ለመተግበሪያዎ ፈቃዶችን ያውጁ

የፈቃድ ጥያቄዎች የእርስዎን Android መተግበሪያ ቅርቅብ ካከሉ በኋላ በሚኖረው የልቀት ሂደት ላይ ይገመገማሉ። የእርስዎ መተግበሪያ ከፍተኛ አደጋን ሊያስከትሉ የሚችሉ ወይም አደገኛ ፈቃዶችን (ለምሳሌ፦ ኤስኤምኤስ ወይም የጥሪ ምዝገባ ማስታወሻ) መጠቀምን የሚጠይቅ ከሆነ የፈቃዶች ማወጂያ ቅጽን እንዲሞሉ እና ከGoogle Play ፈቃድ እንዲያገኙ ሊጠየቁ ይችላሉ።

ስለሂደቱ

መተግበሪያው ለGoogle Play የፈቃዶች ማወጂያ ያልቀረበለትን ፈቃዶች የሚጠይቅ የመተግበሪያ ቅርቅብ በውስጡ የሚያካትት ከሆነ በልቀት ሂደቱ ላይ የፈቃዶች ማወጂያ ቅጽ እንዲታይ ይደረጋል።

በክፍት፣ በዝግ ወይም በውስጣዊ ሙከራ ትራኮች ላይ ያሉትን ልቀቶች ጨምሮ የፈቃዶች መግለጫ የሚፈልግ ገቢር የመተግበሪያ ቅርቅብ ካለዎት ማንቂያ በመተግበሪያው ይዘት ስር በግራ ምናሌው ላይ ማንቂያ ይታያል። የፈቃዶች ማወጂያን የሚያካትት ወይም ፈቃዶችን የሚያስወግድ ልቀትን በመፍጠር ለዚህ ማስጠንቀቂያ መፍትሔ እስከሚሰጡት ድረስ በእርስዎ የመደብር ተገኝነት ላይ የሚኖሩ ለውጦችን ጨምሮ (ለምሳሌ፦ የመደብር ዝርዝር፣ የዋጋ አሰጣጥ እና ስርጭት) በእርስዎ መተግበሪያ ላይ ማናቸውም ለውጦችን ማተም አይችሉም።

ከዚህ መመሪያ ጋር የማይጣጣሙ ከሆኑ አሁን በስራ ላይ የሌሉ ማናቸውም ክፍት፣ ዝግ ወይም ውስጣዊ የሙከራ ትራኮችን ማቦዘን ከግምት ያስገቡ።

መተግበሪያዎችን የGoogle Play ገንቢ አታሚ ኤፒአይ በመጠቀም ካተሙ፣ እነዚህን ልዩ መመሪያዎች ይመልከቷቸው።

የፈቃዶች ማወጂያ ቅጹን ይሙሉት

 

እርምጃ 1፦ የተጠየቁ ፈቃዶችን ይገምግሙ

ሊተገበር የሚችል ከሆነ ከመተግበሪያ ይዘት ገጹ የ«የፈቃዶች ማወጂያ ቅጽ» ክፍል ሥር ያለውን ሊዘረጋ የሚችል ዝርዝር ውስጥ ያሉትን እንደ አዲስ የቀረቡ የፈቃድ ጥያቄዎችን ጨምሮ ከዚህ ቀደም የታወጁ ፈቃዶችን ታሪክ ያገኛሉ።

  • አመልካች ሳጥን ያላቸው ፈቃዶች ከዚህ ቀደም በነበሩት ልቀቶች ላይ ታውጀዋል።

  • ማንቂያ ያላቸው ፈቃዶች እንደ አዲስ የታከሉ ናቸው። እነዚህ የፈቃድ ጥያቄዎች በGoogle Play ቡድን እንዲገመገሙ በእርስዎ የማወጂያ ቅጽ ውስጥ የሚታከሉ ሲሆን ከታተሙ መመሪያዎች አንጻር ይገመገማሉ።
በአዲሱ የተጠየቁ ፈቃዶች ዝርዝር ውስጥ በእርስዎ የፈቃዶች ማወጂያ ቅጽ ላይ ለማካተት ያላቀዷቸውን ፈቃዶች ከተመለከቱ ይህ የመተግበሪያ ቅርቅብ ወይም ኤፒኬ ከመሰናዳቱ በፊት ማስወገድ እና አግባብ የሆኑ የተጠየቁት ፈቃዶች ስብስብ ያለው አዲስ የመተግበሪያ ቅርቅብ መስቀል አለብዎት።

