በቅድመ-ምዝገባ ለመተግበሪያዎችዎ ግንዛቤን ይፍጠሩ

በቅድመ-ምዝገባ አማካኝነት መተግበሪያዎችዎን Google Play ላይ ከማተምዎ በፊት በመረጧቸው አገሮች ላይ ለመተግበሪያዎችዎ መጓጓትን እና ግንዛቤን መገንባት ይችላሉ።

አንድ መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ለቅድመ-ምዝገባ የሚገኝ ካደረጉ በኋላ ተጠቃሚዎች ስለእርስዎ መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ለማወቅ እና ለእሱ ቅድሚያ ለመመዝገብ የመደብር ዝርዝርዎን መጎብኘት ይችላሉ። ከዚያም ቆይተው የእርስዎን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ሲያትሙ ሁሉም በቅድሚያ-የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ከGoogle Play እንዲጭኑት የግፊት ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል። እንዲሁም በሚጀመርበት ቀን ብቁ የሆኑ መሣሪያዎች መተግበሪያውን ወይም ጨዋታውን በራስ-ሰር ይጭኑታል።

ማስታወሻ፦ የመተግበሪያዎን የሙከራ ስሪት አስቀድመው የጫኑ ተጠቃሚዎች የግፊት ማሳወቂያ አይቀበሉም።

ደረጃ 1፦ ለቅድመ-ምዝገባ ይዘጋጁ

በPlay Console ላይ የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻን ከማቀናበርዎ በፊት የቅድመ-ምዝገባ መስፈርቶቹን እና መመሪያዎቹን እና የእኛን የሚመከሩ የቅድመ-ምዝገባ ዝግጅት እንቅስቃሴዎች ያንብቡ።

መስፈርቶች እና መመሪያዎች

ቅድመ-ምዝገባን ከማብራትዎ በፊት በቅድሚያ ለመዘጋጀት ከግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው አንዳንድ ጥቂት ነገሮች እነሆ፦

  • ቅድመ-ምዝገባን ከመጀመርዎ በፊት ልቀትን ወደ ሙከራ ትራክ አቅደው እንዲለቅቁን እና መተግበሪያዎን እንዲሞክሩ በጥብቅ እንመክራለን። የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻዎች መቆየት የሚችሉት 90 ቀናት ብቻ ነው፣ ከዚህ በኋላ መተግበሪያዎን ወደ ምርት መልቀቅ አለብዎት።
  • ከኖቬምበር 13 2023 በኋላ የተፈጠሩ የግል መለያዎች ያላቸው ገንቢዎች መተግበሪያቸውን በGoogle Play ላይ ከማቅረባቸው በፊት እና በቅጥያ ቅድመ-ምዝገባን ከመጠቀማቸው በፊት የተወሰኑ የፍተሻ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው። የበለጠ ለማወቅ ይህን የእገዛ ማዕከል ጽሁፍ ያንብቡ።
  • መተግበሪያዎ ለታሰቡት ተጠቃሚዎቹ አደጋ የሌለው፣ የGoogle Play መመሪያዎችን የሚያከብር እና ሕጋዊ መስፈርቶችን የሚያሟላ መሆኑን ማረጋገጥ እንድንችል የሚያግዘን ስለ መተግበሪያዎ ይዘት የተወሰነ መረጃ እስከሚያቀርቡ ድረስ ቅድመ-ምዝገባን መጠቀም አይችሉም። መተግበሪያዎን ለግምገማ ለማዘጋጀት ምን መረጃ ማቅረብ እንዳለብዎት ይወቁ።
  • አንድ መተግበሪያ ወይም ጨዋታ በአንድ አገር ውስጥ ለቅድመ-ምዝገባ የሚገኝ ካደረጉ በኋላ እዚያው በምርት ዉስጥ በ90 ቀናት ውስጥ መልቀቅ አለብዎት።
  • በአንድ ጊዜ እስከ ሁለት መተግበሪያዎች ወይም ጨዋታዎች ድረስ ለቅድመ-ምዝገባ እንዲገኙ ማድረግ ይችላሉ።
  • የመተግበሪያዎ መግለጫዎች እና ውቅረቶች በተቻለ መጠን ወደታሰቡት የምርት ስሪት ቅርብ በሚሆኑበት ጊዜ የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻዎን እንዲያቀናብሩ እንመክራለን። ይህ መተግበሪያዎን በራስ-ሰር ለመጫን ብቁ ያደርገዋል እና አስቀድመው የተመዘገቡ ተጠቃሚዎችም እንዲሁ የማስጀመሪያ ማስታወቂያ እንደሚቀበሉ ያረጋግጣል።
ለቅድመ-ምዝገባ ለመዘጋጀት በቅድሚያ የሚወሰዱ እርምጃዎች

የተሟላ የመደብር ዝርዝር ይፍጠሩ

የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻዎን ከመጀመርዎ በፊት ግራፊክ እሴቶችን የሚያካትት ሁለገብ የመደብር ዝርዝር መፍጠርዎን እና ወደ ሌሎች ቋንቋዎች መተርጎሙን ያረጋግጡ። ይህ ቅድሚያ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች የእርስዎን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ የመጫን ዕድሉን ሊጨምር ይችላል።

