የእርስዎን የማንነት ወይም የክፍያ መረጃን ያረጋግጡ

እንደ ለGoogle ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ምዝገባዎች፣ ግብይቶች ወይም የመክፈያ ዘዴ ለውጦች ላሉ ልዩ የGoogle መለያ እንቅስቃሴዎች ማንነትዎን ማረጋገጥ ወይም ጥቅም ላይ የዋለው የመክፈያ ዘዴ ባለቤትነትን ማረጋገጥ ሊኖርብዎት ይችላል።

ስለ ማረጋገጫ

እንዲያረጋግጡ ለምን ልንጠይቅዎ እንደምንችል
  • ልዩ ይዘት እንዲደርሱ መረጃዎ ትክክል እንደሆነ ለማረጋገጥ።
  • በGoogle ግብይት ሲፈጽሙ ማንነትዎን ለማረጋገጥ።
  • ያልተለመዱ እንቅስቃሴ ወይም ግብይቶች ስናገኝ።
  • ለሕጋዊ ወይም ደንብ አስከባሪ ምክንያቶች ተጨማሪ መረጃ ሲያስፈልገን።

አስፈላጊ፦ መለያዎን እንዲያረጋግጡ ከጠየቅን ማናቸውም በመጠባበቅ ላይ ያሉ ግብይቶች ይሰረዛሉ። በእርስዎ የባንክ ሒሳብ መግለጫ ላይ ያሉ በመጠባበቅ ላይ ያሉ ክፍያዎች በ14 የሥራ ቀናት ውስጥ ይጠፋሉ።

እንዲያቀርቡ ሊጠየቁት የሚችሉት መረጃ

ማረጋገጫ ለማጠናቀቅ እያንዳንዱን የመክፈያ ዘዴ እንዲያረጋግጡ ሊጠየቁ ይችላሉ። እንደዚያ ለማድረግ ማረጋገጫ ኮድ መጠየቅ ይችላሉ። 

እንዲሁም እንዲያቀርቡ ሊጠየቁት የሚችሉት፦

  • ሕጋዊ ስም
  • በእርስዎ የክፍያዎች መገለጫ ላይ የተጠቀሙት ስም
  • አድራሻ
  • የልደት ቀን
  • የእርስዎ የመንግሥት መታወቂያ ምስል
  • የአድራሻ ማረጋገጫ
  • የመክፈያ ዘዴዎ ምስል
መረጃዎን እንዴት እንደምንጠቀም

Google የሚያቀርቡትን መረጃ ለሚከተለው ይጠቀማል፦

  • ማንነትዎን ወይም የመክፈያ ዘዴዎን ለማረጋገጥ።
  • መጭበርበር እና አላግባብ መጠቀምን ለመከላከል።
  • ለGoogle ምርቶች የማረጋገጫ አገልግሎቶችን ለማሻሻል።

እንደ ስም እና አድራሻ ያለ የእርስዎ የተረጋገጠ መረጃ በእርስዎ Google መለያ ውስጥ ይከማቻል። የእርስዎን የተረጋገጠ መረጃ payments.google.com ላይ ማስተዳደር ይችላሉ።

ተግባራዊ ሲሆን፣ እርስዎ የሚያስገቡት መረጃ Google የግላዊነት መመሪያ እና Google Payments የግላዊነት ማስታወቂያ በሚሉት መሰረት ይስተናገዳል።

