መተግበሪያዎን ለግምገማ ያዘጋጁት

መተግበሪያ ይዘት ገጽ መተግበሪያዎ ለታለሙለት ተጠቃሚዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን፣ ለየGoogle Play ገንቢ የመርሐ-ግብር መመሪያዎች ተገዢ መሆኑን እና ሕጋዊ መስፈርቶችን ማሟላቱን ለማረጋገጥ የሚያስፈልገንን መረጃ እርስዎ የሚያቀርቡበት እና የሚያስተዳድሩበት ነው።

አጠቃላይ ዕይታ

የመተግበሪያ ይዘት ገጹ ስለመተግበሪያዎ ይዘት ያሳውቀናል። በዚህ ገጽ ላይ የመመሪያ መግለጫዎችን ማጠናቀቅ እና እንደ ለገምጋሚዎች ልዩ የመዳረሻ መመሪያዎችን ያለ ሌላ መረጃን ማቅረብ ይችላሉ። የእርስዎ መተግበሪያ የGoogle Play መመሪያዎችን የሚያከብር መሆኑን ለማረጋገጥ በመተግበሪያ ይዘት ገጹ ላይ ማድረግ የሚችሏቸው የሌሎች ነገሮች አንዳንድ ምሳሌዎች እነሆ፦ 

  • ሚስጥራዊነት ያለው የተጠቃሚ እና የመሣሪያ ውሂብን ለማጋራት የእርስዎን የግላዊነት መመሪያ ማከል። 
  • መተግበሪያዎ ማስታወቂያዎችን ይዞ እንደሆነ ያስታውቁ።
  • የተከለከሉ የመተግበሪያዎን ክፍሎች እንዴት መድረስ እንደሚቻል ላይ መመሪያዎችን ያቅርቡ እና ያስተዳድሩ
  • ስለመተግበሪያዎ ዒላማ ታዳሚ እና ይዘት ዝርዝሮችን ማቅረብ።
  • እንደ የኤስኤምኤስ/የጥሪ ምዝገባ ማስታወሻ ፈቃዶች ያሉ ማናቸውንም ከፍተኛ ስጋት ወይም አደገኛ ፈቃዶች እንዴት ለመጠቀም እንዳሰቡ ያብራሩ።
  • የይዘት ደረጃዎችን ከይፋዊ የደረጃዎች ባለሥልጣኖች ይቀበሉ።
  • ስለመተግበሪያዎ ግላዊነት እና የደህንነት ልምዶች ይንገሩን።

የመተግበሪያ ይዘት ገጽ ሁለት ትሮች አሉት፦ 

  • ትኩረት ያስፈልገዋል፦ የእርስዎን ትኩረት የሚሹ የመመሪያ መግለጫዎች እዚህ ይታያሉ። የGoogle Play መመሪያዎችን ለማክበር አግባብነት ካለው የጊዜ ገደብ በፊት መግለጫዎቹን ማጠናቀቅ አለብዎት።
  • እርምጃ የተወሰደባቸው፦ እርምጃ የወሰዱባቸው የመመሪያ መግለጫዎች እዚህ ይታያሉ። ማናቸውንም ችግሮች ካገኘን እናሳውቅዎታለን። የGoogle Play መመሪያዎችን ለማክበር በመደበኛነት ያቀረቡትን መረጃ መገምገም እና ወቅታዊ ሆኖ መቆየቱን ማረጋገጥ አለብዎት።

የመተግበሪያ መረጃ ያቅርቡ

የግላዊነት መመሪያ

የግላዊነት መመሪያን ወደ የእርስዎ መተግበሪያ መደብር ዝርዝር ማከል እርስዎ ምሥጢራዊነት ያለው የተጠቃሚ እና የመሣሪያ ውሂብን እንዴት እንደሚይዙ ላይ ግልጽነት ያለው አሠራን ለመስጠት ያግዛል።

