የYouTube ማሳወቂያዎችን ያስተዳድሩ

የYouTube ማሳወቂያዎች ከተወዳጅ ሰርጦችዎ እና ሌሎች ይዘቶች አዳዲስ ቪድዮዎች እና ዝማኔዎች ሲኖሩ ያሳውቁዎታል። ለተመዘገቡባቸው ሰርጦች ማሳወቂያዎችን እንልክልዎታለን እንዲሁም በፍላጎቶችዎ ላይ ተመስርተን ማሳወቂያዎችን ልንልክልዎ እንችላለን። ማሳወቂያዎችዎን ለመቀየር ወይም ሙሉ ለመሉ ለማጥፋት ከታች ያሉትን መመሪያዎች ይጠቀሙ።

የቅርብ ጊዜ ዜና፣ ዝማኔዎች እና ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት ለYouTube ተመልካቾች ሰርጥ ደንበኝነት ይመዝገቡ።
ማስታወሻ፦ የማሳወቂያ ቅንብሮች በመሣሪያ በትንሹ ሊለያዩ ይችላሉ እና እያንዳንዱ አዲስ ሰቀላ ለተመልካቾች ማሳወቂያ አያመጣም።

በማስታወቂያዎች እና በደንበኝነት ምዝገባዎች ምግብ መካከል ያለው ልዩነት

በሁለቱም በሞባይል እና ኮምፒውተር ላይ የሚገኘው የደንበኝነት ምዝገባዎች ምግብ ከእርስዎ የደንበኝነት ምዝገባዎች ማናቸውም በቅርብ ጊዜ የተሰቀሉ ቪድዮዎችን ያሳያል።

ማሳወቂያዎች አዳዲስ ቪድዮዎች ሲኖሩ ለእርስዎ መንገር፣ ከእርስዎ የደንበኝነት ምዝገባዎች ላይ ዝማኔዎችን ማጋራት እና እንዲሁም ሊወዱት ስለሚችሉት ይዘት ለእርስዎ መንገር ይችላል። ኢሜይሎችን፣ ግላዊነት የተላበሱ ማሳወቂያዎችን በሞባይል ላይ ወይም የገቢ መልዕክት ሳጥን ማሳወቂያዎችን በእርስዎ ኮምፒውተር ወይም ተንቀሳቃሽ መሣሪያ ላይ እንልካለን። ለአንድ ሰርጥ በደንበኝነት ሲመዘገቡ የእንቅስቃሴ ድምቀቶች ያሏቸው ግላዊነት የተላበሱ ማሳወቂያዎችን በራስ-ሰር ያገኛሉ።

የገቢ መልዕክት ሳጥን ማሳወቂያዎች በጊዜ ይደራጃሉ፣ ይበልጥ አዳዲስ ማሳወቂያዎች ከላይ ይሆናሉ። አንዳንድ ማሳወቂያዎች ከአዳዲሶቹ በላይ «አስፈላጊ» በሚለው ክፍል ውስጥ ተለይተው ሊቀርቡ ይችላሉ፣ ይህም ለእርስዎ ይበልጥ አግባብነት ሊኖራቸው ይችላሉ ብለን የምናስባቸውን ማሳወቂያዎች ለይቶ ያቀርባል። የአስፈላጊ ማሳወቂያዎች ምሳሌ ለእርስዎ አስተያየት የተሰጠ መልስን ወይም ሰዎች የእርስዎን ቪድዮዎች ሲያጋሩ ሊያካትት ይችላል።

በደንበኝነት ከተመዘገቡበት ሰርጥ ሁሉንም ማሳወቂያዎች ለማግኘት፣ የማሳወቂያ ደወሉን  መታ ያድርጉ። ሁሉንም ማሳወቂያዎች እንደመረጡ ለማመልከት ደወሉ  ወደሚጮህ ደወል አይነት ይቀየራል።

የሰርጡ ታዳሚ ለልጆች እንደተዘጋጀ ተደርጎ ከተቀናበረ ማሳወቂያዎችን አያገኙም። የማሳወቂያ ደወሉ ወደ ማሳወቂያዎች አይኖሩም«» ወደሚለውም ይቀናበራል። ይህን ቅንብር መለወጥ አይችሉም።

