YouTube የእኔን ቪድዮዎች ወደ የግል ለወጠው?

በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ በሰርጥዎ ላይ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን ስናገኝ ቪድዮዎችን በሰርጎገብ የተጫኑ እንደሆኑ ካመንን ወደ የግል ለማቀናበር እርምጃ ልንወስድ እንችላለን። እነዚህን እርምጃዎች የምንወስደው የእርስዎን ሰርጥ እና ማህበረሰብ በተሻለ ሁኔታ ለመጠበቅ ነው።

ማናቸውም ቪድዮዎችዎን የግል ካደረግን በኢሜይል እናሳውቅዎታለን። በተጨማሪም እርስዎ እና የYouTube ማህበረሰባችን እንደተጠበቃችሁ ለማረጋገጥ ከመለያዎ እናስወጣዎታለን።

ምን ማድረግ አለብኝ?

ቪድዮዎቹን ካተሙ

እንደገና ይፋዊ ለማድረግ ወይም ላለማድረግ ከመወሰንዎ በፊት የግል ቪድዮዎችዎን ይመልከቱ። የእኛን የማህበረሰብ መመሪያዎች እንድሚከተሉ ካመኑ ቪድዮዎቹን ወደ ይፋዊ መለወጥ ይችላሉ።

ማስታወሻ፦ ቪድዮዎችዎን ወደ ይፋዊ መለወጥ ካልቻሉ ቪድዮዎ በሌላ ምክንያት የግል ተብሎ ምልክት ተደርጎበት ሊሆን ይችላል። ያልተገናኙ ወይም አሳሳች መለያዎችን በመጠቀም የግል ስለተደረጉ ቪድዮዎች የበለጠ ይወቁ

ቪድዮዎችን ካላተሙ

  1. studio.youtube.com የሚለውን ይጎብኙ እና ያልሰቀሏቸውን ማናቸውም ቪድዮዎችን ይሰርዙ። የግል ቪድዮዎች እንኳን የማህበረሰብ መመሪያዎችን መከተል አለባቸው እና እርስዎ ላለጠፉት ይዘት እንዲቀጡ አንፈልግም።
  2. በGoogle መለያዎ ላይ የደህንነት ፍተሻ ያከናውኑ እና ማናቸውም የሚመከሩ እርምጃዎችን ይውሰዱ። የሚመከሩ እርምጃዎች የእርስዎን የይለፍ ቃል መለወጥ ወይም የድሮ መሣሪዎችን ማስወገድን ያካትታሉ።
  3. ለሰርጥዎ ማን መዳረሻ እንዳለው ይገምግሙ። ከመለያዎ ጋር ተጓዳኝ የሆኑ ማናቸውም ያልተፈለጉ ተጠቃሚዎች አለመኖራቸውን ለማረጋገጥ የሰርጥ ፈቃዶችን ይፈትሹ።
  4. ሰርጎገብ በሰርጥዎ ላይ እንደ ባነር፣ በቪድዮ መግለጫዎች ውስጥ ያሉ አገናኞችን ወይም የተሰኩ አስተያየቶችን ያለ ሌላ ነገር እንደለወጠ ያረጋግጡ።

እንዴት መለያዎን ከሰርጎገቦች መጠበቅ እንደሚቻል በእኛ የፈጣሪ የደህንነት ማዕከል ወይም የYouTube መለያዎን ደህንነት ይጠብቁ የሚለውን በመጎብኘት የበለጠ ማወቅ ይችላሉ።

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
8016628706459789348
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
59
false
false