መተግበሪያዎ በራስ-ሰር ለመጫን ብቁ ያድርጉት

የእርስዎን መተግበሪያ ለራስ-ሰር ጭነት ብቁ ለማድረግ ከመረጡ በሚለቀቅበት ቀን ላይ በራስ-ሰር ወደ የተጠቃሚዎች መሣሪያዎች መላክ ይችላሉ (እነሱ መርጠው ከገቡ)።

መተግበሪያዎን ለራስ ሰር ጭነት ብቁ ለማደረግ የሚከተሉትን እርምጃዎች ያድርጉ፦

  • የእርስዎ መተግበሪያ ማስታወቂያዎችን የያዘ ከሆነ ያስታውቁ።
  • የእርስዎ መተግበሪያ ወይም ጨዋታ የውስጠ-መተግበሪያ ምርቶችን የሚያቀርብ ከሆነ የአሁኑ የእርስዎ Android መተግበሪያ ቅርቅብ ስሪት በቅድመ-ምዝገባ ትራክዎ ላይ በመተግበሪያ የዝርዝር ሰነድ ውስጥ <uses-permission android:name="com.android.vending.BILLING" /> የሚለውን እንደሚያካትት ያረጋግጡ።
    • የተጠቃሚዎች የራስ-ሰር ጭነትን የመጠቀም ችሎታ በተወሰኑ ሁኔታዎች ላይ የሚወሰን ነው።

አስፈላጊ፦ የራስ-ሰር ጭነት ተገኝነት እና ተግባራዊነት ለሚከተሉት ሁኔታዎች ተገዢ ነው፦

  • ተጠቃሚው የራስ ሰር ጭነትን መጠቀም የሚችሉት የሚከተሉትን መስፈርቶች ካሟሉ ብቻ ነው፦
    • የAndroid M+ መሣሪያ ካላቸው።
    • Google Play መደብር ስሪት 19.2+ እየተጠቀሙ ከሆነ
  • ዕድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ Google መለያዎች እና የሚተዳደሩ የድርጅት መለያዎች የራስ-ሰር ጭነት መተግበሪያዎችን ለመጠቀም ብቁ አይደሉም።
  • የተጠቃሚው የመጫን ቅንብሮች ምንም ይሁኑ ምን ከ200 ሜባ በላይ የሆኑ መተግበሪያዎች የሚወርዱት እና የሚጫኑት Wi-Fiን ብቻ በመጠቀም ነው።
  • መሣሪያዎች መተግበሪያን በራስ-ሰር ወደ መጫን የሚቀጥሉት መሣሪያው በቂ የባትሪ ኃይል ካለው ብቻ ነው።
  • ብቁ ያልሆኑ መሣሪያዎች መደበኛውን የቅድመ-ምዝገባ ማስጀመሪያ ማሳወቂያ አሁንም ይቀበላሉ እና Google Play መሣሪያው የሚፈለጉትን ሁኔታዎች ሲያሟላ መተግበሪያውን በራስ-ሰር ለመጫን እንደገና ይሞክራል።

ትራፊክን ወደ ዝርዝርዎ ለመምራት ይዘጋጁ

በሦስተኛ ወገን ድር ጣቢያዎች፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ ጋዜጣዊ ዘገባዎች፣ የኢሜይል ጋዜጣዎች ወዘተ ላይ ያሉ ጥልቅ አገናኞችን በመጠቀም በመላ የማስተዋወቂያ ሰርጦችዎ ላይ አስቀድመው ትራፊክን ወደ ቅድመ-ምዝገባ ዝርዝርዎ ለማምራት እንዲዘጋጁ እንመክራለን።

  • ጠቃሚ ምክር፦ ቅድመ-ምዝገባን ካበሩ በኋላ የእርስዎ የቅድመ-ምዝገባ ዝርዝር ዩአርኤል የሚከተለውን ይሆናል፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=package የእርስዎ የመተግበሪያ ወይም የጨዋታ ስም
  • ምሳሌ፦ የመተግበሪያዎ የጥቅል ስም your.new.app ከሆነ የእርስዎ የቅድመ-ምዝገባ ዝርዝር ዩአርኤል የሚከተለውን ይሆናል፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=your.new.app

የGoogle Play ይፋዊ ቅድመ-ምዝገባ ባጅ ይጠቀሙ

የእርስዎን ዘመቻ በውጭ ድር ጣቢያዎች ላይ ለማስተዋወቅ የGoogle Playን ይፋዊ ቅድመ-ምዝገባ ባጅ ይጠቀሙ። ይህ መተግበሪያዎ ከመለቀቁ በፊት ቅድመ-ምዝገባዎችን እንዲመራ ያግዛል።

