የእርስዎን የቅድመ-ጅምር ሪፖርት ይረዱ

ይህ ጽሑፍ የስሕተቶች፣ ማስጠንቀቂያዎች ወይም የእርስዎ ሪፖርት ገልጦ ሊያወጣቸው የሚችሉ የችግሮች አጠቃላይ ዕይታን በመስጠት የእርስዎን የቅድመ-ጅምር ሪፖርት እንዲረዱ እርስዎን ያግዝዎታል። የቅድመ-ጅምር ሪፖርት እንዴት ለማቀናበር እና ለማሄድ እንደሚችሉ ማወቅ ከፈለጉ ወደ ችግሮችን ለይቶ ለማወቅ የቅድመ-ጅምር ሪፖርት ይጠቀሙ የሚለው ይሂዱ።

የእርስዎ የቅድመ-ጅምር ሪፖርት የሚገኝ ሲሆን በሙከራ ጊዜ የተገኙ በችግር ዓይነት የተመደቡ የስሕተቶች፣ ማስጠንቀቂያዎች እና ቀላል ችግሮችን ብዛት የሚያካትት የሙከራ አጭር ማጠቃለያን ማየት ይችላሉ። እንዲሁም በመተግበሪያዎ የሙከራ ውጤቶች ላይ በመመስረት ምክርን ይመለከታሉ።

ማስታወሻ፦ ምንም እንኳ የቅድመ-ጅምር ሪፖርቱ የእርስዎን መተግበሪያ ለማሻሻል እንዲችሉ የሚያግዝ ተግባራዊ እና ኃይለኛ መሣሪያ ቢሆንም፣ Google ሙከራዎች ሁሉንም ችግሮች ለይተው እንደሚያውቁ ዋስትና መስጠት አይችልም። የእርስዎ ውጤቶች ሁለገብ እንደሆኑ እና በተቻለ መጠን እርስዎን የሚመለከታቸው መሆናቸውን ለማረጋገጥ የእርስዎን የቅድመ-ጅምር ሪፖርት ቅንብሮች ይገምግሙ እና ያዘምኑ።

የእርስዎ የቅድመ-ጅምር ሪፖርት አጠቃላይ ዕይታ

የቅድመ-ጅምር ሪፖርት አጠቃላይ ዕይታው ገጽ በአራት ምድቦች ማለትም በእርጋታ፣ በአፈጻጸም፣ በተደራሽነት እና በተአማኒነት የተመደቡ በሙከራ ጊዜ የተገኙ የማናቸውም ልዩ ስሕተቶች፣ ማስጠንቀቂያዎች እና ቀላል ችግሮች አጭር ማጠቃለያን ያቀርባል። እነዚህ ምድቦች በበለጠ ዝርዝር ከዚህ በታች ተብራርተዋል።

እንዲሁም የእርስዎ መተግበሪያ የተሞከረባቸው የመሣሪያዎች ብዛትን እና በሙከራው ውጤቶች ላይ በመመሥረት መተግበሪያዎን ለማሻሻል ሊያግዙ የሚችሉ ግንዛቤዎችን እና ምክሮችን ይመለከታሉ።

በሙከራ ወቅት የተገኙ ችግሮች አንዳንድ ምሳሌዎች እነሆ፦

  • ስህተቶች፦ ብልሽቶችን፣ ኤኤንአሮችን፣ ጉድለት ያለባቸው ቤተ መጽሐፍትን መጠቀምን እና የተገደቡ የማይደገፉ ኤፒአዮችን መጠቀምን ያካትታሉ።
  • ማስጠንቀቂያዎች፦ ቀርፋፋ የጅምር እና የጭነት ጊዜዎችን፣ በመለያ የመግባት ወይም የጉብኝት ችግሮችን፣ የማህደረ ትውስታ ችግሮችን፣ ገና ያልተገደቡ የማይደገፉ ኤፒአዮችን መጠቀምን ያካትታሉ።
  • ቀላል ችግሮች፦ የጎደሉ የይዘት መሰየሚያዎች፣ የቀለም ንጽጽር ችግሮች፣ አነስተኛ የንክኪ ዒላማ መጠኖች፣ የትግበራ ችግሮችን ያካትታሉ።