የግላዊነት መመሪያው ከውስጠ-መተግበሪያ ይፋዊ ማውጫዎች ጋር የእርስዎ መተግበሪያ በአጠቃላይ እንዴት የተጠቃሚ ውሂብን እንደሚሰበስብ፣ እንደሚጠቀም እና እንደሚያጋራ ሁለገብ በሆነ መልኩ ማሳወቅ አለበት። ይህ የተጋራባቸውን የአካላት ዓይነቶችን ያጠቃልላል። ምን እንደሚያስፈልግ ምክር እንዲሰጠዎት የራስዎን የሕግ ወኪልዎን ማማከር አለብዎት።

  • ሚስጥራዊነት ያላቸው ፈቃዶችን ወይም ውሂብ ለሚጠይቁ መተግበሪያዎች (በዚህ ላይ እንደተብራራው የተጠቃሚ ውሂብ መመሪያዎች)፦ በእርስዎ የመተግበሪያ መደብር ዝርዝር ገጽ ላይ የግላዊነት መመሪያን ማገናኘት አለብዎት። የግላዊነት መመሪያዎ በገቢር ዩአርኤል ላይ የሚገኝ፣ መተግበሪያዎን የሚመለከት እና የተጠቃሚ ግላዊነትን የሚሸፍን መሆኑን ያረጋግጡ።
  • ልጆችን ለሚያነጣጥሩ መተግበሪያዎች፦ የአደገኛ ፈቃዶች ወይም የውሂብ መዳረሻ ቢኖረውም ባይኖረውም በመተግበሪያዎ የመደብር ዝርዝር ገጽ ላይ እና በመተግበሪያዎ ውስጥ ከግላዊነት መመሪያ ጋር ማገናኘት አለብዎት። የግላዊነት መመሪያዎ በገቢር ዩአርኤል ላይ የሚገኝ፣ መተግበሪያዎን የሚመለከት እና የተጠቃሚ ግላዊነትን የሚሸፍን መሆኑን ያረጋግጡ። ማንኛውም የግል ወይም አደገኛ የተጠቃሚ ውሂብን የማይደርሱ መተግበሪያዎች አንኳ አሁንም የግላዊነት መመሪያ ማስገባት እንዳለባቸው ልብ ይበሉ። 

የግላዊነት መመሪያ ያክሉ

  1. Play Consoleን ይክፈቱ እና ወደ የመተግበሪያ ይዘት ገጽ (መመሪያ > የመተግበሪያ ይዘት) ይሂዱ።
  2. በ«የግላዊነት መመሪያ» ስር ጀምርን ይምረጡ። 
    • ማስታወሻ፦ ከዚህ ቀደም የግላዊነት መመሪያ ካከሉና ለውጦችን ማድረግ ከፈለጉ ከጀምር ይልቅ አቀናብርን ያያሉ እና ይመርጣሉ።
  3. የግላዊነት መመሪያውን በመስመር ላይ የሚያስተናግደውን ዩአርኤል ያስገቡ።
  4. ለውጦችዎን ያስቀምጡ።

ማስታወቂያዎች 

መተግበሪያዎ ማስታወቂያዎችን የያዘ እንደሆነ ማወጅ አለብዎት። ይህ በሶስተኛ ወገን የማስታወቂያ ኤስዲኬዎች (የሶፍትዌር ግንባታ ጥቅል) በኩል የመጡ ማስታወቂያዎች፣ የማሳያ ማስታወቂያዎች፣ ቤተኛ ማስታወቂያዎች እና/ወይም የሰንደቅ ማስታወቂያዎች በኩል የሚደርሱ ማስታወቂያዎችን ያካትታል)። ማስታወቂያዎችን የያዙ መተግበሪያዎች በእነርሱ መደብር ዝርዝር ላይ የሚታይ የ«ማስታወቂያ ያካተተ» መለያ ይኖራቸዋል። ይህ መለያ ለሁሉም የPlay መደብር ተጠቃሚዎች የሚታይ ይሆናል።

