YouTube ላይ ክትትል ለሚደረግባቸው የልጅ መለያዎች የይዘት ቅንብሮችን ይምረጡ

የልጃቸውን የYouTube ጉዞ እንዲመሩ ለወላጆች ምርጫዎችን እንሰጣለን፣ ይህም ክትትል የሚደረግበት የልጅ መለያቸውን ሲያዋቅሩ የይዘት ቅንብርን መምረጥን ያካትታል። የይዘት ቅንብሮች ልጅዎ ምን እና ምን ያህል ይዘት እንደሚመለከቱ ይወስናሉ። የይዘት ቅንብር ከመረጡ በኋላም በማንኛውም ጊዜ ሊለውጡት ይችላሉ

ክትትል የሚደረግባቸው ተሞክሮዎችን ለሚጠቀሙ ቤተሰቦች የይዘት ቅንብሮች

የቅርብ ጊዜ ዜና፣ ዝማኔዎች እና ጠቃሚ ምክሮችን ለማግኘት ለYouTube የተመልካቾች ሰርጥ በደንበኝነት ይመዝገቡ።

እርስዎ በመረጡት የይዘት ቅንብር በመመስረት ልጅዎ በቪድዮዎች ላይ ያሉ አስተያየቶችን ማንበብም ይችላሉ።

የይዘት ቅንብሮች እንዴት እንደሚሠሩ

YouTube በይዘት ተገቢነት ላይ በአጠቃላይ ከቲቪ እና ከፊልም የይዘት ደረጃ አሰጣጦች ጋር የሚጣጣሙ የመመሪያዎች ስብስብን አዘጋጅቷል። እነዚህ መመሪያዎች በይዘት ቅንብራቸው መሠረት ልጅዎ የትኛዎቹን ቪድዮዎች ማየት እንደሚችሉ ለመምራት ያግዛሉ።

የእኛ ራስ-ሰር የተደረጉ ሥርዓቶች በይዘት መመሪያዎቻችን መሠረት እያንዳንዱ የይዘት ቅንብር ውስጥ ለመካተት ተስማሚ የሆኑ ቪድዮዎችን ይለያሉ። ሥርዓቶቻችን ፍፁም እንዳልሆኑ እና እንደሚሳሳቱ እናውቃለን። ሥርዓቶቻችንን ያለማቋረጥ ለማሻሻል በአጋርነት የሚሠሩ የመሐንዲሶች እና የሰው ገምጋሚዎች ቡድን አለን። ለYouTube አግባብ አይደለም ብለው የሚያምኑት ነገር ካገኙሪፖርት ሊያደርጉት ይችላሉ።

እርስዎ በመረጡት የይዘት ቅንብር በመመስረት ልጅዎ በቪድዮዎች ላይ ያሉ አስተያየቶችን ማንበብም ይችላሉ።

የይዘት ቅንብር አማራጮች

ያስሱ በአጠቃላይ 9+ ከሆኑ ተመልካቾች የይዘት ደረጃ አሰጣጦች ጋር ይዛመዳል
ተጨማሪ ያስሱ በአጠቃላይ 13+ ከሆኑ ተመልካቾች የይዘት ደረጃ አሰጣጦች ጋር ይዛመዳል
አብዛኛው YouTube እንደ 18+ ምልክት ከተደረገበት ይዘት እና ሌሎች ክትትል የሚደረግባቸው መለያዎችን ለሚጠቀሙ ተመልካቾች ተገቢ ላይሆኑ ከሚችሉ ቪድዮዎች በስተቀር በYouTube ላይ ያሉ ሁሉም ቪድዮዎች

የይዘት መመሪያዎች

የእኛ የይዘት መመሪያዎች በይዘት ቅንብሮች መካከል ይለያያሉ እና ልጅዎ ምን ዓይነት ቪድዮዎች መመልከት እንደሚችል ይወስናሉ። እነዚህን መመሪያዎች በየጊዜው እንደገና እንገመግማለን፣ ስለዚህ ከታች ያሉት መግለጫዎች ሁሉንም ላያካትቱ ይችላሉ።