ደረጃ 2፦ የቅድመ-ምዝገባ መሣሪያዎችን ይግለጹ

ተጠቃሚዎች ለእርስዎ መተግበሪያ በቅድሚያ ለመመዝገብ የሚጠቀሙባቸው መሣሪያዎችን መግለጽ የሚችሉባቸው የመተግበሪያ ቅርቅቦችን መስቀል ይችላሉ። Play Console የትኛዎቹን መሣሪያዎች ለቅድመ-ምዝገባ እንደሚደግፍ ለማወቅ የመተግበሪያዎችዎን ዝርዝር ሰነድ ይጠቀማል።

ማስታወሻ፦

  • በቅድመ-ምዝገባ ትራክ ላይ የሚሰቅሏቸው ማናቸውም የመተግበሪያ ቅርቅቦች ጥቅም ላይ የሚውሉት የሚደገፉ መሣሪያዎችዎን ለመግለጽ ብቻ ነው፣ እና ለተጠቃሚዎች አይለቀቁም።
  • የእርስዎ መተግበሪያ የውስጠ-መተግበሪያ ምርቶችን ከያዘ ከሚሰቀሏቸው የመተግበሪያ ቅርቅቦች ወይም ኤፒኬዎች ቢያንስ አንዱ የGoogle Play ክፍያ ቤተ-ፍርግምን ማካተቱን ያረጋግጡ።
ተጠቃሚዎች በመተግበሪያዎ ላይ በቅድሚያ መመዝገብ የሚችሉባቸውን መሣሪያዎች ይግለጹ

ለቅድመ-ምዝገባ መሣሪያዎችን የሚገልፅ የመተግበሪያ ቅርቅብ ለመስቀል የሚከተሉትን እርምጃዎች ያድርጉ፦

  1. Play Consoleን ይክፈቱ።
  2. መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ይምረጡ።
  3. በግራ ምናሌው ላይ ልቀት > ሙከራ > ቅድመ-ምዝገባ የሚለውን ይምረጡ።
  4. የሚደገፉ መሣሪያዎች የሚለውን ትር ይምረጡ።
  5. የእርስዎን የAndroid መተግበሪያ ቅርቅቦች (.aab) ለመስቀል ወደ ሳጥኑ ይጎትቷቸው፣ ወይም ስቀልን ይምረጡ።
  6. አስቀምጥን ይምረጡ።

ደረጃ 3፦ ተጠቃሚዎች ቅድሚያ ሊመዘገቡባቸው የሚችሉባቸው አገሮችን ያክሉ

የመተግበሪያዎ በየትኛዎቹ አገሮች እና ክልሎች ውስጥ ለቅድመ-ምዝገባ እንደሚገኝ መምረጥ ይችላሉ።

ማስታወሻ፦ እነዚህ ተጠቃሚው በGoogle Play ላይ የተመዘገቡባቸው አገሮች ወይም ክልሎች ናቸው፣ አካላዊ መገኛ አካባቢያቸው አይደለም።

ለቅድመ-ምዝገባ አገሮችን/ክልሎችን ያክሉ

መተግበሪያዎን ለቅድመ-ምዝገባ እንዲገኝ ለማድረግ ተጠቃሚዎች ለመተግበሪያዎ በቅድሚያ-መመዝገብ እንዲችሉ የሚፈልጉባቸውን አገሮች መምረጥ አለብዎት እና የሚከተሉትን እርምጃዎች ማድረግ፦

  1. Play Consoleን ይክፈቱ።
  2. መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ይምረጡ።
  3. በግራ ምናሌው ላይ ልቀት > ሙከራ > ቅድመ-ምዝገባ የሚለውን ይምረጡ።
  4. አገሮች/ክልሎች ትሩን ይምረጡ።
  5. አገሮችን/ክልሎችን አክል የሚለውን ይምረጡ።
  6. የእርስዎን መተግበሪያ ለቅድመ-ምዝገባ የሚገኝ ማድረግ የሚፈልጉባቸው አገሮችን/ክልሎችን ይምረጡ።
  7. አስቀምጥ የሚለውን ይምረጡ።

ማስታወሻ፦ እንዲሁም የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻዎን ከጀመሩት በኋላ አገሮችን ማከል ይችላሉ። ለአንድ አገር የሚሆነው የ90-ቀን መስኮቱ በዚያ አገር ለመጀመሪያ ጊዜ ቅድመ-ምዝገባውን እንዲገኝ ካደረጉበት ጊዜ ይጀምራል።

ደረጃ 4፦ ለተጠቃሚዎች የቅድመ-ምዝገባ ሽልማቶችን ያቅርቡ (ከፈለጉ)

በቅድመ-ምዝገባ ሽልማቶች አማካኝነት ተጠቃሚዎች ለእርስዎ መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ቅድሚያ ከተመዘገቡ በኋላ የውስጠ-መተግበሪያ ምርት በነፃ ሊሰጧቸው ይችላሉ። የቅድመ-ምዝገባ ሽልማቶች የሚሠራው ከማስተዋወቂያዎች ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ነው። ይሁንና፣ ነፃ ንጥል ለመቀበል የማስተዋወቂያ ኮድ ከመተየብ ይልቅ ተጠቃሚዎች በአንድ የመተግበሪያ መደብር ዝርዝር ላይ የቅድመ-ምዝገባ አዝራርን ከመረጡ በኋላ አንድ ንጥል ይቀበላሉ።