ማስታወሻ፦ የ«ማስታወቂያዎችን ይዟል» መሰየሚያው አንድ መተግበሪያ እንደ የሚከፈልበት የምርት ምደባ ወይም የውስጠ-መተግበሪያ ግዢዎችን ወይም ማላቂያዎችን የማድረግ አቅርቦቶች ያለ ሌላ ዓይነት የንግድ ይዘት ያለው ነገር እንዳካተተ ወይም እንዳላካተተ ለመሸፈን የታሰበ አይደለም። መተግበሪያዎ የሚከፈልባቸው የምርት ምደባዎችን ካካተተ የአካባቢውን ህጎች እንደሚያከብሩ ያረጋግጡ።

የእርስዎ መተግበሪያ ማስታወቂያዎችን እንደያዘ ወይም እንዳልያዘ ያውጁ

  1. Play Consoleን ይክፈቱ እና ወደ የመተግበሪያ ይዘት ገጽ (መመሪያ > የመተግበሪያ ይዘት) ይሂዱ። 
  2. ከ«ማስታወቂያዎች» ስር ጀምርን ይምረጡ።
    • ማስታወሻ፦ ከዚህ ቀደም መተግበሪያዎ ማስታወቂያዎችን ይዞ እንደሆነ አውጀው ከነበረ እና ለውጦችን ማድረግ ከፈለጉ ጀምር ይልቅአቀናብርን ያያሉ እና ይመርጣሉ።
  3. የእርስዎ መተግበሪያ ተገዢ መሆኑን ለማረጋገት የማስታወቂያዎች መመሪያን ይገምግሙ እና ይህን ይምረጡ አዎ ወይም አይ
  4. ለውጦችዎን ያስቀምጡ።

ምሳሌዎች

ለ«ማስታወቂያዎች ይዟል» መሰየሚያው ዓላማ ማስታወቂያ ሲኖረዎት መቼ «አዎ» ብለው መመለስ እንዳለብዎ ጥቂት ምሳሌዎች እነሆ። ይህ ሙሉው ዝርዝር አይደለም፣ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ በጣም በተለመዱ ማስታወቂያዎች ላይ የተመሠረቱ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው።

  • ሰንደቅ እና የመሃል ክፍተት ማስታወቂያዎች፦ ሰንደቆችን እና/ወይም በማውረ ጊዜ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን ለማሳየት የእኔ መተግበሪያ ከማስታውቂያ ኤስዲኬ ጋር ይዋሃዳል። በራሴ ምርቶች ወይም መተግበሪያዎች ገቢ ለመፍጠር እና/ወይም ለማስተዋወቅ የማስታወቂያ ቅርጸቶችን እጠቀማለሁ።
  • ቤተኛ ማስታወቂያዎች፦ የእኔ መተግበሪያ ከሌሎች ይዘቶች ሊለዩ የማይችሉ ቤተኛ ማስታወቂያዎችን ያካትታል (ለምሳሌ፦ ስፖንሰር ያላቸው ዘገባች፣ በምግብ ውስጥ ያሉ ማስታወቂያዎች፣ ወዘተ)።
  • የቤት ማስታወቂያዎች፦ የእኔ መተግበሪያ ሌሎች መተግበሪያዎቼን ለማስተዋወቅ ትንሽ የማስታወቂያ ሰንደቅ፣ የመሃል ማስታወቂያ፣ የማስተወቂያ ግርግዳ እና/ወይም ምግብር ያቀርባል።

ሌሎች መተግበሪያዎችዎን በሚከተሉት መንገዶች እርስ-በእርስ ካስተዋወቁ ብቻ ነው ለ«ማስታወቂያዎች ይዟል» መሰየሚያ ዓላማ ማስታወቂያዎች አለዎት ለሚለው «አይ» ብለው መመለስ አለብዎት፦

  • መተግበሪያው በዋና ምናሌ ውስጥ ተጠቃሚውን ወደ ሌሎች መተግበሪያዎችዎ የሚመራ የተጨማሪ መተግበሪያዎች* ክፍልን ያሳያል
  • የተጨማሪ መተግበሪያዎች* አማራጩ በጨዋታ ዘዴው ላይ ጣልቃ አይገባም
  • የተጨማሪ መተግበሪያዎች* አማራጩ በጨዋታ ዘዴው ላይ ራሱን በመክተት ተጠቃሚውን አያደናግርም