ለሰርጥ የደንበኝነት ምዝገባዎች የማሳወቂያ ደውሎቹ ምን ማለት እንደሆኑ

 ግላዊነትን የተላበሱ ማሳወቂያዎች (ነባሪ)
«» ምንም ማሳወቂያዎች የሉም
 ሁሉም ማሳወቂያዎች

ለልጆች የተሰራ ተብሎ ወደተቀናበረ ቪድዮ ወይም ሰርጥ ለደንበኝነት ከተመዘገቡ፤ የደውል ቅንብርዎ ማሳወቂያዎች የሉም ወደሚለው ይቀናበራል «»፣ እና እንዲደበዝዝ ይደረጋል

ከመጀመርዎ በፊት፦ በትክክለኛው መለያ መግባትዎን ያረጋግጡ። የYouTube የመለያ ቅንብሮችዎ እዚህ ሊገኙ ይችላሉ፦

  1. ወደ YouTube በመለያ ይግቡ።
  2. በማያ ገፅዎ አናት ላይ የመገለጫ ሥዕልዎን ጠቅ ያድርጉ።
  3. ቅንብሮች ላይ ጠቅ ያድርጉ።
  4. ማሳወቂያዎች ላይ ጠቅ ያድርጉ።

ከተወሰኑ ሰርጦች ዝማኔዎችን ያግኙ

ለአንድ ሰርጥ ለደንበኝነት ሲመዘገቡ የእንቅስቃሴውን ድምቀቶች የያዙ ማሳወቂያዎችን በራስ-ሰር ያገኛሉ እና ሁሉም አዳዲስ ቪድዮዎች በእርስዎ የደንበኝነት ምዝገባዎች ምግብ ውስጥ ይሆናሉ። አንድ ሰርጥ ይዘት ባተመ ቁጥር እንዲያሳውቅዎ ለማድረግ ወይም ሙሉ በሙሉ እነሱን ለማጥፋት የማሳወቂያ ቅንብሮችዎን መለወጥ ይችላሉ። 

ለአንድ ሰርጥ ደንበኝነት ሲመዘገቡ ከእሱ ዝማኔዎችን ያግኙ፦

  1. ወደ የሰርጥ ገፅ ወይም መመልከቻ ገፅ ይሂዱ።
  2. ለደንበኝነት ካልተመዘገቡ ለደንበኝነት ይመዝገቡ ላይ ጠቅ ያድርጉ። ለአንድ ሰርጥ ደንበኝነት ሲመዘገቡ ግላዊነት የተላበሱ ማሳወቂያዎችን በራስ-ሰር ያገኛሉ።
  3. «ሁሉም ማሳወቂያዎች» እና «ግላዊነት የተላበሱ ማሳወቂያዎች» በማግኘት መካከል ለመቀያየር የማሳወቂያ ደወሉን ጠቅ ያድርጉ።
    • ሁሉም ማሳወቂያዎች - ለማናቸውም ረዥም ቅርጸት ሰቀላዎች እና የቀጥታ ዥረቶች ማሳወቂያዎችን ያገኛሉ። እንዲሁም በእርስዎ የደንበኝነት ምዝገባዎች እና የዕይታ ታሪክ መሠረት ለShorts ግላዊነት የተላበሱ ማሳወቂያዎችን ሊያገኙ ይችላሉ።
    • ግላዊነት የተላበሱ ማሳወቂያዎች - ለአንዳንድ ሰቀላዎች፣ Shorts እና የቀጥታ ዥረቶች ማሳወቂያዎችን ያገኛሉ። የ«ግላዊነት የተላበሰ» ፍቺ እንደየተጠቃሚው ይለያያል።YouTube ለእርስዎ መቼ ማሳወቂያዎችን እንደሚልክ ለመወሰን በርካታ ምልክቶችን ይጠቀማል። ይህ መረጃ የእርስዎን የዕይታ ታሪክ፣ የተወሰኑ ሰርጦችን ምን ያህል ጊዜ እንደሚመለከቱ፣ አንዳንድ ቪድዮዎች ምን ያህል ታዋቂ እንደሆኑ እና ምን ያህል ጊዜ ማሳወቂያዎችን እንደሚከፍቱ ያካትታል።