ስለ ቅድመ-ምዝገባ ሽልማቶች ማወቅ ያለብዎት አስፈላጊ ነገሮች

የቅድመ-ምዝገባ ሽልማቶችን ከማቀናበርዎ በፊት የሚከተሉት ለማወቅ አስፈላጊ ናቸው፦

  • ለአንድ የመተግበሪያ ዕድሜ ዘመን ወይም የጨዋታ ቅድመ-ምዝገባ ዘመቻ አንድ የቅድመ-ምዝገባ ሽልማት መፍጠር ይችላሉ።
  • የቅድመ-ምዝገባ ሽልማት ከፈጠሩ በኋላ አርትዖት ሊደረግበት ወይም ሊሰረዝ አይችልም።
  • ሽልማቶችን ማብራት ወይም ማጥፋት ይችላሉ፣ ነገር ግን የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻዎ ንቁ በሚሆንበት ጊዜ አይደለም።
  • ገቢር የውስጠ-መተግበሪያ ምርቶችን ብቻ ነው እንደ የቅድመ-ምዝገባ ሽልማቶች አድርገው ማቅረብ የሚችሉት፣ የደንበኝነት ምዝገባዎች ወይም የቦዘኑ የቅድመ-ምዝገባ ምርቶችን አይችሉም።
  • የመተግበሪያዎን የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻ ከመጀመርዎ በፊት የቅድመ-ምዝገባ ሽልማት ማቀናበር አለብዎት።
  • የእርስዎ መተግበሪያ የውስጠ-መተግበሪያ ምርቶች ሊኖረው ይገባል፣ እንዲሁም ከሚደግፉ ማስተዋወቂያዎች ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ሽልማቱን የሚወስደውን ፍሰት መተግበር መቻል አለበት (ለዝርዝሩ ቴክኒካዊ መስፈርቶችን ይመልከቱ)።
  • አንድ የውስጠ-መተግበሪያ ምርትን እንደገና ከመጠቀም ይልቅ ለቅድመ-ምዝገባ ሽልማቶች ብለው የሚጠቀሙበት አንድ የውስጠ-መተግበሪያ ምርት መፍጠር አለብዎት።

የቅድመ-ምዝገባ ሽልማቶችን ለመጠቀም ከወሰኑ የቅድመ-ምዝገባ ሽልማቶችን ለተጠቃሚዎች አለማድረስ መተግበሪያዎን ከPlay መደብር ሊያሳግደው ይችላል።

የቴክኒካዊ ትግበራ ማሟያዎች
  • Google Play መደብር ቅድሚያ ለተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ማድረስ የሚችል የሚተዳደር የውስጠ-መተግበሪያ ምርት ኤስኬዩ መፍጠር አለብዎት (ለምሳሌ፦ የውስጠ-መተግበሪያ ንጥል፣ ልዩ ቁምፊ፣ የምንዛሪ ጥቅል)።
  • የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻዎን ከመጀመርዎ በፊት ለቅድመ-ምዝገባ ሽልማቶች ሥራ ላይ የዋለው የሚተዳደር የውስጥ መተግበሪያ ምርትዎ ገቢር መሆን አለበት።
  • ማስተዋወቂያዎችን ከመጠቀም ጋር ተመሳሳይ በሆነ መልኩ developerPayload እና orderId ከሌሉ መተግበሪያዎ በቴክኒክ ደረጃ መቻል አለበት።
  • ተጠቃሚዎች ውስጠ-ጨዋታ መልዕክት መላላኪያን በመጠቀም ሽልማት ሲቀበሉ አግባብነት ባለው ጊዜ ውስጥ ሊያሳውቋቸው ይገባል።
    • ማስታወሻ፦ በቅድመ-ምዝገባ ዘመቻን መልቀቅ እና በመተግበሪያዎ ሙሉ መለቀቅ መካከል ለተጠቃሚዎች መልዕክት ለመላክ የሚያስፈልገው ቴክኒካዊ ሥራን ማጠናቀቅ ይችላሉ።
የቅድመ-ምዝገባ ሽልማትን ይፍጠሩ እና ያቀናብሩ

የቅድመ-ምዝገባ ሽልማቶችን ለመጠቀም በሚፈልጉባቸው ማናቸውም አገሮች ውስጥ ቅድመ-ምዝገባን ከማብራትዎ በፊት ቅድሚያ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ሽልማታቸውን መቀበላቸውን ለማረጋገጥ መጀመሪያ የቅድመ-ምዝገባ ሽልማቱን ማቀናበርዎን ያረጋግጡ። የቅድመ-ምዝገባ ሽልማት ለመፍጠር ወይም ለማዋቀር የሚከተሉትን እርምጃዎች ያድርጉ፦

