መተግበሪያዎን ያስተርጉሙት እና አካባቢያዊ ያድርጉት

በዓለም ዙሪያ ላሉ ተጠቃሚዎችዎ አካባቢያዊ የተደረገ ተሞክሮን ለማቅረብ ለእርስዎ የመተግበሪያ መደብር ዝርዝር ገጽ፣ የኤፒኬ ፋይሎች፣ ሕብረቁምፊዎች ወይም የውስጠ-መተግበሪያ ምርቶች ትርጉሞችን ማከል ይችላሉ። ራስዎ ማከል ወይም በPlay Console በኩል ሊገዟቸው እና ሊተገብሯቸው ይችላሉ። እንዲሁም መተግበሪያዎን ወደ የተመረጡ ቋንቋዎች ለመተርጎም የPlay Consoleን ነጻ የማሽን ትርጉም አገልግሎት መጠቀም ይችላሉ።

ለመተግበሪያዎ ትርጉሞችን ያክሉ

የአንድ ተጠቃሚ የቋንቋ ምርጫ እርስዎ ካከሏቸው የትርጉም ቋንቋዎች ጋር የሚዛመድ ከሆነ የተተረጎመው የመተግበሪያዎን ስሪት ያያሉ። ለመደብር ዝርዝር ገጾችዎ አካባቢያዊ የተደረጉ ግራፊካዊ እሴቶችን ማከል ይችላሉ።

አካባቢያዊ የተደረጉ እሴቶች የሌላቸው የጽሑፍ ትርጉሞችን ካከሉ የእርስዎ መተግበሪያ ግራፊክ እሴቶች በነባሪው ቋንቋ ይታያሉ።

ማስታወሻ፦ የመደብር ዝርዝርን አካባቢያዊ ማድረግ Play Console እርስዎ የተለያዩ ተሞክሮዎችን በተለያዩ አካባቢዎች ውስጥ ላሉ ተጠቃሚዎች እንዲያደርሱ ማገዝ ከሚችልባቸው ሁለት መንገዶች ውስጥ አንዱ ነው። የተለያዩ የመደብር ዝርዝሮችን በአገር/ክልል (ከቋንቋ ጋር ሲነጻጸር) ለማድረስ ብጁ የመደብር ዝርዝሮችን እንዲፈጥሩ እንመክራለን።

የራስዎን የጽሁፍ ትርጉሞች እና አካባቢያዊ ግራፊክ እሴቶችን ያክሉ
  1. Play Consoleን ይክፈቱ እና ወደ የትርጉም አገልግሎት ገጽ (አሳድግ > የመደብር ተገኝነት > የትርጉም አገልግሎት) ይሂዱ።
  2. በገጹ አናት ላይ ትርጉሞችን አክልን ይምረጡ እና በተቆልቋዩ ምናሌው ላይ የራስዎን የትርጉም ጽሁፍ ያክሉን ጠቅ ያድርጉ።
    • ማስታወሻ፦ ከዚህ ቀደም አስቀድመው ትርጉሞችን አክለው ከሆነ በተቆልቋይ ምናሌው ላይ ትርጉሞችን አስተዳድር እና የራስዎን የትርጉም ጽሑፍ ያስተዳድሩን ያያሉ።
  3. በ«ቋንቋዎችን አክል ወይም አስወግድ» ስር ወደ ዝርዝሩ ለማከል የሚፈልጓቸውን ቋንቋዎች ይምረጡ። 
  4. ተግብርን ጠቅ ያድርጉ።
  5. ለውጦችዎን ያስቀምጡ።
የሚገኙ ቋንቋዎች ዝርዝርን ይመልከቱ