ያስሱ

«አሰሳ» ከYouTube Kids ለመቀጠል እና በYouTube ላይ ያለውን በጣም ትልቅ የሆነውን የይዘት ዓለም ለማሰስ ዝግጁ ለሆኑ ቤተሰቦች ነው። ይህ ቅንብር በአጠቃላይ 9+ ከሆኑ ተመልካቾች የይዘት ደረጃ አሰጣጥ ጋር የሚዛመዱ ሰፋ ያሉ ቪድዮዎችን ያሳያል። ቪድዮዎች ቪጦማሮችን፣ አጋዥ ሥልጠናዎችን፣ የጨዋታ ቪድዮዎችን፣ የሙዚቃ ቪድዮዎችን፣ ዜናን፣ ትምህርታዊ ይዘቶችን፣ ራስዎ ይስሩትን፣ ሥነ ጥበባት እና ዕደ ጥበባትን፣ ዳንስን እና ተጨማሪ ነገሮችን ያካትታሉ። አንዳንድ ቪድዮዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

የጎልማሳ ይዘት፦ የፍቅር እና የመሳሳብ መለስተኛ ማሳያዎችን ጨምሮ የፍቅር ገጽታዎች ያሏቸው ቪድዮዎች። በወሲባዊ እና በፆታ ማንነት እንዲሁም እንደ ጉርምስና እና ስነ ተዋልዶ ባሉ የወሲብ ትምህርት ርዕሶች ላይ ለዕድሜ አግባብ የሆኑ ትምህርታዊ ቪድዮዎች።

ጥቃት:- ከአሁን ወይም ከታሪካዊ ክስተቶች ጋር የተያያዙ ለዕድሜ አግባብ የሆኑ ነገር ግን በክስተቱ አውድ ውስጥ መለስተኛ ጥቃትን ሊይዙ የሚችሉ ትምህርታዊ ቪድዮዎች። በካርቱኖች፣ በጨዋታ፣ በቴሌቪዥን ትዕይንቶች እና በፊልሞች ውስጥ የተለመዱ ስክሪፕት የተደረጉ እና የታነሙ ቪድዮዎች ላይ ግራፊክ ያልሆነ ጥቃት።

የጦር መሣሪያዎች፦ በአሻንጉሊት ጨዋታ፣ በጨዋታ፣ በእነማ እና በታሪካዊ አውድ ውስጥ ባሉ ሥነ ጥበባዊ የጦር መሣሪያዎች አውድ ውስጥ ከእውነታው የራቁ የጦር መሣሪያዎችን የሚያሳዩ ቪድዮዎች።

አደገኛ ይዘት፦ እንደ አስደናቂ ትርዒቶች፣ የሽወዳ ጨዋታዎች እና ተግዳሮቶች ያሉ ለአካለ መጠን ባልደረሱ በቀላሉ ሊደረጉ የማይችሉ ወይም ከተገቢ የደህንነት መግለጫዎች ጋር የጎላ ማሳሰሰቢያን የሚያካትቱ አደገኛ ድርጊቶችን የሚያሳዩ ቪድዮዎች። አልኮል ወይም ትምባሆን በአጭሩ የሚያሳዩ ቪድዮዎች።

አግባብ ያልሆነ ቋንቋ፦ እንደ «ሲያናድድ» ወይም «ገሃነም» ያሉ ትንኮሳ በሌለበት አውድ ውስጥ ተደጋጋሚ ያልሆነ መለስተኛ አጸያፊ ቋንቋን የሚጠቀሙ ቪድዮዎች።

አመጋገብ፣ አካል ብቃት እና ውበት፦ የውበት ምርት ግምገማዎችን፣ ለዕድሜ አግባብ የሆኑ የመዋቢያ አጋዥ ሥልጠናዎችን እና በጤና ላይ ትምህርታዊ ይዘቶችን የሚያሳዩ ቪድዮዎች። ይህ ይዘት ጤናማ አመጋገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ያካትታል።

ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ርዕሶች፦ እንደ የአዕምሮ ጤንነት፣ ሱስ፣ የአመጋገብ መዛባቶች እና የሚወዱትን ማጣት እና ሀዘን ያሉ ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ችግሮች ላይ የሚወያዩ ለዕድሜ አግባብ የሆኑ ቪድዮዎች። በዚህ ቅንብር ውስጥ ያሉ ቪድዮዎች አደገኛ የሆነ ምስል አያካትቱም እና በአዎንታዊ መቋቋም እና የመልሶ ማግኛ ስልቶች እና እርዳታን የመፈለግ ጥቅም ላይ ያተኩራሉ።