*ተቀባይነት ያላቸው የተጨማሪ መተግበሪያዎች ምትኮች እነዚህን ያካትታሉ ተጨማሪ ጨዋታዎችተጨማሪ የሚታሰስ አለሙሉ ስሪትተጨማሪስለ እኛ፣ ወይም የእርስዎ የመተግበሪያ አዶ።

ተጨማሪ ክትትል

በመተግበሪያዎችዎ ውስጥ ማስታወቂያ መገኘቱን በትክክል የመግለጽ ሃላፊነት የእርስዎ ሲሆን፣ አግባብ ያለው ከሆነ Google ይህንን በማንኛውም ጊዜ አረጋግጦ የ«ማስታወቂያዎች ይዟል» መሰየሚያውን ሊያሳይ ይችላል።

መተግበሪያዎ በስርዓታችን ልክ ባልሆነ መልኩ ስያሜ እንደተሰጠው ካሰቡ ለእገዛ የድጋፍ ቡድናችንን ያነጋግሩ

ማስፈጸም

በእርስዎ መተግበሪያ(ዎች) ወስጥ የማስታወቂያዎች መገኘትን በተመለከተ አሳስተው ካቀረቡ እንደ Google Play መመሪያዎች ጥሰት ተደርጎ ይቆጠራል፣ እና የእርስዎ መተግበሪያ(ዎች) መታገድን ሊያስከትል ይችላል።

የመተግበሪያ መዳረሻ

ሙሉው መተግበሪያዎ ወይም የመተግበሪያዎ ክፍሎች በመግቢያ ማስረጃዎች፣ በመለያ መግቢያ ዝርዝሮች፣ አባልነቶች፣ አካባቢ ወይም ሌሎች የማረጋገጫ ዓይነቶች ላይ ተመስርተው የተገደቡ ከሆኑ የመተግበሪያዎን መዳረሻ ለማንቃት ሁሉንም አስፈላጊ ዝርዝሮችን ማቅረብ አለብዎት።

ለመተግበሪያ መዳረሻ መመሪያዎችን ያክሉ

  1. Play Consoleን ይክፈቱ እና ወደ የመተግበሪያ ይዘት ገጽ (መመሪያ > የመተግበሪያ ይዘት) ይሂዱ።
  2. ከ«የመተግበሪያ መዳረሻ» ስር ጀምርን ይምረጡ።
    • ማስታወሻ፦ ከዚህ ቀደም ለመተግበሪያ መዳረሻ መመሪያዎችን ካከሉ እና ለውጦችን ማድረግ ከፈለጉ ከጀምር ይልቅ አቀናብርን ያያሉ።
  3. + አዲስ መመሪያዎችን አክል ላይ ጠቅ ያድርጉ እና የእርስዎን መዳረሻ ዝርዝሮች ይስጡ።
    • ማስታወሻ፦ እንደ የአንድ ጊዜ ብቻ የይለፍ ቃል፣ ባለብዙ ደረጃ ማረጋገጫ ወይም ከሁለት መስኮች በላይ ያላቸው መግቢያዎች ያሉ ስለመግቢያ ስልቶችዎ ልዩ የሆነ ማንኛውም ነገር ካለ ለእኛ ለማሳወቅ የ«ሌሎች ማናቸውም መመሪያዎች» መስክን ይጠቀሙ።
  4. ለውጦችዎን ያስቀምጡ።

ዝማኔዎ ውድቅ ከተደረገ ወይም መተግበሪያዎ ከተወገደ እባክዎ መተግበሪያዎን ለግምገማ እንደገና ለማስገባት ከታች ያሉትን መመሪያዎች ይከተሉ።  ከመመሪያው ድጋፍ ቡድን ምላሽ ሳያገኙ ወይም ሳይጠብቁ እነዚህን ደረጃዎች ማጠናቀቅ ይችላሉ።