  1. Play Consoleን ክፈት።
  2. አንድ መተግበሪያ ይምረጡ።
  3. በግራ ምናሌው ላይ ልቀት > ሙከራ > ቅድመ-ምዝገባ የሚለውን ይምረጡ።
  4. ሽልማቶችትርን ይምረጡ።
  5. ለተጠቃሚዎች የቅድመ-ምዝገባ ሽልማት መስጠት ይፈልጉ እንደሆነ ይምረጡ፦
    • ለተጠቃሚዎች የቅድመ-ምዝገባ ሽልማት አይስጡ፦ ይህን አማራጭ ከመረጡ ወደ ደረጃ 5፦ ቅድመ-ምዝገባ ይጀምሩ ከመሄድዎ በፊት ለውጦችዎን ማስቀመጥ ያስፈልግዎታል።
    • ለተጠቃሚዎች የቅድመ-ምዝገባ ሽልማት ይስጡ፦ ይህ አማራጭ ከመረጡ በሚከተሉት እርምጃዎች ይቀጥሉ።
  6. የቅድመ-ምዝገባ ሽልማት አገልግሎት ውልን ይገምግሙ እና ይስማሙበት።
  7. በዚህ ጊዜ ከዚህ በፊት የውስጠ-መተግበሪያ ምርት ያልፈጠሩ ከሆነ እንዲፈጥሩ የሚጠይቀዎት መልዕክት ያያሉ። አሁን ያለውን የውስጠ-መተግበሪያ ምርት እንደገና ከመጠቀም ይልቅ በተለይ ለቅድመ-ምዝገባ ሽልማቶች የሚጠቀሙበት የውስጠ-መተግበሪያ ምርት መፍጠር አለብዎት። በ«ቅድመ-ምዝገባ ሽልማት ይፍጠሩ» ክፍሉ ውስጥ የሚከተለውን መረጃ ያስገቡ፦
    • ምርት፦ ምርትዎን ከተቆልቋዩ ይምረጡ።
    • የሽልማት ባጅ (አማራጭ)፦ ይህ ባጅ ከቅድመ-ምዝገባ ሽልማቱ ቀጥሎ በመደብር ዝርዝርዎ ላይ ይታያል።
    • የደንቦች እና ሁኔታዎች ዩአርኤሎች፦ ተጠቃሚዎች ሽልማቱን መቀበል ከመቻላቸው በፊት መቀበል ያለባቸውን ወደ እርስዎ የደንቦች እና ሁኔታዎች የሚወስድ አገናኝ ያቅርቡ። ለተለያዩ አገሮች/ክልሎች ተጨማሪ አገናኞችን ማቅረብ ይችላሉ።
  8. የቅድመ-ምዝገባ ሽልማቱን ማብራት እንደሚፈልጉ ለማረጋገጥ አስቀምጥ እና ከዚያ ፍጠር የሚለውን ይምረጡ።
    • አስታዋሽ፦ ተጠቃሚዎች ሽልማቱን በእርስዎ መደብር ዝርዝር ላይ ይመለከታሉ። የእርስዎ የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻ ንቁ ሆኖ እያለ ሽልማቱን መለወጥ ወይም ማስወገድ አይችሉም።
የቅድመ-ምዝገባ ሽልማትዎን ያስወግዱ

ገቢር የሆነ የቅድመ ምዝገባ ዘመቻ እያለዎት የቅድመ ምዝገባ ሽልማቱን መለወጥ አይችሉም፣ ነገር ግን ዘመቻዎ ገና ካልተጀመረ ወይም ገቢር የሆኑ የቅድመ ምዝገባ ዘመቻዎች ያሉባቸው አገሮች ወይም ክልሎች ከሌሉ ይችላሉ። የቅድመ-ምዝገባ ሽልማትን ለማስወገድ የሚከተሉትን እርምጃዎች ያድርጉ፦

  1. Play Consoleን ይክፈቱ።
  2. የቅድመ-ምዝገባ ሽልማቱን ሊያጠፉለት የሚፈልጉትን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ይምረጡ።
  3. በግራ ምናሌው ላይ ልቀት > ሙከራ > ቅድመ-ምዝገባ የሚለውን ይምረጡ።
  4. ሽልማቶችትርን ይምረጡ።
  5. ለተጠቃሚዎች የቅድመ-ምዝገባ ሽልማት አይስጡን ይምረጡ።
  6. የቅድመ-ምዝገባ ሽልማቱን ማጥፋት እንደሚፈልጉ ለማረጋገጥ አስቀምጥ እና ከዚያ አስወግድ የሚለውን ይምረጡ።
    • አስታዋሽ፦ ተጠቃሚዎች ይህን ሽልማት በእርስዎ መደብር ዝርዝር ላይ አይመለከቱም። የእርስዎ ቅድመ-ምዝገባ ዘመቻ ንቁ ሆኖ እያለ አዲስ ሽልማት መፍጠር አይችሉም።
መተግበሪያዎ ከመጀመርዎ በፊት የቅድመ-ምዝገባ ሽልማት ማድረስን ይሞክሩ