 

ሁሉንም ሰብስብ ሁሉንም ዘርጋ

የእርስዎ የቅድመ-ጅምር ሪፖርት ዝርዝሮች

እርጋታ

እርጋታ ትር እያንዳንዱ ክፍል በሙከራ ጊዜ የተገኙ የሚከተሉትን ሊያካትቱ የሚችሉ ችግሮችን በዝርዝር ያቀርባል፦

  • የችግሩ ዓይነት እና አዶ፦
    • ቀይ ስሕተትን ይጠቁማል
    • ቢጫ ማስጠንቀቂያን ይጠቁማል
    • አረንጓዴ ሙከራው ምንም ችግሮች እንዳላገኘ ይጠቁማል
  • ችግሩ የተገኘባቸው የመሣሪያዎች ብዛት
  • ከችግሩ ጋር ግንኙነት ያለው የቁልል ዱካ
  • የሚመለከተው ኤፒአይ (ተገቢነት ካለው)
  • በሙከራ ጊዜ የተገኘ ችግር የተገኘበት ጊዜ ብዛት (ተገቢነት ካለው)

ከእያንዳንዱ ችግር ቀጥሎ እንደ የመሣሪያ ስም፣ የማያ ገጽ መጠን፣ የAndroid ስሪት፣ ራም፣ የመተግበሪያ ሁለትዮሽ በይነገጽ (ኤቢአይ) እና አካባቢ ያሉ ስለችግሩ ጠለቅ ያሉ ዝርዝሮችን ለማግኘት ተጨማሪ አሳይ የሚለውን መምረጥ ይችላሉ። የመሣሪያው ዝርዝር መግለጫዎችን፣ ከሙከራ ቅጽበታዊ ገጽ እይታን እና ቪዲዮን፣ የማሳያ ምልልስ ውጽዓትን እና መከታታያ ቁልሎችን (ሊያወርዱት የሚችሉት) ለማየት የእያንዳንዱን መሣሪያ ሞዴል መምረጥ ይችላሉ። የእነዚህ ዝርዝሮች ተገኝነት ሊለያይ እንደሚችል ልብ ይበሉ።

ማስታወሻ፦ የቅድመ-ጅምር ሪፖርት በመመንጨት ላይ ሳለ የሚገኙ ብልሽቶች የሚመጡት ከሙከራ መሣሪያዎች ስለሆኑ በብልሽት ስታቲስቲክስዎ ላይ ተጽዕኖ አያሳድሩም።

ችግሮች የሌለባቸው የሙከራ መሣሪያዎችን ይመልከቱ

እርጋታ ትር ግርጌ ላይ ምንም ችግሮችን ያላስገኙ ሙከራዎችን በተመለከተ መረጃውን ለማየት ችግር የሌለባቸው የሙከራ መሣሪያዎችን ማየት ይችላሉ። 

በእያንዳንዱ ረድፍ ላይ የመሞከሪያ መሣሪያውን ስም፣ የመሣሪያው Android ስሪት እና የእርስዎ መተግበሪያ ማንኛውም የመሞከሪያ ችግሮች እንዳሉበት የሚያሳይ አዶን ይመለክታሉ።

እርጋታ፦ የAndroid ተኳዃኝነት

መተግበሪያዎ አንድ ወይም ተጨማሪ በይፋዊ የAndroid ኤስዲኬ ውስጥ ያልሆኑ በይነገጾችን (አብዛኛው ጊዜ «የማይደገፉ» ወይም «ኤስዲኬ ያልሆኑ በይነገጾች» የሚባሉ) እየተጠቀመ ከሆነ በቅድመ-ጅምር ሪፖርት አጠቃላይ እይታ እና እርጋታ ትሮች ላይ ስሕተቶች እና ማስጠንቀቂያዎች ተዘርዝረው ያያሉ።

