የበረራ እና የቦታ ማስያዝ አማራጮችዎን ይረዱ

የአየር ጉዞ ውስብስብ ነው። Google በረራዎች እርስዎ እንዴት መድረሻዎ ጋር መድረስ እንደሚችሉ እና ቲኬትዎን እንደሚገዙ እንዲወስኑ ለማገዝ ከ300 በላይ የአየር መንገዶች፣ የመስመር ላይ ጉዞ ወኪሎች እና አዋሃጆች ጋር አጋር ነው።  ይህን ውሳኔ ለመወሰን የሚያስፈልገዎትን ነገር እንዲኖረዎት እንፈልጋለን፣ እና ይህን ለማድረግ ብዙ መረጃ ከአጋሮቻችን እናጋራለን። በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ይህ በርካታ የአየር መንገዶችን ወይም ሌሎች ህጋዊ አካላትን ለአንዲት በረራ ወይም ክፍል መዘርዘር ማለት ሊሆን ይችላል፤ በሌሎች ሁኔታዎች ላይ ደግሞ የእርስዎ የቦታ ማስያዝ አማራጮችዎ እርስዎ የጠበቁት ላይሆን ይችላል። የበረራ ፍለጋ ተሞክሮዎን እንዲዳስሱ ለማገዝ ጥቂት ማወቅ ያሉብዎት ነገሮች እነሆ፦

  • የኮድ ማጋራቶች፦ ብዙ የአየር መንገዶች ከሌሎች የአየር መንገዶች ጋር የኮድ ማጋራት ስምምነቶች ውስጥ ይገባሉ፣ ይህም በርካታ የአየር መንገዶች ቲኬቶችን በአንዲት አውሮፕላን ላይ እንዲሸጡ ያስችላቸዋል። አውሮፕላኑን የሚያበራው ትክክለኛው የአየር መንገድ «ከዋኝ አገልግሎት አቅራቢ» የሚባለው ሲሆን በአውሮፕላኑ ላይ መቀመጫዎችን የሚሸጥ ሌላ ማንኛውም የአየር መንገድ «የአሻሻጭ አገልግሎት አቅራቢ» ነው የሚባለው። በGoogle ላይ በረራዎችን ሲፈልጉ ወደ የማንኛውም በረራ ዝርዝር እይታ ጠቅ አድርገው በመግባት ስለገበያ ስራ እና ከዋኝ አገልግሎት አቅራቢዎች ያለ መረጃን ማግኘት ይችላሉ። የኮድ ማጋራት ስምምነቶች በዚህ ጽሑፍ፦ «ቲኬቶች እንዲሁም የሚሸጡት በ…» ይመላከታሉ፣ ይህም የተመረጠው የጉዞ ዕቅድ የአሻሻጭ አገልግሎት አቅራቢዎቹን ያመለክታል።  
  • በይነመስመሮች፦ የአየር መንገዶች እንዲሁም ከሌሎች አየር መንገዶች ጋር የበይነመስመር ስምምነቶች መግባት ይችላሉ፣ ይህም ሸማች በአንድ አየር መንገድ በኩል በሁለት ወይም ተጨማሪ የአየር መንገዶች ላይ የሚያካትት አንዲት የጉዞ ዕቅድ እንዲያስመዘግብ ያስችለዋል። የእርስዎ የበረራ ፍለጋ ውጤቶች በእያንዳንዱ የጉዞ ዕቅድ ላይ በርካታ የአየር መንገዶችን የሚያካትት ከሆነ በእያንዳንዱ የአየር መንገድ በኩል ለይተው ቦታ ማስያዝ ሳያስፈልገዎት የበይነመስመር ስምምነት እያዩ ሳይሆን አይቀርም።
  • «ምናባዊ በይነመስመሮች»፦ ማንባዊ በይነመስመር የኮድ ማጋራት ወይም የበይነመስመር ስምምነት ሳይኖር የአገልግሎት አቅራቢዎች በረራዎች ጥምረት ነው። እንዲሁም የራስ-ማስተላለፍ ክፍያዎች በመባል የሚታወቁ ምናባዊ በይነመስመሮች በአጠቃላይ ተጓዦች በቆይታ ጊዜ ሻንጣቸውን እንዲሰበስቡ እና ደግመው እንዲፈትሹ፣ ወደ እያንዳንዱ በረራ ተመዝግበው እንዲገቡ እና በአየር መንገዶች መካከል ያለውን የተግባቦት ጥቅሞችን እንዲተዉ ይፈልጉባቸዋል፣ ነገር ግን እነዚህ ጥምረቶች እንዲሁም የበረራ አማራጮችዎን ሊጨምሩ ወይም አነስተኛ ዋጋዎችን ሊያቀርቡ ይችላሉ። አንዳንድ የGoogle የመስመር ላይ ጉዞ ወኪል አጋሮች ምናባዊ በይነመስመሮችን የማስያዝ አማራጭ ያቀርባሉ፣ እነዚህንም «አብረው የተመዘገቡ የተለዩ ቲኬቶች» በሚል ጽሑፍ እናመለክታለን።   
  • የክወና ይፋ ማውጣቶች፦ አንዳንድ ጊዜ አንድ በረራ የአየር መንገድ ባልሆነ ሌላ ህጋዊ አካል (ወይም ቲኬቶችን ለሸማቾች በማይሸጥ አየር መንገድ) ሊከወን ይችላል። በዚህ ጊዜ በበረራ ዝርዝሮች ላይ «የ[ሌላ ህጋዊ አካል] አውሮፕላን እና ሰራተኛዎች» የሚል ጽሑፍ ሊያዩ ይችላሉ። 
  • የአየር መንገዶች እና የመስመር ላይ ጉዞ ወኪሎች የራሳቸው ደንቦች ነው የሚያወጡት። Google ላይ የሚፈልጓቸውን በረራዎች ከመረጡ በኋላ አብዛኛው ጊዜ ይህን የጉዞ ዕቅድ በአንዱ የGoogle የአየር መንገድ ወይም የመስመር ላይ ጉዞ ወኪል አጋሮች በኩል ቦታ የሚያስይዙበት አገናኝ ይቀርብልዎታል። አንዳንድ ጊዜ ቦታ የሚያስይዙበት ብዙ አማራጮች ሊኖረዎት ይችላል። ቲኬቱን ሊሸጡልዎ የሚችሉ ከሆነ በርካታ የአየር መንገዶች (ለምሳሌ፣ በረራው የተጋራ ኮድ ከሆነ) ወይም ማናቸውም የመስመር ላይ ጉዞ ወኪሎች ሊያዩ ይችላሉ።  አንዳንድ ጊዜ አንድ በረራ ቢኖርም እንኳ አጋሮች እኛ በድር ጣቢያቸው ላይ ከእሱ ጋር እንዳናገናኘው የሚከለክሉን ደንቦች ሊኖራቸው ይችላል። እርስዎ የሚፈልጉትን የጉዞ ዕቅድ ቦታ እንዲያስይዙ መርዳት እና አማራጮችዎን የሚያውቁ መሆንዎን ማረጋገጥ የእኛ ግብ ነው። 
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
11441351151914522556
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
254
false
false