የሙዚቃ ቪድዮዎች፦ የሙዚቃ ቪድዮዎች መለስተኛ አፀያፊ ቋንቋ ያላቸው ግጥሞችን ወይም የአልኮል ወይም የትምባሆ መጠቀሶችን ሊያካትቱ ይችላሉ። አንዲሁም ቪድዮዎች አላስፈላጊ የወሲብ ዳንስ እና ሳይደጋገም አልኮል ወይም ትምባሆ ሊያሳዩ ይችላሉ።

ተጨማሪ ያስሱ

«የበለጠ አስስ» የYouTube ሰፊውን ዓለም የበለጠ ለማሰስ ዝግጁ ለሆኑ ልጆች ነው። ይህ ቅንብር በአሰሳ ውስጥ ያለውን ሁሉንም ነገር እና በአጠቃላይ 13+ ለሆኑ ተመልካቾች የይዘት ደረጃዎች ጋር የሚጣጣሙ ሰፋ ያሉ ቪድዮዎችን ያካትታል። ቪድዮዎች የቀጥታ ዥረቶችን፣ ቪጦማሮችን፣ አጋዥ ሥልጠናዎችን፣ የጨዋታ ቪድዮዎችን፣ ዜናን፣ ትምህርታዊ ቪድዮዎችን፣ ራስዎ ይስሩትን፣ ሥነ ጥበባት እና ዕደ ጥበባትን፣ ዳንስን እና ተጨማሪ ነገሮችን ያካትታሉ። አንዳንድ ቪድዮዎች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ፦

የጎልማሳ ይዘት፦ እንደ የወሲባዊ ተሞክሮዎች ልቅ ያልሆኑ መለያዎች ያሉ እና የአካል ንክኪ የሚያሳዩ ወሲባዊ ገጽታዎች ያሏቸው ቪድዮዎች። እንደ ወሲባዊ እድገት፣ የሥነ ተዋልዶ ጤና፣ መታቀብ እና በሽታ መከላከል ባሉ የወሲብ ትምህርት ርዕሶች እና የወሲብ እና የፆታ ማንነት ላይ ትምህርታዊ ቪድዮዎች።

ጥቃት፦ ከአሁን ወይም ከታሪካዊ ክስተቶች ጋር የሚዛመዱ ግልጽ ያልሆኑ ትምህርታዊ ቪድዮዎች። በጨዋታ፣ በቴሌቭዥን ትዕይንቶች እና በፊልሞች ውስጥ የተለመደ በተደረሱ እና በታነሙ ቪድዮዎች ውስጥ ያለ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ግልጽ ጥቃት።

የጦር መሣሪያዎች፦ በቴሌቪዥን ትዕይንቶች እና ፊልሞች ላይ በተለመዱ የተደረሱ ቪድዮዎች ውስጥ የእውነት እና እውነታዊ የጦር መሣሪያዎችን የሚያሳዩ ቪድዮዎች። በስፖርት ወይም በሽጉጥ ደህንነት ትምህርታዊ አውድ ላይ እውነተኛ ሽጉጦች ጥቅም ላይ ሲውሉ የሚያሳይ ቪድዮ።

አደገኛ ይዘት፦ እንደ አስደናቂ ትርዒቶች፣ የሽወዳ ጨዋታዎች እና ተግዳሮቶች ያሉ አደገኛ የአካል ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ነገር ግን ለአካለ መጠን ባልደረሱ በቀላሉ ሊደረጉ የማይችሉ አደገኛ ድርጊቶችን የሚያሳዩ ቪድዮዎች። ተደጋጋሚ የአልኮል ወይም የትምባሆ አጠቃቀምን የሚያሳዩ ቪድዮዎች።