የሚያክሉት የራስዎን ትርጉሞች ከሆነ ይህን በሚከተሉት ቋንቋዎች ውስጥ ማድረግ ይችላሉ፦

  • አፍሪካንስ – af
  • አልባኒያኛ – sq
  • አማርኛ – am
  • አረብኛ – ar
  • አርሜንኛ – hy-AM
  • አዘርባይጃንኛ – az-AZ
  • ባንግላ – bn-BD
  • ባስክ – eu-ES
  • ቤላሩስኛ – be
  • ቡልጋሪያኛ – bg
  • ቡርማኛ – my-MM
  • ካታላን – ca
  • ቻይንኛ (ሆንግ ኮንግ) – zh-HK
  • ቻይንኛ (ቀላል) – zh-CN
  • ቻይንኛ (ባህላዊ) – zh-TW
  • ክሮሽያንኛ – hr
  • ቼክኛ – cs-CZ
  • ዳኒሽ – da-DK
  • ደች – nl-NL
  • እንግሊዝኛ – en-IN
  • እንግሊዝኛ – en-SG
  • እንግሊዝኛ – en-ZA
  • እንግሊዝኛ (አውስትራሊያ) – en-AU
  • እንግሊዝኛ (ካናዳ) – en-CA
  • እንግሊዝኛ (ዩናይትድ ኪንግደም) – en-GB
  • እንግሊዝኛ (አሜሪካ) – en-US
  • ኢስቶኒያኛ – et
  • ፊሊፒኖ – fil
  • ፊንላንድኛ – fi-FI
  • ፈረንሳይኛ (ካናዳ) – fr-CA
  • ፈረንሳይኛ (ፈረንሳይ) – fr-FR
  • ጋሊሲያኛ – gl-ES
  • ጆርጂያኛ – ka-GE
  • ጀርመንኛ – de-DE
  • ግሪክኛ – el-GR
  • ጉጅራቲ – gu
  • ዕብራይስጥ – iw-IL
  • ሂንዲ – hi-IN
  • ሀንጋሪኛ – hu-HU
  • አይስላንድኛ – is-IS
  • ኢንዶኔዥያኛ – id
  • ጣልያንኛ – it-IT
  • ጃፓንኛ – ja-JP
  • ካናዳ – kn-IN
  • ካዛክኛ – kk
  • ክመርኛ – km-KH
  • ኮሪያኛ – ko-KR
  • ኪርጊዝኛ – ky-KG
  • ላኦኛ – lo-LA
  • ላቲቪያኛ – lv
  • ሊቱዌኒያኛ – lt
  • መቄዶኒያኛ – mk-MK
  • ማላይኛ – ms
  • ማላይኛ (ማሌዥያ) – ms-MY
  • ማላያላም – ml-IN
  • ማራቲ – mr-IN
  • ሞንጎሊያኛ – mn-MN
  • ኔፓልኛ – ne-NP
  • ኖርዌይኛ – no-NO
  • ፋርስኛ – fa
  • ፋርስኛ – fa-AE
  • ፋርስኛ – fa-AF
  • ፋርስኛ – fa-IR
  • ፓላንድኛ – pl-PL
  • ፖርቹጋልኛ (ብራዚል) – pt-BR
  • ፖርቹጋልኛ (ፖርቹጋል) – pt-PT
  • ፑንጃቢኛ – pa
  • ሮማኒያኛ – ro
  • ሮማንሽ – rm
  • ሩሲያኛ – ru-RU
  • ሰርቢያኛ – sr
  • ሲንሃላኛ – si-LK
  • ስሎቫክኛ – sk
  • ስሎቬኒያኛ – sl
  • ስፓኒሽ (ላቲን አሜሪካ) – es-419
  • ስፓኒሽ (ስፔን) – es-ES
  • ስፓኒሽ (አሜሪካ) – es-US
  • ስዋሃሊ – sw
  • ስዊድንኛ – sv-SE
  • ታሚል – ta-IN
  • ተለጉ – te-IN
  • ታይ – th
  • ቱርክኛ – tr-TR
  • ዩክሬንኛ – uk
  • ኡርዱኛ – ur
  • ቪየትናምኛ – vi
  • ዙሉ – zu
የሰው ትርጉሞችን ይግዙ እና ይተግብሩ

ትርጉሞችን ይግዙ

የእኛን የሚከፈልበት የሰው ትርጉም አገልግሎት በመጠቀም ለእርስዎ የመተግበሪያ ሕብረቁምፊዎች፣ የመደብር ዝርዝር እና የውስጠ-መተግበሪያ ምርቶች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ትርጉሞችን ከባለሙያ ሦስተኛ ወገን አቅራቢ ማዘዝ ይችላሉ። ማዘዝ ደቂቃዎች ይወስዳል፣ ወጪ እስከ በቃል USD 0.07 ድረስ አነስተኛ ነው እና ትርጉሞች በሰባት ቀናት ውስጥ ይጠናቀቃሉ።