የቅድመ-ምዝገባ ሽልማቶች ከማስተዋወቂያዎች ጋር ተመሳሳይ ስለሆኑ ተመሳሳዮቹን ስልቶች ተጠቅመው ሊሞክሯቸው ይችላሉ። የቅድመ-ምዝገባ ሽልማት ማድረስን ለመሞከር በPlay Console ውስጥ እንደ ሽልማት ለሚጠቀሙበት የሚተዳደር ምርት የማስተዋወቂያ ኮድን ያመንጩ እና ጥቅም ላይ ያውሉ

ደረጃ 5፦ ቅድመ-ምዝገባ ይጀምሩ

የሚደገፉ መሣሪያዎቹን ከገለጹ፣ ዘመቻዎ እንዲካሄድ የሚፈልጉባቸው አገሮች ከመረጡ እና የቅድመ-ምዝገባ ሽልማቱን ይሰጡ ወይም አይስጡ ከወሰኑ በኋላ ቅድመ-ምዝገባን ለመጀመር ዝግጁ ነዎት።

ቅድመ-ምዝገባን ካበሩ በኋላ የእርስዎን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ የቅድመ-ምዝገባ ዝርዝር ዩአርኤልን በመጠቀም በመላው የማስተዋወቂያ ሰርጦችዎ ላይ የእርስዎን ዘመቻ ማስተዋወቅዎን ያረጋግጡ። መጠቀም የሚችሏቸው የተለመዱ ሰርጦች በሦስተኛ ወገን ድር ጣቢያዎች፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ የጋዜጣዊ ዘገባዎች፣ የኢሜይል ጋዜጣዎች ላይ ያሉ ጥልቅ አገናኞችን መጠቀም ያካትታሉ።

የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻዎን ይጀምሩ

የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻዎን ለመጀመር የሚከተሉትን እርምጃዎች ያድርጉ፦

  1. Play Consoleን ይክፈቱ።
  2. ቅድመ ምዝገባን ለመጀመር የሚፈልጉበትን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ይምረጡ።
  3. በግራ ምናሌው ላይ ልቀት > ሙከራ > ቅድመ-ምዝገባ የሚለውን ይምረጡ።
  4. ቅድመ-ምዝገባን ጀምር የሚለውን ይምረጡ።

ይህ የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻ ሲጀምሩ የመጀመሪያዎ ከሆነ እስካሁኑ ጊዜ ድረስ ባዶ የነበረው በቅድመ-ምዝገባ ገፁ ላይ ያለው «የክትትል ማጠቃለያ» ክፍሉ በቅድመ-ምዝገባ ልቀት መረጃዎ ይሞላል።

የቅድመ-ምዝገባ አስተዳደር

የእርስዎ ቅድመ-ምዝገባ ዘመቻ እያሄደ ባለበት ጊዜ እንደ የእይታ ስታቲስቲክስ፣ በተለያዩ አገሮች ወይም ክልሎች ውስጥ ምን ያህል ጊዜ እንደቀረ ማየት እና ሙከራዎችን ማሄድ ያሉ እርስዎ አጋዥ ሆነው ሊያገኟቸው የሚችሏቸው የተለያዩ የአስተዳደር እንቅስቃሴዎች አለ። የእርስዎን የመተግበሪያ ሲገነቡ ወይም ጨዋታውን ሲያጀምሩ አጋዥ ሆነው ሊያገኟቸው ይችላሉ።

የቅድመ-ምዝገባ ቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያዎችን ይመልከቱ

የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻዎ በሁለቱም እየተከናወነ ባለበት ወቅት እና ከተከናወነ በኋላ ያሉትን ቁልፍ የአፈጻጸም መለኪያዎችን ለመመልከት የሚከተሉትን እርምጃዎች ያድርጉ፦

  1. Play Consoleን ይክፈቱ።
  2. እርስዎ ለቅድመ-ምዝገባ እንዲገኝ ያደረጉትን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ይምረጡ።
  3. በግራ ምናሌው ላይ ስታቲስቲክስን ይምረጡ።
  4. ከሚገኙት የቅድመ-ምዝገባ መለኪያዎች ውስጥ ሁለቱን በመጠቀም ሪፖርት ያዋቅሩ፦
    • ቅድሚያ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች፦ ለመተግበሪያዎ ቅድሚያ የተመዘገቡ የተጠቃሚዎች ብዛት።
    • ልወጣዎች፦ መተግበሪያው ለእነሱ ከተገኘ በኋላ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ የጫኑት በቅድሚያ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች ብዛት። ይህ ቁጥር ከጊዜው በፊት መዳረሻ እና በሌሎች የቅድመ-ጅምር የሙከራ ዘዴዎች በኩል የጫኑ ቅድሚያ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎችን ያካትታል።
  5. ለመመልከት የሚፈልጓቸውን መለኪያዎች ከመረጡ በኋላ ሪፖርትዎን ያስቀምጡ።

እንዲሁም በየልቀቶች አጠቃላይ ዕይታ ገፁ ላይ ወይም በቅድመ-ምዝገባ ገፁ «የክትትል ማጠቃለያ» ክፍሉ ውስጥ አንድ መተግበሪያን በመምረጥና የልቀት ዝርዝሮችን በማየት የቅድመ-ምዝገባ ማጠቃለያ ስታቲስቲክስን መመልከት ይችላሉ።