አግባብ ያልሆነ ቋንቋ፦ ትንኮሳ በሌለበት ወይም ወሲባዊ ባልሆነ አውድ ውስጥ እንደ «ውሻ» ወይም «አህያ» ያሉ አጸያፊ ቋንቋዎችን ወይም ጸያፍ ይዘት በተደጋጋሚ የሚጠቀሙ ቪድዮዎች። ተደጋጋሚ ካልሆነ እና ትንኮሳ በሌለበት አውድ ውስጥ ጥቅም ላይ ከዋሉ የስድብ ዘለፋዎች በጥብቅ ትምህርታዊ ወይም የሙዚቃ ቪድዮ አውድ ውስጥ ሊታዩ ይችላሉ።

አመጋገብ፣ የአካል ብቃት እና ውበት፦ የመዋቢያ አጋዥ ሥልጠናዎችን፣ የውበት ጠቃሚ ምክሮችን እና በህይወት ላይ ለውጥ የሚያመጡ አዳዲስ ሃሳቦችን እና ከጤናማ አመጋገብ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጋር የተያያዙ ቪድዮዎችን የሚያሳዩ ቪድዮዎች።

አደገኛ ርዕሶች፦ እንደ የአዕምሮ ጤንነት፣ ራስን ለማጥፋት ማሰብ፣ ራስን መጉዳት፣ ሱስ፣ የአመጋገብ መዛባት፣ የሚወዱትን ማጣት እና ሃዘን ካሉ አደገኛ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ግልጽ ያልሆኑ ቪድዮዎች። እነዚህ ቪድዮዎች በአዎንታዊ የመቋቋሚያ እና የማገገሚያ ስልቶች እና እርዳታ የመፈለግ አሰፈላጊነት ላይ ያተኩራሉ።

የሙዚቃ ቪድዮዎች፦ የሙዚቃ ቪድዮዎች ትንኮሳ ወይም ጥላቻ በሌለበት አውድ ውስጥ ከወሲባዊ ማጣቀሻዎች ጋር የተያያዙ ግጥሞችን፣ ተደጋጋሚ ያልሆነ ግልፅ ጸያፍ ይዘትን ወይም የሚያንቋሽሹ ስድቦችን ሊያካትቱ ይችላሉ። ቪድዮዎች ወሲባዊ ዳንስ እና አልኮል፣ ትምባሆ ወይም ማሪዋና መጠቀምን ሊያሳዩ ይችላሉ።

እንዲሁም በዚህ የይዘት ቅንብር ውስጥ ቪድዮዎች ላይ ልጅዎ አስተያየቶችን ማንበብ ይችላሉ፣ ነገር ግን መጻፍ አይችሉም።

አብዛኛው YouTube
«አብዛኛው YouTube» ለትልልቅ ታዳጊዎች ይዘትን ጨምሮ ሰፊውን የYouTube ዓለም ለማሰስ ዝግጁ ለሆኑ ልጆች ነው። ይህ ቅንብር እንደ 18+ ምልክት የተደረገባቸው ቪድዮዎች እና ሌሎች ክትትል የሚደረግባቸው መለያዎችን ለሚጠቀሙ ተመልካቾች አግባብ ላይሆኑ ከሚችሉ ቪድዮዎች በስተቀር በYouTube ላይ ያለ ሁሉንም ነገር ያካትታል። ቪድዮዎች የቀጥታ ዥረቶችን፣ ቪጦማሮችን፣ አጋዥ ሥልጠናዎችን፣ የጨዋታ ቪድዮዎችን፣ ዜናን፣ ትምህርታዊ ቪድዮዎችን፣ ራስዎ ይስሩትን፣ ሥነ ጥበባትን እና ዕደ ጥበባትን፣ ዳንስ እና ተጨማሪ ነገሮችን ያካትታሉ።
እንዲሁም በዚህ የይዘት ቅንብር ውስጥ ቪድዮዎች ላይ ልጅዎ አስተያየቶችን ማንበብ ይችላሉ፣ ነገር ግን መጻፍ አይችሉም።

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?

ተጨማሪ እገዛ ያስፈልግሃል?

እነዚህን ቀጣይ እርምጃዎች ይሞክሩ፦

ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
Google መተግበሪያዎች
ዋናው ምናሌ
10224751320338494805
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
false
true
true
true
true
true
59
false
false
false
false
false