ቪድዮዎችን በበይነመረብ አሳሽዎ ወይም በተንቀሳቃሽ መሣሪያዎ ላይ ለማውረድ ከተቸገሩ፣ ከታች ያሉትን የመላ ፍለጋ እርምጃዎች ይከተሉ።
የYouTube Premium አባልነትዎ ካበቃ እርስዎ ላወረዷቸው ቪድዮዎች መዳረሻ አይኖርዎትም።
የመላ ፍለጋ እርምጃዎች
ወደ YouTube Premium ዳግም በመለያ ለመግባት ይሞክሩ
ችግር፦ በመለያ ወደ YouTube Premium አልገቡም።
መፍትሔ፦ ከእርስዎ YouTube Premium አባልነት ጋር ወደተጎዳኘው መለያ እንደገቡ ያረጋግጡ።
- ከYouTube Premium ጋር ከተጎዳኘው መለያ ዘግተው ለመውጣት እና መልሰው ለመግባት ይሞክሩ።
- በYouTube ውስጥ የYouTube Premium ዓርማ (ከYouTube አርማ ይልቅ) ማየትዎን ያረጋግጡ።
የአባልነት ሁኔታዎን ይፈትሹ
ችግር፦ የእርስዎ YouTube Premium አባልነት ጊዜው አልፎበት ሊሆን ይችላል።
መፍትሔ፦ የYouTube Premium አባልነትዎ ጊዜው ያላለፈበት መሆኑን ያረጋግጡ።
በYouTube መተግበሪያው ውስጥ፣ የእርስዎ የመገለጫ ፎቶ ቅንብሮች
ግዢዎች እና አባልነቶች ላይ መታ ያድርጉ።
- በቅርቡ የYouTube Premium መዳረሻዎን ካጡ እና በድጋሚ ለደንበኝነት ተመዝግበው ከሆነ፣ እንደገና ለደንበኝነት ከተመዘገቡ በኋላ የተቀመጡ ቪድዮዎች እስኪታዩ ድረስ ጥቂት ሰዓታትን ይወስዳል።
- አንድን ቪድዮ ወዲያው ማየት ካለብዎት ምናሌ
ላይ መታ ያድርጉ እና እንደገና ለማውረድ ሞክር የሚለውን ይምረጡ።
- የYouTube Premium አባልነትዎ ካበቃ እርስዎ ላወረዷቸው ቪድዮዎች መዳረሻ አይኖርዎትም። ለውርዶችዎ መዳረሻን ዳግም ለማግኘት ለPremium አባልነት ይመዝገቡ።
የበይነመረብ ግንኙነት ጥንካሬን ይፈትሹ
ችግር፦ ደካማ የበይነመረብ ግንኙነት ውርዶችን ሊያደናቅፍ ይችላል።
መፍትሔ፦ የቪድዮዎ ውርዶች ጠንካራ የበይነመረብ ግንኙነት ያስፈልጋቸዋል። መሣሪያዎ ከ3 ሜቢ/ሴ ወይም ከዚያ በላይ ፈጣን የሆነ አውታረ መረብ ጋር የተገናኘ መሆኑን ወይም 3ጂ፣ 4ጂ ወይም LTE ፍጥነቶችን ከሚደግፍ የተንቀሳቃሽ ስልክ አውታረ መረብ ጋር መገናኘቱን ያረጋግጡ። የአሁኑ የበይነመረብ ፍጥነትዎ ምን ያህል እንደሆነ እርገጠኛ ካልሆኑ መስመር ላይ ፍጥነትዎን መሞከር ይችላሉ።
የተንቀሳቃሽ ስልክ ውሂብ ይፈትሹ
ችግር፦ ተንቀሳቃሽ መሣሪያ እየተጠቀሙ ከሆነ የተንቀሳቃሽ ስልክ ውሂብ ገደብዎ ላይ ደርሰው ሊሆን ይችላል።
መፍትሔ፦ የተንቀሳቃሽ ስልክ ውሂብ እየተጠቀሙ ከሆነ፣ የውሂብ አጠቃቀምዎን ይፈትሹ። ገደብዎ ላይ ከደረሱ፣ ከWi-Fi ጋር መገናኘት ወይም ቪድዮዎችን ለማውረድ ተጨማሪ ውሂብ መግዛት ያስፈልግዎታል። ለYouTube የዳራ ውሂብን ማንቃትዎን ለማረጋገጥ በተንቀሳቃሽ መሣሪያዎ ላይ ቅንብሮቹን ይፈትሹ።
የውርድ መሣሪያ ገደብን ይፈትሹ
ችግር፦ በYouTube Premium ለማውረድ የሚፈቀደው ከፍተኛው የመሣሪያዎች ብዛት ላይ ደርሰው ሊሆን ይችላል።
መፍትሔ፦ ለውርዶች ምን ያህል መሣሪያዎችን እንደተጠቀሙ ይፈትሹ። ገደቡ ላይ ከደረሱ ውርዶችን ጥቅም ላይ ካልዋሉ መሣሪያዎች ላይ በማስወገድ ክፍተት ማስለቀቅ ያስፈልግዎታል። በYouTube Premium ላይ ስላሉ የመሣሪያ ገደቦች የበለጠ ይወቁ።