ከYouTube የሚመጡ ያልተጠበቁ የሂሳብ ክፍያዎችን ይረዱ

በእርስዎ ክሬዲት ካርድ ወይም የባንክ ተጠቃሚ መለያ ላይ (እንደ «GOOGLE*YouTube» ይታያል) ከYouTube የመጣ ያልተጠበቀ ክፍያ እያዩ ከሆነ ለምን ክፍያ እንደተጠየቁ ከታች ያንብቡ።


ከYouTube የሚመጡ ያልተጠበቁ ክፍያዎችን እንዴት እንደሚያስተናግዱ

በጣም ብዙ እንድከፍል ተደርጌያለሁ

  • በግብር ተመኑ ላይ ያለ ማስተካከያ፡- በወርሃዊ የሂሳብ አከፋፈል ክፍያዎ ላይ ከሚከፈልበት አባልነትዎ ጋር በተያያዙ የግብር ተመኖች ለውጦች ምክንያት አነስተኛ መለዋወጦች ሊያዩ ይችላሉ። በYouTube ግዢዎች ላይ የሚጣል ግብር የሚወሰነው አካባቢዎ ውስጥ ባሉ የግብር ሕግጋት ላይ በመመስረት ነው እና በአካባቢያዊ የግብር መስፈርቶች ምክንያት በጊዜ ሂድት ሊለወጥ ይችላል። እዚህ የበለጠ ማወቅ እና በGoogle Pay ውስጥ ማንኛውም የተተገበረ ግብርን ጨምሮ ለግብይቶችዎ ደረሰኞችን ማግኘት ይችላሉ።

  • ወደ የቤተሰብ ዕቅድ አልቀዋል፡- በቅርቡ ወደ የቤተሰብ ዕቅድ ካላቁ የእርስዎ ወርሃዊ የሂሳብ አከፋፈል ክፍያ ለግለሰብ ዕቅድ ከነበረው በላይ ከፍ ያለ ይሆናል። የእርስዎን ዕቅድ ሁኔታ እና ክፍያዎች ለማየት http://youtube.com/purchasesን ይጎብኙ።

  • ክፍያዎች፦ የእርስዎ ባንክ ወይም የካርድ ኩባንያ በአካባቢዎ ላይ በመመስረት ለዓለም አቀፍ ግብይቶች ክፍያዎችን ሊያስከፍል ይችላል። በተጨማሪም በአካባቢያዊ ምንዛሪዎ እና በአሜሪካ ዶላር መካከል በሚኖር ልወጣ ምክንያት መከፈል በሚኖርበት አጠቃላይ ሂሳብ ላይ ለውጦች ሊኖሩ ይችላሉ።

  • መያዣ ፈቃዶች፦ ከወርሃዊ የሂሳብ አከፋፈል ክፍያዎ ጋር ተመሳሳይ ለሆነ መጠን የመያዣ ፈቃድ ሊያዩ ይችላሉ። እነዚህ ፈቀዳዎች የሚከሰቱት YouTube ካርዱ ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲችል እና እርስዎ ግዢውን ለመፈጸም በመለያዎ ውስጥ በቂ ገንዘብ እንዳለዎት ለማረጋገጥ ነው - ነገር ግን ትክክለኛ ክፍያ አይደሉም። ስለመያዣ ፈቃዶች እዚህ የበለጠ ይወቁ።

http://youtube.com/purchasesን በመጎብኘት ለእርስዎ የYouTube የሚከፈልበት አባልነቶች የሂሳብ ክፍያዎችን ማየት ይችላሉ።

በተማሪ ዕቅዶች ላይ የYouTube Premium የዋጋ አሰጣጥ ስህተት፦ በቴክኒካዊ ችግር ምክንያት ለተደጋጋሚ የተማሪ ዕቅድ የተመዘገቡ አንዳንድ የYouTube Premium አባላት ከመጠን በላይ እንዲከፍሉ ተደርገዋል። ለሁሉም ተጽዕኖ ለደረሰባቸው አባላት ገንዘቦችን ተመላሽ ማድረግ ጀምረናል። ተማሪ ከሆኑ እና የእርስዎን Premium የደንበኝነት ምዝገባ በቅናሽ ተመን መቀጠል ከፈልጉ አሁን ያለዎት የክፍያ አከፋፈል ዑደት ከማለቁ በፊት አሁን ያለዎትን ምዝገባ ማረጋገጥዎን ያስታውሱ። ይህን ለማድረግ ወደ መለያዎ በላክነው ኢሜይል ውስጥ «አሁን አረጋግጥ» የሚለውን አዝራር ጠቅ ያድርጉ።

