ለሚከፈልበት አባልነት የሒሳብ አከፋፈል ወይም የመዳረሻ ችግሮች መላ ይፈልጉ

የእርስዎ የሚከፈልበት አባልነት ውቅድ ከተደረገ አባልነትዎን ወደነበረበት መመለስ እንዲችሉ በኢሜይል በኩል እናሳውቅዎታለን።

ይህን ኢሜይል ካገኙ በኋላ፦

  • ለእርስዎ የሚከፈልበት አባልነት ጥቅማጥቅሞች ያለዎትን መዳረሻ ከማጣትዎ በፊት ችግሩን ለመጠገን 3 ቀናት ይኖርዎታል። በዚህ የ3 ቀን ጊዜ ውስጥ ወርሃዊ ክፍያዎን በመደበኛነት እንደገና ለማሰናዳት እንሞክራለን።

  • ከ3 ቀናት በኋላ አሁንም ልናስከፍለዎት ካልቻልን የደንበኝነት ምዝገባዎ ለ30 ቀናት ወደ የ«ባለበት ቆሟል» ሁኔታ ላይ ይገባል። በዚህ ባለበት በቆመበት ሁኔታ ላይ የደንበኝነት ምዝገባዎን ካልሰረዙ በስተቀር የአባልነትዎን መዳረሻ ወደነበረበት ለመመለስ በየጊዜው ክፍያ ለማሰናዳት እንሞክራለን።

በዚህ ጊዜ ውስጥ የክፍያ መረጃዎን ካዘመኑ አባልነትዎ በራስ-ሰር በቀጣዩ የመክፈያ ዘዴዎን የማስከፈል ሙከራችን ላይ ወደነበረበት ይመለሳል። ስርዓቱ ዳግም እስኪሞክር ድረስ መጠበቅ ካልፈለጉ ወዲያውኑ መዳረሻ ለማግኘት የደንበኝነት ምዝገባዎን ሰርዘው ዳግም መመዝገብ ይችላሉ።

Fix billing issues with a Premium membership

ለሚከፈልበት አባልነት እንዲከፍሉ ተደርገው ነገር ግን ጥቅማጥቅሞችዎን መድረስ እንዳልቻሉ ካመኑ ይህን ጽሑፍ ይመልከቱ

ለYouTube ክፍያ መላ ይፈልጉ

ስለ YouTube ሒሳብዎ መላ ለመፈለግ ወይም ለማወቅ ከታች ያለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

ለYouTube ክፍያ መላ ይፈልጉ

ለሚከፈልበት አባልነት የከፈሉት ክፍያ ውድቅ ከተደረገ በመክፈያ ዘዴዎ ላይ ያለ ችግርን ማስተካከል አለብዎት ማለት ነው። ከታች እንዴት እነዚህን ችግሮች እንደሚያስተካክሉ ላይ ጠቃሚ ምክሮቻችንን ይመልከቱ።

ውድቅ የተደረገ ክፍያን ያስተካክሉ

ወርሃዊ የአባልነት ክፍያዎ ውድቅ የተደረገው በካርድዎ ወይም በሌላ የመክፈያ ዓይነት ላይ ባለ ችግር ምክንያት ሊሆን ይችላል። አንዴ ማናቸውንም የክፍያ ችግሮች ከጠገኑ በኋላ ሥርዓቱ በድጋሚ በራስ-ሰር ሊያስከፍልዎ እና ለእርስዎ የአባልነት ጥቅማጥቅሞች መዳረሻዎን እንደገና ወደነበረበት ለመመለስ ይሞክራል።

የካርድዎ መረጃ የተዘመነ መሆኑን ያረጋግጡ።

አሁን አዘምን                

ክፍያዎች አብዛኛውን ጊዜ የማይሳኩት ጊዜው ባለፈበት ክሬዲት ካርድ ወይም በተሳሳተ የሒሳብ መጠየቂያ አድራሻ ምክንያት ነው። ይህን መረጃ ለማዘመን፦