ተናጠል ችግሮችን ይመልከቱ

ሥራ ላይ የዋሉትን የማይደገፉ በይነገጾች ለመለየት በቅድመ-ጅምር ሪፖርትዎ ውስጥ ከ«የሥርዓተ ክወና ተኳኋኝነት» ስሕተቶች እና ማስጠንቀቂያዎች ጎን ያሉት የችግሮችን ይመልከቱ አገናኞችን ጠቅ ያድርጉ። በመተግበሪያዎ ውስጥ አንድ የተወሰነ በይነገጽ የት እንደተጠራ ለማየት ከእሱ ቀጥሎ ያለውን የታች ቀስ ጠቅ ያድርጉና የቁልሎች ዱካን ይመልከቱ። አንድ በይነገጽ በአንድ ሙከራ ላይ ለበርካታ ጊዜ ሊጠራ ይችላል።

የማይደገፉ በይነገጾች በከባድነት ይመደባሉ። የእርጋታ ችግሮችን ለመከላከል የማይደገፉ በይነገጾችን ሙሉ ለሙሉ መጠቀሙን ማቆም ይመረጣል፣ ነገር ግን የትኛዎቹ ችግሮች መጀመሪያ እንደሚፈቱ ቅድሚያ ለመስጠት ምድቦቹን መጠቀም ይችላሉ።

የሚመከረው የቅድሚያ ቅደም-ተከተል እነሆ፦

  1. የተገደበ፦ በአንዳንድ ወይም ሁሉም የAndroid ስሪቶች ላይ የሚሰበሩ በይነገጾች።
  2. የማይደገፉ ነገር ግን ገደብ የተቃረበባቸው፦ በመጪ የAndroid ልቀት ላይ የሚገደቡ በትክክል እንደሚሠሩ ዋስትና የማይሰጥባቸው በይነገጾች።
  3. የማይደገፉ፣ ገደብ ያልተቃረበባቸው፦ በትክክል እንደሚሠሩ ዋስትና የማይሰጥባቸው በይነገጾች።

ማስታወሻ፦ በየእያንዳንዱ ምድብ ውስጥ በይነገጾች ውስጥ በተደጋጋሚነት መሠረት በቅደም-ተከተል ይቀመጣሉ፣ በዚህም የትኛዎቹን ችግሮች ቅድሚያ እንደሚሰጧቸው እንዲለዩ ሊያግዝዎት ይችላል።

አፈጻጸም

ለእያንዳንዱ የመሣሪያ ሞዴል እያንዳንዱ የሙከራ ማጠቃለያ የሚከተሉትን ሜትሪኮች ያካትታል፦

  • አማካኝ ክፈፎች በሰከንድ (ሚሴ)፦ ክፈፎች የሚታዩበት አማካይ ፍጥነት።
    • ማስታወሻ፦ የአማካኝ ክፈፎች በሰከንድ ውሂብ የጨዋታ ድግግሞሾችን ለሚጠቀሙ ሙከራዎች ብቻ ነው የሚገኘው።
  • አማካኝ ሲፒዩ፦ በተወሰነው የመሣሪያ ሞዴል ላይ የእርስዎ መተግበሪያ አማካኝ የሲፒዩ አጠቃቀም መቶኛ።
  • አማካኝ የተላከ አውታረ መረብ፦ በአንድ የተወሰነ የመሣሪያ ሞዴል ላይ በአንድ የአውታረ መረብ ግንኙነት ላይ በእርስዎ መተግበሪያ በሰከንድ የተላከ የባይቶች ብዛት አማካኝ።
  • አማካኝ የመጣ አውታረ መረብ፦ በአንድ የተወሰነ የመሣሪያ ሞዴል ላይ በአንድ የአውታረ መረብ ግንኙነት ላይ በእርስዎ መተግበሪያ በሰከንድ የመጣ የባይቶች ብዛት አማካኝ።
  • አማካኝ ማህደረ ትውስታ፦ በተወሰነው የመሣሪያ ሞዴል ላይ በተመረጠው የጊዜ ክልል ላይ በእርስዎ መተግበሪያ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለ ማህደረ ትውስታ አማካኝ።

