በረራዎችን እና ዋጋዎችን ይከታተሉ

ለጉዞ ቦታ ለማስያዝ ዝግጁ ካልሆኑ፣ የተወሰኑ በረራዎች፣ መስመሮች እና ቀናትን መነሻ በማረግ ዋጋዎችን ለመከታተል በGoogle በረራዎች መጠቀም ይችላሉ።

የመስመር ወይም የበረራ ዋጋዎችን ይከታተሉ

እየተከታተሉት ያለ በረራ ወይም መስመር ዋጋ ጉልህ በሆነ መጠን ሲቀየር፣ የኢሜይል እና የሞባይል ማሳወቂያዎችን ማግኘት ይችላሉ።

  1. ወደ Google በረራዎች ይሂዱ።
  2. የማቆሚያዎች ብዛት፣ የጋቢና ክፍል እና ስንት ትኬቶች እንደሚፈልጉ ለመምረጥ ከላይ ያለውን አዝራር ይጠቀሙ።
  3. አየር መንገድ መነሻዎን እና ማረፊያዎን ይምረጡ።
  4. የበረራ ቀናትዎን ለመምረጥ፣ የቀን መቁጠሪያን መታ ያድርጉ።
  5. በዚህ መስመር ዋጋዎችን ለመከታተል፣ ዋጋዎችን ይከታተሉ
    • ፍለጋ ለተደረገባቸው ቀኖች ወይም የጉዞ ቀናትዎ ሊለዋወጡ የሚችሉ ከሆኑ፣ «ማናቸውንም ቀናት» መከታተል ይችላሉ።
  6. የግድ ያልሆነ፦ የተመረጠውን በረራ ዋጋ ለመከታተል፣ በረራዎን ይምረጡ፣ ከዚያም ዋጋዎችን ይከታተሉ የሚለውን መታ ያድርጉ።
«ማናቸውንም ቀናት» ሲከታተሉ፣ የመስመሩ ዝቅተኛ ዋጋ በወር ውስጥ ጉልህ በሆነ መጠን ሲቀንስ ኢሜይል ይደርስዎታል። በበቂ መጠን አነስተኛ የዋጋ መውረድ ከሌለ፣ የሚገኙትን የተሻሉ የበረራ ዋጋዎች ያካተቱ መደበኛ ኢሜይሎችን ያገኛሉ።

ክትትል የሚደረግባቸው በረራዎችን ያግኙ ወይም ኢሜሎችን ያጥፉ

  1. ወደ Google በረራዎች ይሂዱ።
  2. ከላይ በግራ በኩል፣ ምናሌ እና በመቀጠል ክትትል የሚደረግባቸው ዋጋዎች ምናሌ ላይ መታ ያድርጉ።
    • የሚከታተሏቸውን በረራዎች ለማግኘት፣ የተቀመጠ አቅጣጫ መታ ያድርጉ።
    • የክትትል ኢሜይሎችን ለማብራት ወይም ለማጥፋት፣ ማሳወቂያዎችን ያክሉ  ላይ መታ ያድርጉ።
  3. የግድ ያልሆነ፦ አንድን መስመር ወይም በረራ መከታተልን ለማቆም፣ ያስወግዱ Remove ላይ መታ ያድርጉ።

ስለ የዋጋ ለውጦች ግንዛቤዎችን ያግኙ

በተጨማሪም የሚከተሉት ሁኔታዎች ሲፈጠሩ በGoogle በረራዎች ውስጥ ማሳወቂያዎችን፣ የኢሜይል ወይም የሞባይል ማሳወቂያዎችን ማግኘት ይችላሉ፦

  • እየተከታተሉት ያለ መስመር ዋጋ ሊያሻቅብ የሚችልበት ዕድል ሲኖር።
  • የበረራ አሁናዊ ታሪፍ በቅርቡ ጊዜው የሚያልፍበት ሲሆን እና አዲሱ ዋጋ ተጨማሪ የማስወጣት ዕድል ሲኖረው።

ይህ ምን ያህል ዋጋዎች እንደሚጨምሩ ያለንን ግምት እና በእያንዳንዱ ግምት ላይ ያለን እርግጠኛነት ያካትታል።

ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
4816907932662725125
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
254
false
false