  1. ኮምፒውተር ላይ ከሆኑ ወደ youtube.com/paid_memberships ይሂዱ። የYouTube ሞባይል መተግበሪያ ላይ ከሆኑ የመገለጫ ስዕልዎን «» እና በመቀጠል ግዢዎች እና አባልነቶች ጠቅ ያድርጉ።
  2. ከ«የአሁኑ የመክፈያ ዘዴ ሊሰናዳ አልቻለም» መልዕክት ጎን ያለውን ጠቅ ያድርጉ።
  3. የመክፈያ ዘዴን አዘምንን ጠቅ ያድርጉ።

የሚያበቃበት ቀንን ጨምሮ ሁሉንም የካርድ መረጃዎችዎ ትክክለኛ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እንዲፈትሹ እንመክራለን። ለመክፈያ ዘዴዎ የተዘረዘረው ዚፕ ኮድ እንዲሁም ከካርድዎ የአሁኑ የሂሳብ መጠየቂያ አድራሻ ጋር መመሳሰል አለበት።

በፋይል ላይ ያለው የመክፈያ ዘዴዎ ከእንግዲህ ጥቅም ላይ መዋል ካልቻለ ሌላ የመክፈያ ዘዴ ያክሉ ወይም ይምረጡ።

ጠቃሚ ምክር፦ «የመክፈያ ዘዴን አዘምን» አማራጩን ካላዩት ከGoogle Pay የደንበኝነት ምዝገባዎች እና አገልግሎቶች ገፅ ሆነው ማዘመንም ይችላሉ።

ማንኛውም የተጠየቀ መረጃን ያስገቡ

ለGoogle ተጨማሪ መረጃ እንዲያስገቡ የሚጠይቅ የስህተት መልዕክት ከተመለከቱ እነዚህን ዝርዝሮች ለማስገባት መመሪያዎቹን ይከተሉ። ለምሳሌ፣ የGoogle መለያዎን ተጠቅመው ግዢ መፈጸም ከመቻልዎ በፊት በGoogle Pay ላይ ማንነትዎን ማረጋገጥ ሊኖርብዎት ይችላል።

እንዲሁም በማንኛውም ጊዜ በGoogle Pay የመለያ ችግሮችን ለመጠገን የሚላኩ ማንቂያዎችን ወይም ጥያቄዎችን መፈተሽ ይችላሉ።

ለግዢው በቂ ገንዘብ እንዳለዎት ያረጋግጡ

አንዳንድ ጊዜ ግብይት በቂ ባልሆነ ገንዘብ ምክንያት ውድቅ ሊደረግ ይችላል። ግዢውን ለማጠናቀቅ በቂ እንዳለዎት ለማረጋገጥ መለያዎን ያጣሩ።

የእርስዎን ባንክ ወይም ካርድ ሰጪ ያነጋግሩ

የእርስዎ ካርድ ክፍያዎ እንዳይሳካ የሚያደርጉ የተወሰኑ ገደቦች ሊኖሩት ይችላል። ስለግብይቱ ለመጠየቅ ካርድዎን የሰጠው ባንክ ወይም ኩባንያ ያነጋግሩ።

በተለየ የመክፈያ ዘዴ ለመክፈል ይሞክሩ 

አሁን አዘምን

የሚከተሉትን ደረጃዎች በመከተል ወደ ሌላ የመክፈያ ዓይነት ለመቀየር መሞከር ይችላሉ፦

  1. ኮምፒውተር ላይ ከሆኑ ወደ youtube.com/paid_memberships ይሂዱ። በYouTube ሞባይል መተግበሪያው ላይ ከሆኑ የመገለጫ ስዕልዎን «» እና በመቀጠል ግዢዎች እና አባልነቶችን ጠቅ ያድርጉ።
  2. ከ«የአሁኑ የመክፈያ ዘዴ ሊሰናዳ አልቻለም» መልዕክት ጎን ያለውን የ አዶ ጠቅ ያድርጉ።
  3. የመክፈያ ዘዴን አዘምንን ጠቅ ያድርጉ።
  4. የተለየ የመክፈያ ዘዴ ይምረጡ።