ማስታወሻዎች፦

  • ትርጉሞቹን ለማቀናበር እና ማንኛውንም አይነት የድጋፍ ችግሮችን ለመፍታት ከአገልግሎት አቅራቢው ጋር በቀጥታ አብረው ይሠራሉ።
  • ትርጉሞች ለሁሉም የምንጭ እና የዒላማ ቋንቋዎች ጥምሮች አይገኝም።

በPlay Console በኩል ትርጉሞችን ለመግዛት፦

  1. Play Consoleን ይክፈቱ እና ወደ የትርጉም አገልግሎት ገጽ (አሳድግ > የመደብር ተገኝነት > የትርጉም አገልግሎት) ይሂዱ።
  2. ትርጉሞችን ፍጠርን ጠቅ ያድርጉ።
  3. የሚከፈለበት የሰው ትርጉምን እንደ የእርስዎ የትርጉም ዓይነት ይምረጡ።
  4. በ «ቋንቋዎችን ይምረጡ» ክፍል ውስጥ፦ 
    • በመጀመሪያው ጽሁፍዎ ውስጥ ሥራ ላይ የዋለውን ምንጭ ቋንቋ ይግለጹ።
    • የትርጉም ዒላማ ቋንቋዎችዎን ይምረጡ። 
    • የእርስዎን ቋንቋዎች መርጠው ሲጨርሱ ቀጣይን ጠቅ ያድርጉ።
  5. በ«ምን እንደሚተረጎም ይምረጡ» ክፍል ውስጥ ለማስተርጎም የሚፈልጓቸውን ንጥሎች ይምረጡ፦
    • የመደብር ዝርዝር፦ በGoogle Play ላይ ለተጠቃሚዎች እንደሚታየው የመተግበሪያዎን ርዕስ፣ አጭር መግለጫ እና ሙሉ መግለጫ ያቅርቡ።
    • የመተግበሪያ ሕብረቁምፊዎች፦ ከመተግበሪያዎ የተገኘን ጽሁፍ እንደ የXML ወይም የCSV ፋይል ያክሉ።
    • የውስጠ-መተግበሪያ ምርቶች፦ የውስጠ-መተግበሪያ ምርቶችዎን ርዕስ እና መግለጫ ያቅርቡ።
    • ተጨማሪ መረጃ፦ ቅጽበታዊ ገጽ ዕይታዎችን ወይም እንደ የGIF፣ JPEG፣ PNG ወይም ZIP ፋይል ያለ ሌላ ሰነዳ ያክሉ። ቅጽበታዊ ገጽ እይታን ማከል ጽሑፉ በመተግበሪያዎ ላይ እንዴት ሆኖ እንደሚታይ ለቋንቋ ባለሙያዎች አውድ ይሰጣቸዋል።
    • የቀዳሚ ትዕዛዞች የተተረጎሙ ሕብረቁምፊዎችን ዳግም ይጠቀሙባቸው፦ ገንዘብ ለመቆጠብ አስቀድመው የተተረጎሙ ሐብረቁምፊዎችን ዳግም ለመጠቀም ሳጥኑ ላይ ምልክት ያድርጉ። ለአዲስ ትርጉሞች ብቻ ነው እንዲከፍሉ የሚደረጉት፣ እና ትዕዛዝዎን ከመስጠትዎ በፊት ጠቅላላውን ዋጋ ያያሉ።
    • ለማስተርጎም የሚፈልጉትን ነገር መርጠው ሲጨርሱ ትዕዛዝን ገምግምን ጠቅ ያድርጉ።

      ማስታወሻዎች፦ 
    • እየመረጡ ሳለ የተገመተው ዋጋ በገጹ ላይኛው ክፍል በስተቀኝ ላይ እየተዘመነ ይሄዳል። የቋንቋዎቹ፣ የቃል ዋጋ እና የጠቅላላው ግምት ትንታኔ ለማግኘት ዝርዝሮችን ይመልከቱን ጠቅ ማድረግ ይችላሉ። 
    • የሌሎች ትርጉም አቅራቢዎችን እና የዋጋዎቻቸውን ዝርዝር ለማግኘት ሌሎች አቅራቢዎችን ይመልከቱን ጠቅ ማድረግ ይችላሉ።
       