 

እርምጃ 2፦ የእርስዎን መተግበሪያ ዋና ተግባራዊነትን ይግለጹ

ከሚደገፉ የተጠቃሚ ገጠመኞች ዝርዝር የእርስዎን መተግበሪያ ዋና ትግበራ ባህሪ በግልፅ መጥቀስ ይኖርብዎታል። ወደ የእርስዎ መተግበሪያ ዋና ትግበራ ባህሪ ተፈጻሚነት ያላቸውን ሁሉንም ሳጥኖች ምልክት ያድርጉና ይምረጡዋቸው።

እርምጃ 3፦ ለመተግበሪያ ግምገማ መመሪያዎችን ያቅርቡ

አንዴ የእርስዎን የፈቃዶች ማወጂያ ቅጽ ካስገቡ በኋላ የተጠየቁት ፈቃዶች ለሚደገፍ የተጠቃሚ አጠቃቀም የሚያስፈልጉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የGoogle Play ቡድን የእርስዎን መተግበሪያ ዋና የትግበራ ባህሪ ይገመግማል። 
ይህን ዋና ተግባር ለማሳየት የተወሰኑ መመሪያዎች የሚያስፈልጉ ከሆኑ እነዚያን መመሪያዎች በዚህ ክፍል ውስጥ ሊያካትቷቸው ይችላሉ።

እርምጃ 4፦ የእርስዎን መተግበሪያ የቪዲዮ የተግባር ማሳያ ያቅርቡ

የGoogle Play ግምገማ ቡድን የእርስዎን መተግበሪያ ዋና ትግበራ ባህሪ በቀላሉ ለመገምገም እንዲችል የቪዲዮ የተግባር ማሳያ ማቅረብ አለብዎት።

የሚደገፉ የቪዲዮ ቅርጸቶች፦ ለmp4 ወይም ሌላ የተለመደ የቪዲዮ ፋይል ቅርጸት የYouTube አገናኝ (ይበልጥ ይመረጣል)፣ የደመና ማከማቻ አገናኝ

እርምጃ 5፦ የተገደበ መተግበሪያ ይዘትን ለመድረስ መመሪያዎች ያቅርቡ

የመተግበሪያዎ ወሳኝ ተግባራት በመለያ ለገቡ ተጠቃሚዎች የተወሰነ ከሆነ ይህን የተገደበ ይዘት የሚደረስበት መመሪያዎችን ማቅረብ አለብዎት። የGoogle Play ግምገማ ቡድኑ የተገደበውን ተግባር ለመገምገም እነዚህን መመሪያዎች ይጠቀማል።

የእርስዎ መተግበሪያ በመለያ መግባት የሚያስፈልገው ከሆነ ሁሉም ወይም አንዳንድ ተግባራት የተገደቡ ናቸው ን ይምረጡና የሚሰራ የሙከራ ተጠቃሚ ስም ወይም ስልክ ቁጥር፣ የይለፍ ቃል እና የተገደበውን የመተግበሪያ ይዘት ለመድረስ የሚያስፈልጉት ሌሎች ማናቸውም መመሪያዎችን ማቅረብ አለብዎት።

ለሙከራ ብቻ የሆኑ የመለያ መግቢያ ማስረጃዎችን ብቻ ያቅርቡ። የማንኛውም ፕሮዳክሽን ተጠቃሚ መግቢያ መረጃዎችን አያቅርቡ።
አለበለዚያ የሙከራ መግቢያ መረጃዎችን ሳያቀርቡ ለመቀጠል ሁሉም ተግባራት ያለልዩ መዳረሻ ይገኛሉን ይምረጡ።

እርምጃ 6፦ (ባለብዙ ኤፒኬ ብቻ) ለድሮ ኤፒኬዎች ለየት ያለ ይጠይቁ 

ማስታወሻ፦ ይህ መስክ የሚታየው ለልቀቶችዎ ባለብዙ ኤፒኬ ውቅረት የሚጠቀሙ ከሆኑ እና አንዱ የኤፒኬ ስሪት የጥሪ ምዝግብ ማስታወሻ ወይም የኤስኤምኤስ ውሂብን ለመጠቀም ፈቃድ ከጠየቀ ብቻ ነው።