እንዲከፍሉ ከተደረጉ በኋላ ጥቅማጥቅሞችን በመድረስ ላይ ያሉ ችግሮችን ያስተካክሉ

አንድ ግዢ ፈጽመው ነገር ግን የገዙት ነገር መዳረሻ ከሌለዎት ክፍያው አሁንም እየተሰናዳ ሊሆን ይችላል። እንዲሁም ክፍያው ውድቅ ከተደረገ መዳረሻ ላይኖረዎት ይችላል።

ስለመያዣ ፈቃዶች እና በመጠባበቅ ላይ ስላሉ ግብይቶች

በGoogle Pay ወይም በካርድዎ መግለጫ ላይ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ገና ያልተሰናዱ ክፍያዎች የመያዣ ፈቃዶች ናቸው።

እያንዳንዱ በመጠባበቅ ላይ ያለ ክፍያ የፈቀዳ ሙከራ የሚያመለክት እንደመሆኑ መጠን ለተመሳሳዩ የደንበኝነት ምዝገባ ክፍያ ጥቂት በመጠባበቅ ላይ ክፍያዎችን ሊያዩ ይችላሉ። አንድ ክፍያ ከተሰናድቷል ይልቅ «በመጠባበቅ ላይ» ከሆነ እርስዎ እንዲከፍሉት አልተደርጉም፣ እና ማናቸውም ለክፍያ የተደረጉ ያልተሳኩ የካርድ ፈቀዳ ሙከራዎች በራሳቸው ከመግለጫዎችዎ ይወጣሉ እና እርስዎ እንዲከፍሏቸው አይደረጉም።

በመጠባበቅ ላይ ያለ ክፍያን እንዴት መፈተሽ እንደሚቻል

  • የሂሳብ መጠየቂያ መግለጫዎን ወይም Google Payን ይፈትሹ። በGoogle Pay ላይ ያለው ግብይት ላይ ጠቅ ካደረጉ ግዢውን እንደተጠናቀቀ ሳይሆን እንደ «በመጠባበቅ ላይ» ያለ ክፍያ ተዘርዝሮ ሊያዩት ይገባል።
  • የኢሜይል ደረሰኝ ይፈልጉ። አንድ ክፍያ ከተሰናዳ ከYouTube የኢሜይል ደረሰኝ ያገኛሉ።
  • እንዲሁም በማንኛውም ጊዜ በGoogle Pay የመለያ ችግሮችን ለመጠገን የሚላኩ ማንቂያዎችን ወይም ጥያቄዎችን መፈተሽ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ የGoogle መለያዎን ተጠቅመው መግዛት ከመቻልዎ በፊት በGoogle Pay ላይ ማንነትዎን ማረጋገጥ ሊኖርብዎት ይችላል። በGoogle Pay ላይ ይህ በመጠባበቅ ላይ ያለ ክፍያ በ1-14 የስራ ቀናት ውስጥ ያልፋል፣ ወይም ደግሞ ክፍያው ውድቅ ሲደረግ ይጠፋል። አሁንም ከዚህ ጊዜ በኋላ በመጠባበቅ ላይ ያለ ክፍያ እየተመለከቱ ከሆነ የክፍያ አቅራቢዎን ያነጋግሩ።

ውድቅ የተደረገ ክፍያን እንዴት መፈተሽ እንደሚቻል

የግዢዎን ሁኔታ በGoogle Pay ውስጥ ዳግም ማረጋገጥ ይችላሉ። Google Pay የግብይቱን ሁኔታ እንደ «ውድቅ ተደርጓል» አድርጎ ማሳየት አለበት። ውድቅ የተደረገ ክፍያን እንዴት ማስተካከል እንደሚቻል ከላይ ባለው ክፍል ውስጥ የእኛን ጠቃሚ ምክሮች ይመልከቱ።
የሂሳብ ክፍያ መግለጫዎ አሁንም «በመጠባበቅ ላይ» የሚያሳይ ከሆነ ይህ ክፍያ በ1-14 የስራ ቀናት ውስጥ መሄድ አለበት ወይም ውድቅ ከተደረገ ይጠፋል። አሁንም ከዚህ ጊዜ በኋላ በመጠባበቅ ላይ ያለ ክፍያ እየተመለከቱ ከሆነ የክፍያ አቅራቢዎን ያነጋግሩ።

 

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
14224831689395950929
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
59
false
false