  6. በ«ይገምግሙ እና ይክፈሉ» ክፍል ውስጥ፦ 
    • የትርጉም ትዕዛዝ ማጠቃለያዎን ይገምግሙ እና የማይፈልጓቸውን ማናቸውም ንጥሎችን ያስወግዱ። 
    • የሚጠበቀው የማጠናቀቂያ ቀንዎን ያስተውሉት።
    • ካለዎት የደረሰኝ ኮድ ያስገቡ።
  7. ትዕዛዝዎን ለማጠናቀቅ አረጋግጥ እና ክፈልን ጠቅ ያድርጉ። የክፍያ ማረጋገጫ ኢሜይል ይደርሰዎታል፣ እና ትርጉሞችዎ ሲጠናቀቁ ሌላ ኢሜይል ይደርሰዎታል።

ትርጉሞችን ይተግብሩ

የእርስዎ ትርጉሞች ከተጠናቀቁ በኋላ የእርስዎን ትርጉሞች እንዴት እንደሚተገብሯቸው እነሆ፦

  1. Play Consoleን ይክፈቱ እና ወደ የትርጉም አገልግሎት ገጽ (አሳድግ > የመደብር ተገኝነት > የትርጉም አገልግሎት) ይሂዱ።
  2. በሠንጠረዡ ላይ ሊተገብሩት ለሚፈልጉት ቋንቋ ረድፉን ይምረጡ። 
  3. የትርጉም ፋይልዎን እርስዎ ጋር ለማስቀመጥ አውርድን ጠቅ ያድርጉ።
  4. ለመተግበር ከሚፈልጉት ቋንቋ ቀጥሎ ተግብርን ጠቅ ያድርጉ።

አንዴ ለመተግበሪያዎ ሕብረቁምፊዎች ትርጉሞችን ካከሉ በኋላ የተተረጎመው የኤፒኬ ፋይል ወደ Google Play መስቀል ይችላሉ። የአንድ ተጠቃሚ የቋንቋ ምርጫ እርስዎ ካከሏቸው የትርጉም ቋንቋዎች ጋር የሚዛመድ ከሆነ የተተረጎመውን ስሪት ያያሉ።

የPlay Consoleን ነጻ የማሽን ትርጉም አገልግሎት ይጠቀሙ

የእኛን ነጻ የማሽን ትርጉም አገልግሎት በመጠቀም፣ ለእርስዎ የመተግበሪያ ሕብረቁምፊዎች፣ የመደብር ዝርዝር እና የውስጠ-መተግበሪያ ምርቶች ቅጽበታዊ፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የማሽን ትርጉሞችን ማዘዝ ይችላሉ። የማሽን ትርጉሞችን መጠቀም የመተግበሪያዎን ዓለም አቀፍ ተጠቃሚዎች ያለምንም ወጪ የተሻለ ለማገልገል ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ትርጉሞችን በፍጥነት ለማከል አሪፍ መንገድ ነው።

 የሚከተሉት ቋንቋዎች ይገኛሉ (ወደፊት ተጨማሪ ቋንቋዎችን ለማከል እየሰራን ነው)፦

  • ቻይንኛ (ቀላል) – zh-CN
  • ፈረንሳይኛ (ፈረንሳይ) – fr-FR
  • ጀርመንኛ – de-DE
  • ኢንዶኔዢያኛ – id
  • ጃፓንኛ – ja-JP
  • ፖርቹጋልኛ (ብራዚል) – pt-BR
  • ስፓኒሽ (ስፔን) – es-ES