  1. Play Consoleን ይክፈቱ እና ወደ የመተግበሪያ መዳረሻ ገጽ ይሂዱ። 
  2. የእርስዎን የመተግበሪያ መዳረሻ መረጃ ያዘምኑ እና አስቀምጥን ጠቅ ያድርጉ።
  3. የዝማኔ ሁኔታዎ «ለግምገማ ለመላክ ዝግጁ» ከሆነ ወይም የህትመት አጠቃላይ እይታ ገጽዎ «ለግምገማ ለመላክ ዝግጁ የሆኑ ለውጦች» ክፍል ካለው ከዚያ ለውጦችዎን ለግምገማ ለማስገባት ከህትመት አጠቃላይ እይታ ገጽ ለግምገማ ላክ የሚለውን ጠቅ ማድረግ አለብዎት።

ማስታወሻዎች፦ 

  • እስከ አምስት የመመሪያዎች ስብስቦች ድረስ ማከል ይችላሉ።
  • የመግቢያ ማስረጃዎ አሃዛዊ ወይም ፊደላት ካልሆኑ (ለምሳሌ፣ QR ኮድ ወይም የአሞሌ ኮድ) አይለወጤ ዩአርኤል ያመንጩና ወደ Play Console ይስቀሉት።
  • የእርስዎ መተግበሪያ በተለምዶ ባለ2-ደረጃ ማረጋገጫ ኮድ ወይም የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃል የሚያስፈልገው ከሆነ የአገልግሎት ጊዜያቸው የማያበቃ በድጋሚ ስራ ላይ ሊውሉ የሚችሉ የመግቢያ ማስረጃዎችን ያቅርቡልን።
  • የእርስዎ መተግበሪያ በመደበኝነት በአካባቢ ላይ የተመሰረተ የይለፍ ቃል (ለምሳሌ፣ ጂኦ-ጌት) የሚጠቀም ከሆነ የተጠቃሚ አካባቢ ምንም ይሁን ምን የሚሰራ የመግቢያ ማስረጃዎን ያቅርቡ (ለምሳሌ «ዋና» የመግቢያ ማስረጃዎች)።
  • የመግባት ማስረጃዎ በተለምዶ እንግሊዝኛ ባልሆኑ ቋንቋዎች ከሆኑ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ሰሪት የሆኑ ሁሉንም አስፈላጊ የሆኑ የመግቢያ ማስረጃዎች በPlay Console በኩል ያቅርቡ።

ዒላማ ታዳሚ እና ይዘት

የእርስዎን መተግበሪያ ዒላማ የዕድሜ ቡድን ማወጅ አለብዎት። ማናቸውም በዒላማ ታዳሚያቸው ውስጥ ሕፃናትን የሚያካትቱ መተግበሪያዎች በGoogle Play ተገዢ መሆን አለባቸው የቤተሰብ መመሪያ መስፈርቶች

ስለ የእርስዎ መተግበሪያ ትክክለኛ መረጃ መስጠት አስፈላጊ ነው። እርስዎ በሚመርጡት የታዳሚ ምርጫዎች ላይ በመመስረት የእርስዎ መተግበሪያ ለተጨማሪ የGoogle Play መመሪያዎች ተገዢ ሊሆን ይችላል። ራስዎን ከእነዚህ መመሪያዎች ጋር ማላመድ እና እንዴት የመተግበሪያው ይዘት ገጽ የ«ዒላማ ታዳሚ እና ይዘት» ክፍልን እንደሚሞሉ ማወቅ ይችላሉ ። 

ስለሂደቱ ተጨማሪ ማወቅ እና መስተጋብራዊውን የማረጋገጫ ዝርዝር በዚህ ላይ መረዳት ይችላሉ የመተግበሪያ ስኬት አካዳሚ

የፈቃዶች ማወጂያ ቅጽ

የፈቃድ ጥያቄዎች የእርስዎን Android መተግበሪያ ቅርቅብ ካከሉ በኋላ በሚኖረው የልቀት ሂደት ላይ ይገመገማሉ። የእርስዎ መተግበሪያ ከፍተኛ ስጋት ወይም ሚስጥራዊነት ያላቸው ፈቃዶች (ለምሳሌ፦ የኤስኤምኤስ ወይም የጥሪ ምዝገባ ማስታወሻ) እርስዎ የፈቃዶች ማወጂያ ቅጹን መሙላት እና ከGoogle Play ፈቃድ እንዲያገኙ ሊፈለግብዎት ይችላል።