ለሙከራ እንድከፍል ተደርጌያለሁ

ብቁ ካልነበሩ ለሙከራ ከተመዘገቡ በኋላ ክፍያ ሊያዩ ይችላሉ። ለሙከራ ብቁ የሆኑት የመጀመሪያ ጊዜ የYouTube Premium፣ የMusic Premium እና የGoogle Play ሙዚቃ የደንበኝነት ተመዝጋቢ ብቻ ናቸው።

ለሙከራ ሲመዘገቡ ይህ የመጀመሪያ ጊዜዎ ከሆነ እያዩ ያሉት ክፍያ ሳይሆን የመያዣ ፈቃድ ይሆናል። እነዚህ ፈቀዳዎች የሚከሰቱት YouTube ካርዱ ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲችል እና ሙከራዎ ሲያበቃ እርስዎ ግዢውን ለመፈጸም በመለያዎ ውስጥ በቂ ገንዘብ እንዳለዎት ለማረጋገጥ ነው። ስለመያዣ ፈቃዶች እዚህ የበለጠ ይወቁ።

በርካታ ጊዜ እንደከፍል ተደርጌያለው

ከYouTube በርካታ ክፍያዎችን የሚመለከቱባቸው በጣም የተለመዱ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፡-

  • በመለያዎ ላይ ከአንድ በላይ አባልነት አለዎት፦ በስህተት ለተደራረቡ የሚከፈልባቸው አባልነቶች ተመዝገበው እንደሆነ ለማየት እነዚህን የተለመዱ የተባዙ የደንበኝነት ምዝገባ ሁኔታዎች ይመልከቱ።

  • ለተለየ የGoogle የደንበኝነት ምዝገባ ወይም አገልግሎት ክፍያ እያዩ ሊሆን ይችላል፡- በክፍያው ላይ ያሉትን ዝርዝሮች ለማረጋገጥ እና ከYouTube የሚከፈልበት አባልነት የመጣ መሆኑን ለማረጋገጥ በእርስዎ Google Pay መለያ ውስጥ ያለውን «እንቅስቃሴ» ይፈትሹ።

  • የYouTube የሚከፈልበት አባልነት ያለው ከአንድ በላይ መለያ አለዎት። እርስዎ ወይም የመለያዎ መዳረሻ ያለው አንድ ሰው ሌላ የኢሜይል አድራሻን፣ መሣሪያን ወይም የሂሳብ አከፋፈል መሰረተ ስርዓትን በመጠቀም ተመዝግቦ ሊሆን ይችላል። ሌሎች የGoogle መለያዎች ካሉ ለመፈተሽ፦
    1. የመገለጫ ሥዕልዎን «» ጠቅ ያድርጉ።
    2. መለያን ቀያይርን ጠቅ ያድርጉ።
    3. በአሁኑ ጊዜ ከገቡበት መለያ ጎን የጭረት ምልክት ያያሉ። ሌላም የእርስዎ የሆነ መለያ ተዘርዝሮ ካዩ ወደዚያ መለያ ለመቀየር መታ ያድርጉት።
    4. http://youtube.com/purchasesን በመጎብኘት ሌላ መለያዎ ለሚከፈልበት አባልነት እንደተመዘገበ ያረጋግጡ። ሌሎች የተዘረዘሩ መለያዎች ከሌሉ በማንኛውም ጊዜ የእርስዎ የሆኑ ሌሎች የGoogle መለያዎችን በመጠቀም ለመግባት መሞከር እና ገቢር አባልነቶችን መፈተሽ ይችላሉ።
  • የመያዣ ፈቃድ ወይም «በመጠባበቅ ላይ ያለ» ክፍያ እያዩ ይሆናል፦ እነዚህ ፈቀዳዎች የሚከሰቱት YouTube ካርዱ ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ እንዲችል እና እርስዎ ግዢውን ለመፈጸም በመለያዎ ውስጥ በቂ ገንዘብ እንዳለዎት ለማረጋገጥ ነው - ነገር ግን ትክክለኛ ክፍያ አይደሉም። ስለመያዣ ፈቃዶች እዚህ የበለጠ ይወቁ።

ያልፈጸምኩት ክፍያ ይታየኛል

መለያዎ ላይ የማያውቁት ክፍያ ካለ እነዚህን ያልተፈቀደ ክፍያ ይግባኝ ለመሙላት እነዚህን የሚመከሩ ቀጣይ ደረጃዎች እና መመሪያዎች ይመልከቱ።

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
17441829085242236275
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
59
false
false