ማረጋገጫን እንዴት እንደሚያጠናቅቁ

መረጃዎን ለማረጋገጥ ሰነዶችን ማስገባት ወይም ኮድ መጠየቅ ሊኖርብዎት ይችላል።

  1. ወደ payments.google.com ይሂዱ።
  2. ወደ መለያዎ ይግቡ።
  3. በላይኛው ቀኝ ላይ ማንቂያዎች Alert እና ከዚያ አረጋግጥ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።
    • ማንቂያዎች ከሌሉ መክፈያ ዘዴዎች የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።
  4. መረጋግጥ ካለበት ካርድ ቀጥሎ አረጋግጥ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።
  5. ማረጋገጫ ኮድ እንዲጠይቁ ወይም ሰነድ እንዲሰቅሉ ሲጠየቁ ለእያንዳንዱ ጥያቄ መመሪያዎቹን ይከተሉ።
  6. መረጋገጥ ላለበት እያንዳንዱ የመክፈያ ዘዴ ከላይ ያሉትን እርምጃዎች ይድገሙ።
የማረጋገጫ ኮድ ይጠይቁ
  1. ኮድ አግኝ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።
  2. ወደ የእርስዎ የመክፈያ ዘዴ አቅራቢ ድር ጣቢያ ይሂዱ እና በመለያዎ ይግቡ። 
  3. በእርስዎ የግብይት ታሪክ ውስጥ «GOOGLE» የሚባል ከ$1.95 የአሜሪካ ዶላር በታች የሆነ ጊዜያዊ ክፍያ ይፈልጉ። የማረጋገጫ ኮዱ የመጨረሻዎቹ 6 አሃዞች ነው።
    • የጊዜያዊ ክፍያ መጠኑ በምንዛሬው ዓይነት ይለያያል።
    • ኮዱን ወዲያው ማግኘት አለብዎት ግን እስከ 7 ቀናት ድረስ ሊወስድ ይችላል።
    • ጠቃሚ ምክር፦ በመለያዎ ላይ ያለው ክፍያ ወይም ማቆያ ጊዜያዊ ነው። ክፍያዎች በ30 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይሆናል።
  4. ወደ payments.google.com ይመለሱ።
  5. የ6 አሃዝ ኮዱን ያስገቡ።
  6. አረጋግጥ ላይ ጠቅ ያድርጉ።
ሰነዶችን ይስቀሉ

የእርስዎን ማንነት ወይም የመክፈያ ዘዴ ለማረጋገጥ የማረጋገጫ ጥያቄውን ያግኙ። ተቀባይነት ያገኙ ሰነዶች እና መመሪያዎች ዝርዝርን ለማግኘት በማረጋገጫ ጥያቄ ውስጥ ያለውን አገናኝ ይጠቀሙ።

ሰነዶችዎ የሚከተሉትን እንደሆኑ ያረጋግጡ፦

  • በሚያስገቧቸው ሁሉም ሰነዶች ውስጥ አንድ ዓይነት ሙሉ ስም እንደተጠቀሙ።
  • የዘመኑ እና ጊዜያቸው ያላለፈባቸው መሆናቸውን።
  • ሕጋዊ መሆናቸውን።

የሚሰቅሉት ምስል የሚከተለውን መሆኑን ያረጋግጡ፦

  • የሰነድ እና ሌላ ምንም ያልሆነ ምስል እንደሆነ
  • ሕጋዊ መሆኑን
  • ባለቀለም፣ በጥቁር እና ነጭ እንዳልሆነ
  • ብዥታ፣ ነጸብራቅ ወይም ደብዛዛ ብርሃን እንደሌለው
  • የሙሉ ሰነዱን ሁሉም 4 ጠርዞችን እንደሚያሳይ

ጠቃሚ ምክሮች፦

  • የእርስዎ ስም፣ አድራሻ እና የክፍያ መረጃ payments.google.com ላይ ወቅታዊ እንደሆኑ ያረጋግጡ።
  • የእርስዎን ሰነዶች ካስገቡ በኋላ ማረጋገጫ የተወሰኑ ቀናትን ሊወስድ ይችላል።
አሳሳቢ ማንቂያውን የት እንደሚያገኙ

Google Pay notifications

ማረጋገጫ ላይ ያሉ ችግሮችን ይጠግኑ

የማረጋገጫ ኮዶች እና በጊዜያዊነት የተደረገ ገደብ ያላቸውን ችግሮች ይጠግኑ

በማረጋገጫ ኮድ የመክፈያ ዘዴዎችን ለማረጋገጥ ሲሞክሩ ችግሮችን እንዴት እንደሚጠግኑ ይወቁ

የሰነድ ማረጋገጫ ችግሮችን ይጠግኑ

ችግሩን ለመፍታት፦

  • ኢሜይል ከደረሰዎት ወይም የስህተት መልዕክት ካገኙ፦ በመልዕክቱ ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተሉ።
  • ችግሩ እንዲፈታ ለማገዝ ከቡድናችን እገዛ ካስፈለገዎት፦ መረጃዎን ከገመገምን በኋላ እናገኝዎታለን።

ያልተሳካ ማረጋገጫ

ማረጋገጫ ካልተሳካልዎት ከውሳኔው በኋላ በአጭሩ ኢሜይል ይደርስዎታል። ውሳኔውን ይግባኝ ለማለት በኢሜይል ውስጥ ያሉትን መመሪያዎች ይከተሉ።

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
15616366935298447011
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
59
false
false