የቅድመ-ምዝገባ ማጠቃለያ ስታቲስቲክስን ይመልከቱ

ቅድመ-ምዝገባን መጠቀም ከጀመሩ በኋላ ቅድመ-ምዝገባ የሚገኝ ባደረጉበት እያንዳንዱ አገር ወይም ክልል ውስጥ ዘመቻዎ ምን ያህል ጊዜ እንደቀረው መከታተል አለብዎት። በማናቸውም እነዚህ አገሮች ውስጥ በ90 ቀናት ጊዜ ውስጥ ካላስጀመሩ የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻዎ በሁሉም አገሮች ውስጥ ይቋረጣል እና አዲስ የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻዎች መጀመር አይችሉም።

የቅድመ-ምዝገባ ማጠቃለያ ስታቲስቲክስን ለመመልከት እና ዘመቻዎ በእያንዳንዱ አገር ምን ያህል ጊዜ እንደቀረው እና የእያንዳንዱን አገር ሁኔታ ለመከታተል የሚከተሉትን እርምጃዎች ያድርጉ፦

  1. Play Console ይክፈቱ።
  2. እርስዎ ለቅድመ-ምዝገባ እንዲገኝ ያደርጉትን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ይምረጡ።
  3. በግራ ምናሌው ላይ ልቀት > ሙከራ > ቅድመ-ምዝገባ የሚለውን ይምረጡ።
  4. «የክትትል ማጠቃለያ» ክፍሉ ላይ የቅድመ-ምዝገባዎን ልቀት ያግኙ እና መረጃውን ይገምግሙ፣ ይህም የሚከተሉትን ያካትታል፦
    • የቅድመ-ምዝገባ ሁኔታ
      • ረቂቅ ወይም በግምገማ ላይ፦ አገር/ክልል ነቅቷል እና በግምገማ ላይ ነው።
      • ገቢር፦ ቅድመ-ምዝገባ እያሄደ ነው እና መተግበሪያዎ እስከተገለጸው ቀን ድረስ (የ90-ቀን ገደብ) ወደ ምርት መለቀቅ አለበት።
      • የአገልግሎት ጊዜው አብቅቷል፦ ቅድመ-ምዝገባ ከ90-ቀን ገደቡ አልፏል እና መተግበሪያዎ ወዲያውኑ መለቀቅ አለበት።
      • በምርት ላይ፦ ቅድመ-ምዝገባ ምርትን አስጀምሯል፣ ወይም መተግበሪያው በዚህ አገር ውስጥ መጀመሪያ ቅድመ-ምዝገባ ሳያሄድ ምርትን አስጀምሯል።
      • ገቢር አልሆነም፦ ቅድመ-ምዝገባ ባለበት እንዲቆም ተደርጓል (የ90-ቀን ገደቡ አሁንም ተፈጻሚ ነው)።
      • አልተጀመረም፦ ቅድመ-ምዝገባ ገና አልተጀመረም።
    • የምዝገባዎች ብዛት
    • የሚደገፉ የመሣሪያዎች ብዛት
    • እርስዎ ያከሏቸው የአገሮች/ክልሎች ብዛት
ከቅድመ-ምዝገባ ላይ የእርስዎን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ያስጀምሩ

የእርስዎን ጨዋታ ወይም መተግበሪያ ለማስጀመር እና የቅድመ-ምዝገባ ዘመቻውን ለማብቃት ዝግጁ በሚሆኑበት ጊዜ የእርስዎ መተግበሪያ ወይም ጨዋታ እንዲገኝ የሚፈልጉባቸውን አገሮችን እንዴት መምረጥ እንደሚችሉ እነሆ። የእርስዎን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ በምርት ላይ ካተሙ በኋላ በቅድሚያ የተመዘገቡ ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን ወይም ጨዋታውን ለማውረድ የሚገኝ መሆኑን የሚያሳውቅ የPlay መደብር ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል፣ እንዲሁም ብቁ የሆኑ መሣሪያዎች መተግበሪያውን ወይም ጨዋታውን በራስ-ሰር ይጭኑታል።

ከቅድመ-ምዝገባ ላይ የእርስዎን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ለማስጀመር የሚከተሉትን እርምጃዎች ያድርጉ፦

  1. Play Console ይክፈቱ።
  2. እርስዎ ለማስጀመር የሚፈልጉትን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ይምረጡ።
  3. በግራ ምናሌው ላይ ልቀት > ሙከራ > ምርትን ይምረጡ።
  4. አገሮች/ክልሎች ትሩን ይምረጡ።
  5. አገሮችን/ክልሎችን አክልን ይምረጡ።
  6. መተግበሪያዎ እንዲገኝ ማድረግ የሚፈልጉባቸውን አገሮች/ክልሎች ይምረጡ።
  7. አስቀምጥ የሚለውን ይምረጡ።

