouTube Premium አባል ጥቅማጥቅሞችን መላ ይፈልጉ።  

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
1863912364138478367
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
59
false
false