የእርስዎ ባለብዙ-ኤፒኬ ውቅረት ከእንግዲህ የኮድ ለውጦችን ሊያደርጉባቸው የማይችሉባቸው የድሮ ኤፒኬዎችን የሚጠቀሙ በሆኑባቸው አጋጣሚዎች የማይካተት ማስገባት ይችላል። ከመቀጠልዎ በፊት ለዚህ የማይካተት ያሉትን መስፈርቶች ያማክሩ። ከመቀጠልዎ በፊት ለዚህ የማይካተት የሁኔታ መስፈርቶቹን ያማክሩ–ለበለጠ መረጃ የኤስኤምኤስ ወይም የጥሪ ምዝግብ ማስታወሻ ፈቃድ ቡድኖች እና ከበስተጀርባ ያለውን የአካባቢ መዳረሻ መጠየቅ ጽሑፎችን ይመልከቱ።

የፈቃዶች መመሪያውን ለማክበር መስፈርቶቹን የማያሟሉ ማናቸውም ኤፒኬዎች መቦዘን አለባቸው።

ለዚህ የማይካተት ብቁ ከሆኑ የስሪት ኮዱን/ኮዶቹን በማይካተቱ የኤፒኬዎች መስክ ላይ በኮማ አለያይተው ያስገቡ። 

እርምጃ 7፦ የእርስዎን ማወጂያ ያረጋግጡ

የእርስዎ ማወጂያ ዝርዝሮች ትክክለኛ እንደሆኑ እና የታወጁትን ፈቃዶች ተገቢነት ያላቸውን አጠቃቀም በተመለከተ እንደሚስማሙ ለማረጋገጥ ተጓዳኝ አመልካች ሳጥኖቹን ይምረጡ።

ልቀትዎን ያዘጋጁ እና ይልቀቁ

የፈቃዶች ማወጂያ ቅጹን በተመለከተ የሚያስፈልጉትን ቅድመ ሁኔታ እርምጃዎች አንዴ ካሟሉ በኋላ መተግበሪያዎን ለግምገማ ለማዘጋጀት እና ልቀትዎን አዘጋጅተው ለመልቀቅ ቀሪዎቹን እርምጃዎች ያጠናቅቁ።

የፈቃዶች ግምገማ ሂደት

የፈቃዶች ማወጂያ ቅጽን ሞልተው ሲጨርሱ እና የእርስዎን የታቀደ ልቀት ሲለቁ የእርስዎ መተግበሪያ በGoogle Play ቡድን በጥልቀት የሚገመገም ይሆናል። የእርስዎ ጥያቄ እስከሚስተናገድ በርካታ ሳምንታትን ሊወስድ ይችል ይሆናል። በዚህ ጊዜ ላይ የእርስዎ አዲሱ መተግበሪያ ወይም የመተግበሪያ ዝማኔ የእርስዎ ጥያቄ እስከሚገመገም ድረስ ሕትመትን በመጠባበቅ ላይ ያለ ሁነታ ላይ ይሆናል። የእርስዎ መተግበሪያ በተጨማሪም የGoogle Play ገንቢ ፕሮግራም መመሪያዎች መደበኛ የተገዢነት ግምገማ ማለፍ ግድ ይሆንበታል።

አዲስ ልቀትን በማምጣት የእርስዎን በመጠባበቅ ላይ ያለ ሕትመትን ከሻሩ፣ በእርስዎ የግምገማ ሂደት ላይ ተጨማሪ መዘግየቶች መኖራቸውን ሊያስተውሉ ይችሉ ይሆናል። አንድን የመተግበሪያ ዝማኔ በአስቸኳይ መልቀት የሚፈልጉ ከሆነ፣ ከእርስዎ የመተግበሪያ ቅርቅብ ላይ ያሉትን ከፍተኛ-አደጋ ሊያስከትል የሚችል ወይም አደገኛ ፈቃዶችን ማስወገድ እና አዲስ ልቀት መልቀት ይኖርብዎታል። ይህ አዲስ ልቀት ከመመሪያዎች ጋር በመደበኛ ሁኔታ ተገዢ መሆኑ ብቻ ይገመገም እና በበርካታ ሰዓታት ውስጥ የሚታተም ይሆናል።