ከሰርጡ የደንበኝነት ምዝገባዎን ከወጡ እና እንደገና ለደንበኝነት ከተመዘገቡ፣ የማሳወቂያ ቅንብሮችዎ ወደ ግላዊነት የተላበሱ አሊያም ወደ ማሳወቂያዎች የሉም ሊመለሱ ይችላሉ። ለእያንዳንዱ ሰቀላ ማሳወቂያ መግኘት የሚፈልጉ ከሆነ፣ ሁሉንም ማሳወቂያዎች ማብራትዎን እርግጠኛ ይሁኑ።

ማሳወቂያዎችዎን ይፈትሹ

አሁን በኮምፒውተርዎ ላይ ማሳወቂያዎችን መፈተሽ እና ማግኘት ይችላሉ።
  1. በማንኛውም አሳሽ ውስጥ YouTube ይክፈቱ። 
  2. ማሳወቂያዎችን ለመፈተሽ በገፁ አናት ላይ የማሳወቂያ ደወሉ   ላይ ጠቅ ያድርጉ።
  3. ቪድዮውን ወይም አስተያየቱን ለመመልከት የሚፈልጉትን ማሳወቂያ ይምረጡ። 
እንዲሁም ከኮምፒውተርዎ የገቢ መልዕክት ሳጥን ላይ ማሳወቂያዎችን ማስተዳደር ይችላሉ።
  1. ከማሳወቂያው አጠገብ ተጨማሪ '' ላይ ጠቅ ያድርጉ።
  2. ይህን ማሳወቂያ ደብቅ፣ ከ<የሰርጥ ስም> ሁሉንም አጥፋ፣ ወይም ሁሉንም [የማሳወቂያ ዓይነት] ዝማኔዎችን አጥፋ ላይ ጠቅ ያድርጉ።

የሚፈልጉትን የማሳወቂያዎች ዓይነት ይምረጡ

ምን ዓይነት ማሳወቂያዎችን ከYouTube እንደሚያገኙ እና እንዴት እንደሚያገኟቸው መቆጣጠር ይችላሉ።

  1. ወደ YouTube በመለያ ይግቡ።
  2. ወደ የእርስዎ የማሳወቂያ ቅንብሮች ይሂዱ።
  3. በገፁ ላይ ያሉ የተለያዩ ክፍሎች ስር የሚፈልጓቸውን ማሳወቂያዎች ይምረጡ፦
    • የደንበኝነት ምዝገባዎች፦ እርስዎ ለደንበኝነት በተመዘገቡባቸው ሰርጦች ላይ ስላለ እንቅስቃሴ ይነግሩዎታል።
    • የሚመከሩ ቪድዮዎች፦ በሚመለከቱት መሠረት ሊወዷቸው የሚችሏቸውን ቪድዮዎች ይነግሩዎታል። ቪድዮዎች እርስዎ ለደንበኝነት ከተመዘገቡባቸው ሰርጦች አይደሉም።
    • በእኔ ሰርጥ ላይ ያለ እንቅስቃሴ፦ በእርስዎ ሰርጥ ወይም ቪድዮዎች ላይ ስላሉ አስተያየቶች እና ሌላ እንቅስቃሴ ይነግርዎታል።
    • በእኔ አስተያየቶች ላይ ያለ እንቅስቃሴ፦ የእርስዎ አስተያየቶች መውደዶችን፣ ፒን መደረጎችን ወይም <3ዎችን ሲያገኙ ይነግርዎታል።
    • ለአስተያየቶቼ የተሰጡ ምላሾች፦ የሆነ ሰው ለእርስዎ አስተያየቶች ምላሽ ሲሰጡ ዝማኔዎችን ያግኙ።
    • መጠቀሶች፦ ሌሎች ሰርጥዎን ሲጠቅሱ ይነግሩዎታል።
    • የተጋራ ይዘት፦ የእርስዎ ይዘት በሌሎች ሰርጦች ላይ ሲጋራ አልፎ አልፎ ይነግርዎታል።
  4. «የኢሜይል ማሳወቂያዎች» ከሚለው ስር ምን ዓይነት የኢሜይል ማሳወቂያዎችን ማግኘት እንደሚፈልጉ ይምረጡ።