አስፈላጊ፦ እነዚህ የማሽን ትርጉሞች እንደመሆናቸው በሰዎች የተገመገሙ ወይም የጸደቁ አይደሉም።

በPlay Console ውስጥ ነጻ የማሽን ትርጉሞችን ለማከል፦

  1. Play Consoleን ይክፈቱ እና ወደ የትርጉም አገልግሎት ገጽ (አሳድግ > የመደብር ተገኝነት > የትርጉም አገልግሎት) ይሂዱ።
  2. ትርጉሞችን ፍጠርን ጠቅ ያድርጉ።
  3. ነጻ የማሽን ትርጉምን እንደ የእርስዎ የትርጉም ዓይነት ይምረጡ።
  4. በ «ቋንቋዎችን ይምረጡ» ክፍል ውስጥ፦ 
    • በመጀመሪያው ጽሁፍዎ ውስጥ ሥራ ላይ የዋለውን ምንጭ ቋንቋ ይግለጹ።
    • የትርጉም ዒላማ ቋንቋዎችዎን ይምረጡ። 
    • የእርስዎን ቋንቋዎች መርጠው ሲጨርሱ ቀጣይን ጠቅ ያድርጉ።
  5. በ«ምን እንደሚተረጎም ይምረጡ» ክፍል ውስጥ ለማስተርጎም የሚፈልጓቸውን ንጥሎች ይምረጡ፦
    • የመደብር ዝርዝር፦ በGoogle Play ላይ ለተጠቃሚዎች እንደሚታየው የመተግበሪያዎን ርዕስ፣ አጭር መግለጫ እና ሙሉ መግለጫ ያቅርቡ።
    • የመተግበሪያ ሕብረቁምፊዎች፦ ከመተግበሪያዎ የተገኘን ጽሁፍ እንደ የXML ወይም የCSV ፋይል ያክሉ።
    • የውስጠ-መተግበሪያ ምርቶች፦ የውስጠ-መተግበሪያ ምርቶችዎን ርዕስ እና መግለጫ ያቅርቡ።
    • ለማስተርጎም የሚፈልጉትን መርጠው ሲጨርሱ ትርጉሞችን አሳይን ጠቅ ያድርጉ።
  6. የትርጉሞች አገልግሎቶች ገጽ ላይ የእርስዎን የመደብር ዝርዝር ጽሑፍ እና የውስጠ-መተግበሪያ ምርት ትርጉሞችን ለመገምገም እና ለመተግበር ይገምግሙ እና ይተግብሩን ጠቅ ያድርጉ። ምንም ለውጦችን ማድረግ ካልፈለጉ በማሽን በተተረጎመው ጽሑፍ ላይ ምንም ለውጦችን ሳያደርጉ ተግብርን ጠቅ ያድርጉ። እንዲሁም የእርስዎን በማሽን የተተረገሙ ሕብረቁምፊዎች ከትርጉም አገልግሎቶች ገጽ ማውረድ ይችላሉ።
ትርጉሞችን የማያክሉ ወይም የማይገዙ ከሆነ

በቋንቋው ተወላጆች የተተረጎሙ ትርጉሞችን መጠቀም በጣም የተሻለ ሲሆን፣ የእርስዎ መተግበሪያ መደብር ዝርዝር ራስ-ሰር ትርጉሞች ለGoogle Play ተጠቃሚዎች የሚገኙ ይሆናሉ።

ተጠቃሚዎች በGoogle Play ላይ የመተግበሪያዎን መደብር ዝርዝር እርስዎ ባልተረጎሙት ቋንቋ ከጎበኙት በራስ-ሰር የተተረጎመ የመተግበሪያዎን ገጽ ለመመልከት መምረጥ ይችላሉ። ከገጹ አናት አጠገብ ትርጉሙ በራስ-ሰር መሰራቱን የሚያብራራ ማሳወቂያ ይኖራል፣ ከዚህ ይልቅ የመደብር ዝርዝሩን በነባሪው ቋንቋ ለመመልከት ከሚያስችል ከአንድ አማራጭ ጋር አብሮ።

ማስታወሻ፦ ራስ-ሰር ትርጉሞች በአርመንኛ፣ በራኤቶ-ሮማንስ፣ በታጋሎግ እና በዙሉ አይገኙም።

የቋንቋ ምክሮች

በአንዳንድ አጋጣሚዎች ላይ በ Play Console ላይ ጭነቶችን ለመጨመር ከፍ ያለ ዕድል ያላቸው የትርጉም ምክሮችን የያዘ ሰንደቅ ሊያዩ ይችላሉ። 

በቂ ውሂብ ሲኖር እነዚህ ምክሮች በሚከተሉት ላይ የተመሠረቱ ይሆናሉ፦

  • መተግበሪያዎ ለእያንዳንዱ ቋንቋ ያለው የአሁኑ የጭነት ስርጭት ከሌሎች ተመሳሳይ ምድብ ውስጥ ካሉ መተግበሪያዎች ጋር ይነጻጸራል።
  • መተግበሪያዎ ለእያንዳንዱ ቋንቋ ያለው የአሁኑ የጭነት ዕድገት ከሌሎች ተመሳሳይ ምድብ ውስጥ ካሉ መተግበሪያዎች ጋር ይነጻጸራል።
  • የመተግበሪያዎ ምድብ እና ለዚያ ምድብ ያሉት የቋንቋ ምርጫዎች።
  • መተግበሪያዎ ለእያንዳንዱ ቋንቋ ያለው የአሁኑ የልወጣ ብዛት።
  • ለእያንዳንዱ ቋንቋ ያለው የገበያ ዕድል።

