የተሳሳተ መረጃ መመሪያዎች

ከባድ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ የተወሰኑ አሳሳች ወይም አታላይ የይዘት ዓይነቶች YouTube ላይ አይፈቀዱም። ይህም ቴክኒካዊ በሆነ መንገድ ቅንብር የተደረገባቸው የተወሰኑ የይዘት ዓይነቶችን ወይም በዲሞክራሲያዊ ሂደት ጣልቃ የሚገባ ይዘትን በገሃዱ ዓለም ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ የተወሰኑ የተሳሳተ መረጃ ዓይነቶችን ያካትታል። በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ የሕዝብ ፍላጎት ውስጥ ያለ ይዘትን ጨምሮ ትምህርታዊ፣ ጥናታዊ፣ ሳይንሳዊ ወይም ጥበባዊ አውድ ላለው ይዘት ልዩ ሁኔታዎችን ልናደርግ እንችላለን።

ይህን መመሪያ የሚጥስ ይዘት ካገኙ፣ ሪፖርት ያድርጉት። የእኛን የማህበረሰብ መመሪያዎች ጥሰቶች ሪፖርት ለማድረግ መመሪያዎች እዚህ ይገኛሉ። ሪፖርት ማድረግ የሚፈልጓቸውን በርካታ ቪድዮዎች ወይም አስተያየቶች ካገኙ ሰርጡን ሪፖርት ያድርጉ

የምርጫ የተሳሳተ መረጃ መመሪያዎች

ይዘት እየለጠፉ ከሆነ

ከታች ካሉት መግለጫዎች ለማንኛቸውም የሚስማማ ከሆነ ይዘት በYouTube ላይ አይለጥፉ።

  • የሕዝብ ቆጠራ ተሳትፎን ማፈን፦የሕዝብ ቆጠራ ተሳታፊዎችን ስለ ሕዝብ ቆጠራው ጊዜ፣ ቦታ፣ ዘዴ ወይም የብቁነት መስፈርቶች ለማሳሳት ዒላማ ያደረገ ይዘት ወይም የሕዝብ ቆጠራ ተሳትፎን ቁሳዊ በሆነ መልኩ ተስፋ ሊያስቆርጡ የሚችሉ የሐሰት የይገባኛል ጥያቄዎች።
  • የተቀየረ ይዘት፦ ተጠቃሚዎችን በሚያሳስት መልኩ ቴክኒካዊ በሆነ መንገድ የተቀየረ ወይም የተለወጠ ይዘት (ብዙ ጊዜ ቅንጥቦችን ከዓውድ ውጭ ከመውሰድ ባለፈ) እና ከባድ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል የሚታሰብ ይዘት።
  • በስህተት የተጠቀሰ ይዘት፦ ካለፈ ክስተት የሆነ የድሮ ቀረጻን የአሁን ክስተስ ነው ብሎ በሐሰት በመናገር ለከባድ ጉዳት ከፍተኛ ስጋትን ሊያስከትል የሚችል ይዘት።

ምሳሌዎች

በYouTube ላይ ያልተፈቀዱ አንዳንድ የይዘት ምሳሌዎች እነሆ።

የቆጠራ ተሳትፎን ማፈን
  • በቆጠራው መሳተፍ በሚቻልበት መንገድ ላይ የተሳሳተ መመሪያ መስጠት።
  • የምላሽ ሰጪው የኢሚግሬሽን ሁኔታ ለሕግ አስከባሪ አካላት ሪፖርት እንደሚደረግ በሐሰት በመናገር በቆጠራው ውስጥ መሳተፍን አለማበረታታት።
የተጭበረበረ ይዘት
  • ለከባድ ጉድት ከፍተኛ ስጋትን የሚፈጥሩ የጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶችን የሚያባብሱ በትክክል ያልተተረጎሙ የቪድዮ የግርጌ ጽሁፎች።
  • የመንግሥት ሹም እንደሞተ ለማስመል (ቅንጥቦችን ከዓውድ ውጭ ከመውሰድ ባለፈ) ቴክኒዊ በሆነ መንገድ የተቀየሩ ቪድዮዎች።
  • ለከባድ ጉድት ከፍተኛ ስጋት ባለበት ክስተቶችን ለመፍጠር (ቅንጥቦችን ከዓውድ ውጭ ከመውሰድ ባለፈ) ቴክኒካዊ በሆነ መልኩ የተቀየረ የቪድዮ ይዘት።
በስህተት የተጠቀሰ ይዘት
  • ይዘቱ ከሌላ አካባቢ ወይም ክስተት የተገኘ ቢሆንም በተለየ ቦታ ላይ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች እንደሆነ ተደርጎ ተዘግቦ ቀርቧል።
  • ቀረጻው በእርግጥ ብዙ አመታትን ያስቆጠረ ከሆነ ይዘቱ አሁን የነበረ ክስተት ነው በሚል በተቃዋሚዎች ላይ ወታደራዊ እርምጃን ከሐሰት የይገባኛል ጥያቄ ጋር የሚያሳይ ይዘት።

