በተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት አቅራቢዎ (ቀጥተኛ የአገልግሎት አቅራቢ ክፍያ መጠያቂያ) በኩል በመክፈል ላይ ላሉ ችግሮች መላ ይፈልጉ

በተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት አቅራቢዎ በኩል የሚከፈል ግዢ ላይ ችግር እያጋጠመዎት ከሆነ እነዚህን የመላ ፍለጋ ጠቃሚ ምክሮች ይሞክሯቸው።

ለመጀመሪያ ጊዜ የቀጥተኛ የአገልግሎት አቅራቢ ክፍያ መጠያቂያ ደንበኛዎች ጠቃሚ ምክሮች

በአገልግሎት አቅራቢ በኩል የሚደረግ ክፍያን በመጠቀም ግዢ መፈጸም ላይ ችግር እያጋጠመዎት ከሆነ የሚከተሉትን በማረጋገጥ እንዲጀምሩ እንመክራለን፦

  • በYouTube ላይ በአገልግሎት አቅራቢ በኩል የሚደረግ ክፍያን ሲጠቀሙ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ ከአገልግሎት አቅራቢዎ አውታረ መረብ ጋር ተገናኝተዋል።
  • የሞባይል አሳሽ ወይም ኮምፒውተር ሳይሆን የYouTube መተግበሪያን እየተጠቀሙ መሆንዎን።

እንዲሁም መሣሪያዎን ማጥፋት፣ ጥቂት ሰከንዶችን መጠበቅ እና ኪዚያም መልሶ ማብራትን እንዲሞክሩ እንመክራለን። መሣሪያዎን ካበሩ በኋላ ግዢዎን እንደገና ይሞክሩት።

ተጨማሪ የመላ ፍለጋ ጠቃሚ ምክሮች

አሁንም ችግሮች እያጋጠሙዎት ከሆነ፦

  • የግል መለያ እየተጠቀሙ መሆንዎን ያረጋግጡ። አንዳንድ ኩባንያዎች በድርጅት መለያዎች ላይ በአገልግሎት አቅራቢ በኩል የሚደረግ ክፍያን ሊያግዱ ይችላሉ።
  • ስርወ መሣሪያ መነሻን እየተጠቀሙ እንዳልሆነ ያረጋግጡ።
  • ሁለት ሲም ካርዶች ያሉት መሣሪያ እየተጠቀሙ ከሆነ ትክክለኛውን SIM ካርድ በማስገቢያ 1 ውስጥ ማስገባትዎን እና ማስገቢያ 2ን ባዶ መተዎን ያረጋግጡ።

የአገልግሎት አቅራቢ ቅንብሮችዎን ይፈትሹ

ከላይ ያሉት የትኛዎቹም ጠቃሚ ምክሮች ችግርዎን ካላስተካከሉት አገልግሎትዎ ላይ ተጽዕኖ እያሳደሩ ያሉ አንዳንድ የአገልግሎት አቅራቢ ቅንብሮች ሊኖሩ ይችላሉ። የሚከተሉትን ለማረጋገጥ የአገልግሎት አቅራቢዎን ያነጋግሩ፦

  • በአገልግሎት አቅራቢዎ የተቀናበሩ የወርሃዊ አጠቃላይ የወጪ ገደቦች ላይ ወይም ነጠላ የግዢ ዋጋዎች ላይ አለመድረስዎን (እነዚያ ገደቦች ላይ ሲደረስ የሂሳብ አከፋፈል አማራጩ ይጠፋል)።
  • የቅድመ-ክፍያ ዕቅድን እየተጠቀሙ ከሆነ ለግዢ መጠኑ በቂ ቀሪ ሒሳብ እንዳለዎት።
  • መሣሪያዎ እና የአገልግሎት ዕቅድዎ የPremium ይዘት ግዢዎችን እንደሚፈቅዱ።
  • መሣሪያዎ የተንቀሳቃሽ ስልክ የሂሳብ አከፋፈልን መጠቀም እንደሚችል።

እነዚህ ደረጃዎችን ከሞከሩ እና አሁንም ችግሮች እያጋጠሙዎት ከሆነ ለተጨማሪ እገዛ የተንቀሳቃሽ ስልክ ግልጋሎት ሰጪዎን ያነጋግሩ።

በተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት አቅራቢ በኩል ለሚከፈሉ ነባር አባልነቶች ጠቃሚ ምክሮች

ከጃኑዋሪ 24 2023 አንስቶ Rogers Communications በካናዳ ውስጥ በተደጋጋሚ ለሚከፈልባቸው አባልነቶች ተቀባይነት ያለው የክፍያ ዘዴ አይሆንም። ለYouTube Premium፣ YouTube Music Premium ወይም የሰርጥ አባልነት በRogers Communications በኩል ከተመዘገቡ የክፍያ ዘዴዎን ተቀባይነት ካላቸው የክፍያ ዘዴዎች አንዱ ወደሆነው ያዘምኑ።

ለYouTube የሚከፈልበት አባልነት ለመክፈል ቀጥተኛ የአገልግሎት አቅራቢ ክፍያ መጠየቂያ እየተጠቀሙ ከነበረ እና የክፍያ ችግሮች እያጋጠሙዎት ከሆነ ውድቅ የተደረገበትን ምክንያት ለማወቅ የአገልግሎት አቅራቢዎን ያነጋግሩ። በመለያዎ ላይ እንደ የወጪ ገደብ ማለፍ ያለ ችግር ሊኖር ይችላል።

በአገልግሎት አቅራቢ መለያዎ ላይ ምንም ችግር ከሌለ እሱን እንደ የመክፈያ ዘዴ ማስወገድን እና እንደገና እንደሚከተለው ማከልን ይሞክሩ፦

  1. ወደ እርስዎ በGoogle Pay ላይ የመክፈያ ዘዴዎች ገጽ ይሂዱ እና በአገልግሎት አቅራቢ በኩል የሚደረግ ክፍያ የመክፈያ ዘዴዎን ያስወግዱት። ማስታወሻ፦ ይህን የመክፈያ ዘዴ ለማናቸውም በአሁን ጊዜ ገቢር የሆኑ አባልነቶች እየተጠቀሙት ከሆነ በአገልግሎት አቅራቢ በኩል የሚደረግ ክፍያን ከመለያዎ ማስወገድ አይችሉም።
  2. ወደ YouTube መተግበሪያ ይሂዱ እና የመገለጫ ሥዕልዎ ላይ መታ ያድርጉ «»
  3. ግዢዎች እና አባልነቶች መታ ያድርጉ እና የመመዝገብ ሂደቱን እንደገና ያጠናቅቁ።

በአገልግሎት አቅራቢ በኩል የሚደረግ ክፍያን እንደገና ማከል ላይ ችግሮች እያጋጠሙዎት ከሆነ ከላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠቃሚዎች የመላ ፍለጋ ጠቃሚ ምክሮችን ይመልከቱ።

እነዚህ ካላገዙዎት እባክዎ ለተጨማሪ እገዛ የተንቀሳቃሽ ስልክ ግልጋሎት ሰጪዎን ያነጋግሩ።

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
517997474081008401
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
59
false
false