አስፈላጊ፦ መተግበሪያዎን በመረጧቸው አገሮች ላይ በGoogle Play ላይ እንዲገኝ ለማድረግ የእርስዎን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ በምርት ትራኩ ላይ ማተምዎን ያረጋግጡ።

በቅድመ-ምዝገባ ጊዜ መሞከር

የቅድመ-ማስመጀር ሙከራዎችም ጨምሮ ቅድመ-ምዝገባን ከሌሎች የቅድመ-ጅምር ባህሪያት ጋር በተመሳሳይ ጊዜ በPlay Console ውስጥ መጠቀም ይችላሉ። የሚከተሉት ቅድመ-ምዝገባን ስለ መጠቀም እና በተመሳሳይ ጊዜ ሙከራዎችን ስለ ማሄድ መታወቅ ያለባቸው አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮች ናቸው፦

  • እርስዎ በመረጧቸው አገሮች ውስጥ ቅድመ-ምዝገባን ማሄድ እና በተመሳሳይ ጊዜ የቅድመ-ጅመር ሙከራዎችን በሌሎች ላይ ማሄድ ይችላሉ።
  • ለቅድመ-ምዝገባ የእርስዎን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ እንዲገኝ ለማድረግ የሚፈልጉበት አገር ውስጥ ክፍት ወይም ዝግ ሙከራ እያሄዱ ያሉ ከሆነ አሁንም ወደ ቅድመ-ምዝገባ መቀየር ይችላሉ። በዚያ አገር ውስጥ ወደ ቅድመ-ምዝገባ ከቀየሩ በኋላ የሚከተሉትን ከግምት ውስጥ ያስገቡ፦
    • የእርስዎን ሙከራ አስቀድመው የተቀላቀሉ ተጠቃሚዎች በየራሳቸው የሙከራ ትራክ ላይ የሚለቀቁ ዝማኔዎችን መቀበላቸውን ይቀጥላሉ። ሌሎች ተጠቃሚዎች በመደብር ዝርዝርዎ ላይ በጫን አዝራር ምትክ ቅድመ-ምዝገባ አዝራርን ይመለከታሉ።
    • ማስታወሻ፦ ክፍት ሙከራ ሲያሄዱ በነበሩበት አገር ቅድመ-ምዝገባን ካበሩ በዚያ አገር ያሉ ተጠቃሚዎች በመደብር ዝርዝርዎ በኩል ወደ ሙከራዎ መርጠው መግባት አይችሉም፣ ነገር ግን በPlay Console ውስጥ በሚገኘው የመርጦ መግቢያ ዩአርኤል በኩል አሁንም መቀላቀል ይችላሉ።
      • ለሙከራዎ የመርጦ-መግቢያ ዩአርኤሉን ለማግኘት ወደ Play Console ይግቡ እና ከዚያ ልቀት > ሙከራ > ዝግ ሙከራ ወይም ክፍት ሙከራ የሚለውን ይጎብኙ እና የሞካሪዎች ትሩን ይምረጡ።
      • የእርስዎ መርጦ-መግቢያ ዩአርኤል የሚከተለውን ይሆናል፦ https://play.google.com/apps/testing/package የእርስዎ መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ስም
      • ምሳሌ፦ የመተግበሪያዎ የጥቅል ስም your.new.app ከሆነ የእርስዎ መርጦ-መግቢያ ዩአርኤል የሚከተለውን ይሆናል፦ https://play.google.com/apps/testing/your.new.app
    • የእርስዎን ሙከራዎች አስቀድመው የተቀላቀሉ ተጠቃሚዎች እስከሚያራግፉ እና ከመተግበሪያዎ የሙከራ ፕሮግራም መርጠው እስከሚወጡ ድረስ በቅድሚያ-መመዝገብ አይችሉም።
    • እርስዎ ቆይተው ክፍት ወይም ዝግ ሙከራን ማሄድ እንደሚፈልጉ በወሰኑበት አገር ውስጥ አስቀድመው ቅድመ-ምዝገባን ካበሩ እርስዎ ሙከራውን በዚያ ገበያ ውስጥ ሲለቅቁ ለሙከራ ብቁ የሆኑ እና የመርጠው የገቡ ተጠቃሚዎች እንዲጭኑ የሚጠይቅ የቅድመ-ምዝገባ ማሳወቂያ እንደሚደርሳቸው ማወቅ አስፈላጊ ነው። የእርስዎን መተግበሪያ ወይም ጨዋታ በምርት ውስጥ ካስጀመሩት በኋላ እነሱ ተከታይ ማሳወቂያ አይደርሳቸውም። ለዝግ ሙከራዎች የጋበዟቸው እና ለሙከራ መርጠው የገቡ ተጠቃሚዎች ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል።

ተዛማጅ ይዘት

  • Play አካዳሚ ውስጥ ባለ ቅድመ-ምዝገባ የቅድመ-ጅምር አፍታዎን ስለማሳደግ የበለጠ ይወቁ።

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?

ተጨማሪ እገዛ ያስፈልግሃል?

እነዚህን ቀጣይ እርምጃዎች ይሞክሩ፦

ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
8609278815366819194
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
92637
false
false