የተዘመኑ ትርጉሞች

ከዚህ በፊት ትርጉሞች ለነበሩት መተግበሪያ የትርጉም ጥያቄ እያስገቡ ከሆነ እነዚህን ከግምት ውስጥ ያስገቡ፦

  • ከቀዳሚው ልቀት ወዲህ የተዘመነ ማንኛውም ጽሑፍ ማስተርጎም አለብዎት። ከዚህ በፊት የተተረጎሙ ሕብረቁምፊዎችን ማስገባት አያስፈልገዎትም።
  • ትዕዛዝ ሲያስገቡ ጽሑፉን ከቀዳሚዎቹ ትዕዛዞችዎ ጋር እናነጻጽራለን። ለአዲስ ጽሑፍ ብቻ እንዲከፍሉ ማንኛውም ነባር ጽሑፍ ከትዕዛዙ ይወጣል።
  • ሁሉንም ጽሑፍ (ከዚህ ቀደም የተተረጎሙ ሕብረቁምፊዎችም ጨምሮ) ለትርጉም ማስገባት ከፈለጉ ትርጉምዎን ሲገዙ በምን እንደሚተረጎም ይምረጡ ገጹ ላይ ከ«የተተረጎሙ ሕብረቁምፊዎችን ዳግም ተጠቀም» ቀጥለው ባለው ሳጥን ላይ ምልክቱን ያንሱ።

የትዕዛዝ ሁኔታን ይመልከቱ

የትርጉም ግዢዎችዎን ሁኔታ ለመከታተል፦

  1. Play Consoleን ይክፈቱ እና ወደ የትርጉም አገልግሎት ገጽ (አሳድግ > የመደብር ተገኝነት > የትርጉም አገልግሎት) ይሂዱ።
  2. ለእያንዳንዱ ትዕዛዝ የግዢውን ቀን፣ የተጠየቁትን ቋንቋዎች፣ ሁኔታን እና የተከፈለውን ዋጋ ያያሉ። ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማየት አንድ ረድፍ መምረጥ ይችላሉ።

የትርጉም አቅራቢን ያነጋግሩ

የእርስዎን ትርጉም አቅራቢ ለማነጋገር፦

  1. Play Consoleን ይክፈቱ እና ወደ የትርጉም አገልግሎት ገጽ (አሳድግ > የመደብር ተገኝነት > የትርጉም አገልግሎት) ይሂዱ።
  2. ከእርስዎ ትዕዛዝ ቀጥሎ ያለውን የሦስት ነጥብ አዶ  > የአገልግሎት አቅራቢውን ያነጋግሩን ጠቅ ያድርጉ።

ትርጉሞችዎን ይመልከቱ ወይም ይፈትሹ

መተግበሪያዎን በሌላ ቋንቋ ለመመልከትና የመተግበሪያዎን ትርጉሞች ለመፈተሽ በAndroid መሣሪያዎ ላይ ያለውን ቋንቋ መቀየር ይኖርብዎታል። ይህንን ለማድረግ፦

  1. በእርስዎ መሣሪያ ላይ የቅንብሮች መተግሪያውን ይክፈቱ።
  2. ቋንቋ እና ግቤት > ቋንቋ የሚለውን ይምረጡ።
  3. መመልከት የሚፈልጉበትን ቋንቋ ይምረጡ።
  4. የእርስዎን መተግበሪያ ይገምግሙ።

የተእታ ክፍያ መጠየቂያ ይጠይቁ

ለእርስዎ የትርጉም ትዕዛዝ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ተእታ) ክፍያ መጠየቂያ የሚያስፈልገዎት ከሆነ ወደ Google payments የእገዛ ማዕከል ይሂዱ።

ተዛማጅ ይዘት

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?

ተጨማሪ እገዛ ያስፈልግሃል?

እነዚህን ቀጣይ እርምጃዎች ይሞክሩ፦

ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
4708675656492129793
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
92637
false
false