የበረራ ዋጋዎችን በቦርሳ ክፍያ ያጣሩ

የቦርሳ ክፍያዎችን ያካተተ የበረራ ዋጋ ያሳዩ

ጠቃሚ፦ Google ከአጋሮቻችን ያገኘነውን የሻንጣ መረሻ ያሳያል። የሚታዩት ማናቸውም ግምታዊ የቦርሳ ክፍያዎች ተጨማሪ የመንግስት ግብር ሊጨመርባቸው ይችላል።

የቦርሳዎች ማጣሪያ የተፈተሹ ቦርሳዎችን ወይም በእጅ የሚያዙ ቦርሳዎችን ዋጋዎች እንዲያሳዩ ያስችልዎታል። ይህ ዋጋዎችን በተሻለ ሁኔታ እንዲያወዳድሩ እና በአየር ማረፊያው የሚከሰቱ ያልተጠበቁ ወጪዎችን እንዲያስወግዱ ሊያግዝዎት ይችላል። 

ከመጀመርዎ በፊት

ቦርሳዎች በሁሉም ቅርጾች እና መጠኖች ውስጥ ይመጣሉ ፣ ነገር ግን አየር መንገዶች አብዛኛውን ጊዜ በእጅ የሚያዝ እና የተፈተሹ በርሳዎች በማለት ይከፋፍሏቸዋል።

የሻንጣ ዓይነት

ምን ተብሎ ይጠራል

የሚቀመጥበት ቦታ

በእጅ የሚያዝ

በእጅ የሚያዝ ቦርሳ፣ የእጅ ሻንጣ፣ የሽርሽር ሻንጣ፣ ባለ ጎማ ሻንጣዎች፣ ተሽከርካሪ ሻንጣዎች

የራስጌ እቃ ማስቀመጫ ውስጥ

የተፈተሹ ሻንጣዎች

የተፈተሹ ሻንጣዎች

እቃ መጫኛ ውስጥ

በእጅ የሚያዝ ሻንጣ ክፍያ በአገር ይለያያል። በተጨማሪም፣ ምን በእጅ የሚያዝ ሻንጣ እንደሆነ መስፈርት የሚያሟላው እንደ አየር መንገዱ ይለያያል። ለእያንዳንዱ የጓዝ ዓይነት የተለዩ የመጠን ገደቦችን፣ የክብደት ገደቦችን እና ዋጋዎችን ለማግኘት፣ የአየር መንገዱን የሻንጣ ክፍያዎች እና መመሪያዎች ገፅን ይመልከቱ።

የቦርሳዎች ማጣሪያን ይጠቀሙ

በረራዎችን ሲፈልጉ፣ ሻንጣዎችን ይዘው ለመሳፈር ወይም አስፈትሸው ማስጫን እንደሚፈልጉ አስቀድመው አውቀው ሊሆን ይችላል። የሚያውቁ ከሆነ፣ ለእያንዳንዱ የተፈተሸ ሻንጣ ወይም በራስጌ እቃ ማስቀመጫ ውስጥ ማስቀመጥን ያካተተ በረራ ዋጋ ለማሳየት የሻንጣዎች ማጣሪያ በGoogle በረራዎች ላይ ሊጠቀሙ ይችላሉ።

የሻንጣዎች ማጣሪያውን ማብራት ማንኛውንም በረራ ከውጤቶቹ ውስጥ ማስወገድ የለበትም—ዋጋዎቹን ማዘመን ብቻ ነው ያለበት። ልዩ ሁኔታ ማለት በተወሰኑ በረራዎች ላይ የቀሩ ብቸኛ መቀመጫዎች የራስጌ እቃ ማስቀመጫ መዳረሻ የማያካትቱ ከሆነ ማለት ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ቦርሳዎን ማስፈተሽ በእጅ ለመያዝ ከመክፈል ይልቅ እርካሽ ሊሆን ይችላል። 

ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
16496406856310403728
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
254
false
false