በማስታወቂያዎች እና የደንበኝነት ምዝገባዎች ምግብ መካከል ያለ ልዩነት

በሁለቱም በሞባይል እና ኮምፒውተር ላይ የሚገኘው የደንበኝነት ምዝገባዎች ምግብ ከእርስዎ የደንበኝነት ምዝገባዎች ማናቸውም በቅርብ ጊዜ የተሰቀሉ ቪድዮዎችን ያሳያል።

ማሳወቂያዎች አዳዲስ ቪድዮዎች ሲኖሩ ለእርስዎ መንገር፣ ከእርስዎ የደንበኝነት ምዝገባዎች ላይ ዝማኔዎችን ማጋራት እና እንዲሁም ሊወዱት ስለሚችሉት ይዘት ለእርስዎ መንገር ይችላል። ኢሜይሎችን፣ ግላዊነት የተላበሱ ማሳወቂያዎችን በሞባይል ላይ ወይም የገቢ መልዕክት ሳጥን ማሳወቂያዎችን በእርስዎ ኮምፒውተር ወይም ተንቀሳቃሽ መሣሪያ ላይ እንልካለን። ለአንድ ሰርጥ በደንበኝነት ሲመዘገቡ የእንቅስቃሴ ድምቀቶች ያሏቸው ግላዊነት የተላበሱ ማሳወቂያዎችን በራስ-ሰር ያገኛሉ።

የገቢ መልዕክት ሳጥን ማሳወቂያዎች በጊዜ ይደራጃሉ፣ ይበልጥ አዳዲስ ማሳወቂያዎች ከላይ ይሆናሉ። አንዳንድ ማሳወቂያዎች ከአዳዲሶቹ በላይ «አስፈላጊ» በሚለው ክፍል ውስጥ ተለይተው ሊቀርቡ ይችላሉ፣ ይህም ለእርስዎ ይበልጥ አግባብነት ሊኖራቸው ይችላሉ ብለን የምናስባቸውን ማሳወቂያዎች ለይቶ ያቀርባል። የአስፈላጊ ማሳወቂያዎች ምሳሌ ለእርስዎ አስተያየት የተሰጠ መልስን ወይም ሰዎች የእርስዎን ቪድዮዎች ሲያጋሩ ሊያካትት ይችላል።

በደንበኝነት ከተመዘገቡበት ሰርጥ ሁሉንም ማሳወቂያዎች ለማግኘት፣ የማሳወቂያ ደወሉን  መታ ያድርጉ። ሁሉንም ማሳወቂያዎች እንደመረጡ ለማመልከት ደወሉ  ወደሚጮህ ደወል አይነት ይቀየራል።

የሰርጡ ታዳሚ ለልጆች እንደተዘጋጀ ተደርጎ ከተቀናበረ ማሳወቂያዎችን አያገኙም። የማሳወቂያ ደወሉ ወደ ማሳወቂያዎች አይኖሩም«» ወደሚለውም ይቀናበራል። ይህን ቅንብር መለወጥ አይችሉም።

የሰርጥ ባለቤት ማሳወቂያዎች

ለደንበኝነት ተመዝጋቢዎች የሚደርሱ የቪድዮ ማሳወቂያዎች የቪድዮ ደረጃ ቅንብሮችን ለመለወጥ፦
  1. ወደ YouTube ስቱዲዮ እና በመቀጠል ይዘት «» እና በመቀጠል ቪድዮዎች ያስሱ።
  2. ያልተዘረዘረውን ቪድዮ እና በመቀጠል ዝርዝሮች «» እና በመቀጠል ተጨማሪ አሳይ የሚለውን ይምረጡ።
  3. ወደ ታች ወደ ፈቃዶች ያሸብልሉ።
  4. ለዛ የተወሰነ ቪድዮ ወደ የደንበኝነት ምዝገባዎች ምግብ አትም እና የደንበኝነት ተመዝጋቢዎችን አሳውቅ የሚለውን ይምረጡ ወይም ያስወግዱ።

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
14689806962974524318
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
59
false
false