ስለሂደቱ እና እንዴት የፈቃዶች ማወጂያ ቅጽን መሙላት እንደሚችሉ በመተግበሪያ ይዘት ገጽ ላይ ማወቅ ይችላሉ።

የይዘት ደረጃዎች

የሚታወቁ እና ለአካባቢው ተገቢነት ያላቸው ደረጃዎችን ለእርስዎ ተጠቃሚዎች ማሳወቅ እና ለይዘትዎ ትክክለኛዎቹን ታዳሚዎች በማነጣጠር የመተግበሪያ ተሳትፎ እንዲሻሻል ማገዝ ይችላሉ።

የእርስዎን መተግበሪያዎች እንደ «ደረጃ ያልተሰጣቸው» ተብለው እንዳይዘረዘሩ ለመከላከል ወደ Play Console ይግቡና በተቻለ ፍጥነት ለእያንዳንዱ መተግበሪያዎችዎ መጠይቆችን ይሙሉ። «ደረጃ ያልተሰጣቸው» መተግበሪያዎች ከGoogle Play ላይ ሊወገዱ ይችላሉ።

ስለ የተወሰኑ የደረጃዎች ባለሥልጣን እና መግለጫዎች የበለጠ ለማወቅ፣ እና ይህን የመተግበሪያ ይዘት ገጹን ክፍል እንዴት እንደሚያጠናቅቁ መመሪያዎችን ለማግኘት ወደ ለመተግበሪያዎች እና ጨዋታዎች የይዘት ደረጃዎች አሰጣጥ ይሂዱ።

የኮቪድ-19 ሰዎች ንክኪን መከታተል እና የሁኔታ መተግበሪያዎች

መተግበሪያዎ የኮቪድ-19 የሰዎች ንክኪን መከታተል እና/ወይም የኮቪድ-19 የሁኔታ ተግባራዊነት የያዘ መሆኑን ለእኛ ማሳወቅ አለብዎት። 

ይህንን ክፍል ከማጠናቀቅዎ በፊት ለኮሮና ቫይረስ በሽታ 2019 (ኮቪድ-19) መተግበሪያዎች መስፈርቶችን ያንብቡ።

የኮቪድ-19 የሰዎች ንክኪን መከታተል እና የሁኔታ መተግበሪያዎችን መግለጫ ለማጠናቀቅ፦

  1. Play Consoleን ይክፈቱ እና ወደ የመተግበሪያ ይዘት ገጽ (መመሪያ > የመተግበሪያ ይዘት) ይሂዱ።
  2. ከ«ኮቪድ-19 የሰዎች ንክኪን መከታተል እና የሁኔታ መተግበሪያዎች» ስር ጀምርን ይምረጡ።
    • ማስታወሻ፦ ከዚህ በፊት መግለጫውን ካጠናቀቁ እና ለውጦችን ማድረግ ከፈለጉ ከጀምር ይልቅ አቀናብርን ያያሉ እና ይመርጣሉ።
  3. ለመተግበሪያዎ የሚመለከተውን ሁሉንም መግለጫዎች ይምረጡ።
  4. ለውጦችዎን ያስቀምጡ

መተግበሪያዎ የኮቪድ-19 የሰዎች ንክኪን መከታተል ወይም የሁኔታ ተግባራዊነት የያዘ ከሆነ፣ ለGoogle Play መተግበሪያ ግምገማ ቡድን ቀደም ያለ ማሳሰቢያ መስጠት አለብዎት።

ተዛማጅ ይዘት

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?

ተጨማሪ እገዛ ያስፈልግሃል?

እነዚህን ቀጣይ እርምጃዎች ይሞክሩ፦

ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
6713645850587392514
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
92637
false
false