የእርስዎ መተግበሪያ በፈቃዶች መመሪያ ተገዢ ካልሆነ፣ የGoogle Play ቡድን ከግምገማው ውጤቶች ጋር ወደ መለያው ባለቤት እና በእርስዎ የገንቢ መለያ የእውቂያ ኢሜይል አድራሻ ወደ ሰጡት ኢሜይል ይልካል። የእርስዎ ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ እና የእርስዎ መተግበሪያ በገንቢ ፕሮግራም መመሪያዎች ተገዢ ከሆነ የእርስዎ አዲሱ መተግበሪያ ወይም ዝማኔ በራስ-ሰር ወደ Google Play ይታተማል።

ለGoogle Play ገንቢ አታሚ ኤፒአይ ተጠቃሚዎች ልዩ መመሪያዎች

የGoogle Play ገንቢ አታሚ ኤፒአይን ተጠቅመው አንድን ልቀት በታቀደ ልቀት ከለቀቁ እና Google Play ከዚህ ቀደም የእርስዎ የመተግበሪያ ቅርቅብ ከፍተኛ አደጋን ሊያስከትል የሚችል ወይም አደገኛ ፈቃዶች እንዲጤቀም ያልፈቀደ ከሆነ ስህተት ነው የሚል መልዕክት ይደርሰዎታል።

የአታሚ ኤፒአይን በመጠቀም ልቀቶችን ማቀናበሩን መቀጠል የሚፈልጉ ከሆነ በእርስዎ የመተግበሪያ ቅርቅብ ላይ ያሉትን ከፍተኛ አደጋ ወይም አደገኛ ፈቃዶችን ማስወገድ እና በተሻሻለው የመተግበሪያ ቅርቅብ አዲስ ልቀት መፍጠር ይኖርብዎታል። እንዲሁም እነዚህን እርምጃዎች በመጠቀም የPlay Console የድር ዩአይን በመጠቀም የእርስዎን ልቀት ማዘጋጀት እና በታቀደ ልቀት መልቀቅ ይችላሉ፦

  1. የእርስዎን የመተግበሪያ ቅርቅብ ከተጠየቁት ከፍተኛ አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ወይም አደገኛ ፈቃዶች ጋር ይስቅሉ

  2. ልክ ከዚህ በላይ እንዳለው የፈቃዶች ማወጂያ ቅጹን ይሙሉት

  3. የPlay Console ድር ጣቢያ ዩአይ በመጠቀም የልቀትን የታቀደ ልቀት ያጠናቁ

የእርስዎ የፈቃድ ማወጂያ አንዴ ከጸደቀ በኋላ እና የእርስዎ መተግበሪያ በመመሪያ ተገዢ ስለመሆኑ ከጸደቀ የእርስዎ ልቀት ይታተማል እና አሁንም እንደገና የእርስዎን ልቀቶች ለማስተዳደር የአታሚ ኤፒአይን መጠቀም ይችላሉ። አለበለዚያ የGoogle Play ቡድን የእርስዎ የፈቃዶች ማወጂያ ውድቅ ስለመደረጉ ያሳውቅዎት እና ማናቸውንም ተጨማሪ መረጃ ይሰጥዎታል።

ማስታወሻ፦ የእርስዎ መተግበሪያ ማናቸውም አዲስ ፈቃዶችን በጠየቀ ጊዜ አዲሶቹን የተጠየቁት ፈቃዶች በተመለከተ የተሻሻለ የፈቃዶች ማወጂያ ቅጽ ለመሙላት ዩአዩን እንዲጠቀሙ ይፈለግብዎታል።

ተዛማጅ ይዘት

  • Play አካዳሚ ውስጥ ስለPlay Console ፈቃዶች የበለጠ ይወቁ።

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?

ተጨማሪ እገዛ ያስፈልግሃል?

እነዚህን ቀጣይ እርምጃዎች ይሞክሩ፦

true
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
12181323093367104789
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
92637
false
false