እነዚህ አንዳንድ ምሳሌዎች መሆናቸውን ያስታውሱ እና እነዚህን መመሪያዎች ሊጥስ ይችላል ብለው ካሰቡ ይዘትን አይለጥፉ። እባክዎ እነዚህ መመሪያዎች በይዘትዎ ውስጥ ባሉትውጫዊ አገናኞች ላይም እንደሚተገበሩ ልብ ይበሉ። ይህ ጠቅ ሊደረጉ የሚችሉ ዩአርኤሎችን፣ በቪድዮ ውስጥ ተጠቃሚዎችን በቃል ወደ ሌሎች ጣቢያዎች መምራትን እንዲሁም ሌሎች አካሄዶችን ሊያካትት ይችላል።

ትምህርታዊ፣ ጥናታዊ፣ ሳይንሳዊ ወይም ጥበባዊ ይዘት

ይህ ይዘት በቪድዮ፣ ኦዲዮ፣ ርዕስ ወይም መግለጫ ላይ ተጨማሪ አውድ የሚያካትት ከሆነ በዚህ ገጽ ላይ የተገለጹትን የተሳሳቱ የመረጃ መመሪያዎችን የሚጥስ ይዘትን ልንፈቅድ እንችላለን። እንዲሁም እንደ የኮንግረሱ ወይም የፓርላማ ሂደቶች፣ የዘመቻ ንግግሮች ወይም በመንግሥት ድርጊቶች ላይ የሚደረጉ ክርክሮች ያሉ የሕዝብ ፍላጎት ላለው ይዘት ልዩ ሁኔታዎችን ልናደርግ እንችላለን። ይህ የተሳሳተ መረጃን ለማስተዋወቅ ማሳለፊያ አይደለም። የይዘቱ ዓላማ መመሪያዎቻችንን የሚጥስ የተሳሳተ መረጃን ለመውቀስ፣ ለመሞገት ወይም ለመከላከል ከሆነ ለየት ያሉ ነገሮችን ልናደርግ እንችላለን።

እንዲሁም ከላይ የተዘረዘሩትን ማናቸውም መመሪያዎች እስካልጣሱ ድረስ ከላይ ባሉት ርዕሶች ላይ ግላዊ የአመለካከት አገላለጾችን እንፈቅዳለን።

ይዘት ይህን መመሪያ የሚጥስ ከሆነ ምን ይከሰታል

የእርስዎ ይዘት ይህን መመሪያ የሚጥስ ከሆነ ይዘቱን እናስወግደዋለን እና ለእርስዎ ለማሳወቅ ኢሜይል እንልክልዎታለን። የሚለጥፉት አገናኝ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ካልቻልን አገናኙን ልናስወግደው እንችላለን።

የማህበረሰብ መመሪያዎቻችንን ሲጥሱ የመጀመሪያ ጊዜዎ ከሆነ በሰርጥዎ ላይ ምንም ዓይነት ቅጣት የሌለው ማስጠንቀቂያ ሊደርስዎ ይችላል። ማስጠንቀቂያው በ90 ቀናት ውስጥ ጊዜው እንዲያልፍ ለመፍቀድ የመመሪያ ሥልጠና የመውሰድ አማራጩ ይኖርዎታል። የ90 ቀን ጊዜ የሚጀምረው ሥልጠናው ከተጠናቀቀ በኋላ እንጂ ማስጠንቀቂያው ሲሰጥ አይደለም። ይሁን እንጂ በዚያ 90 ቀን መስኮት ውስጥ ተመሳሳይ መመሪያ ከተጣሰ ማስጠንቀቂያው ጊዜው ላያልፍ ይችላል እና ሰርጥዎ ምልክት ሊሰጠው ይችላል። ሥልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላ የተለየ መመሪያ ከጣሱ ሌላ ማስጠንቀቂያ ያገኛሉ።

በ90 ቀናት ውስጥ 3 ምልክቶች ካገኙ ሰርጥዎ ሊቋረጥ ይችላል። ስለ የእኛ የምልክቶች ሥርዓት እዚህ የበለጠ ማወቅ ይችላሉ።

በማህበረሰብ መመሪያዎችን ወይም በአገልግሎት ውሉ ተደጋጋሚ ጥሰቶች ምክንያት ሰርጥዎን ወይም መለያዎን ልናቋርጥ እንችላለን። እንዲሁም አንድ ጊዜ ከባድ አላግባብ የመጠቀም ጉዳይ ከተከሰተ በኋላ ወይም ሰርጡ ለመመሪያ ጥሰት ሥራ ላይ ሲውል የእርስዎን ሰርጥ ወይም መለያ ልናቋርጥ እንችላለን። ስለ የሰርጥ ወይም የመለያ መቋረጦች እዚህ ተጨማሪ ማወቅ ይችላሉ።

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?

ተጨማሪ እገዛ ያስፈልግሃል?

እነዚህን ቀጣይ እርምጃዎች ይሞክሩ፦

ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ
13955760134175194396
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
false
true
true
true
true
true
59
false
false
false
false