ማስታወሻ፦ አንዳንድ የቆዩ የAndroid ስሪቶችን የሚያስኬዱ የሙከራ መሣሪያዎች የአፈጻጸም ውሂብን ማመንጨት አይችሉ ይሆናል።

ተናጠል ሪፖርቶችን ይመልከቱ

የመሣሪያውን ዝርዝር መገለጫዎች፣ የአፈጻጸም ስታትስቲክስ፣ የአፈጻጸም ትርፍ ጊዜ እና ከሙከራ ላይ የቅጽበታዊ ገጽ እይታና ቪዲዮ ለማየት የእያንዳንዱን መሣሪያ ሞዴል ይምረጡ። እንዲሁም በሙሉው የሙከራ ጊዜ ላይ የተሳለውን እያንዳንዱን የሜትሪክ ግራፍ እና መዝገብን መመልከት ይችላሉ። 

ለምሳሌ፣ ሙከራው በሂደቱ ሲቀጥል የመተግበሪያዎን ሲፒዩ መቶኛ ለመመልከት ይችላሉ። ድንገተኛ የሲፒዩ ሥራ መብዛት እንዳለ ካስተዋሉ ችግሩን ለመፍታት ጎብኚው በዚያን ጊዜ የወሰደውን እርምጃ ይገምግሙ።

የእነዚህ ዝርዝሮች ተገኝነት ሊለያይ እንደሚችል ልብ ይበሉ።

ተደራሽነት

እያንዳንዱ የሙከራ ማጠቃለያ በሙከራ ጊዜ የተገኙ የስህተቶች ብዛትን፣ ማስጠንቀቂያዎችን እና ቀላል ችግሮችን በሚከተሉት ምድቦች ለይቶ ያካትታል፦

  • የይዘት አሰያየም፦ ለማያ ገጽ አንባቢዎች በትክክል ያልተሰየሙ በእርስዎ መተግበሪያ ውስጥ ያሉ አባለ ነገሮች።
  • የንክኪ ዒላማ መጠን፦ የሚመከረውን የንክኪ ዒላማ መጠን የማያሟሉ በእርስዎ መተግበሪያ ውስጥ ያሉ አባለ ነገሮች።
  • ትግበራ፦ የአቀማመጥ ችግሮች የእርስዎን መተግበሪያ የመንቀሳቀስ ችግር ላለባቸው ተጠቃሚዎች ለመጠቀም አስቸጋሪ እንዲሆንባቸው ሊያደርግ ይችላል።
  • አነስተኛ ንጽጽር፦ አነስተኛ ንጽጽር ቀለም ችግሮች በእርስዎ መተግበሪያ ውስጥ።

ሪፖርቶችን በምድብ አሳይ

በእርስዎ መተግበሪያ ውስጥ የተደራሽነት ችግሮች ለይተው ከሚያሳዩ የማያ ገጽ ክፍሎች ጋር በምድብ የተለዩ ክፍሎችን ለመመልከት ከተደራሽነት ትር አናት ላይ ካለው አጭር ማጠቃለያ ሥር መሸብለል ይችላሉ።

  • ማናቸውም ዓይነት ችግሮች ተለይተው ከታወቁ ቀይ አዶ ይመለከታሉ።
  • ማናቸውም ማስጠንቀቂያዎች ተለይተው ከታወቁ ቢጫ አዶ ይመለከታሉ።
  • ቀላል ችግሮች ብቻ ተለይተው ከታወቁ ሰማያዊ አዶ ይመለከታሉ።
  • ምንም ዓይነት ችግሮች ተለይተው ካልታወቁ አረንጓዴ የትክክል ነው ምልክት ይመለከታሉ።

ተናጠል ችግሮችን ይመልከቱ

ከተዛማጅ የመሣሪያ ሞዴል ስሞች፣ ሥርዓተ ክወናዎች፣ የማያ ገጽ መጠኖች፣ የማያ ገጽ ትፍገቶች፣ እና ቋንቋዎች ከምክር ጋር ቅጽበታዊ ማያ ገጾችን ምሳሌ ለማየት የማያ ገጽ ስብስብ ላይ ጠቅ ማድረግ ይችላሉ።

የእርስዎን መተግበሪያ ተደራሽነት ያሻሽሉ

ቅጽበታዊ ገጽ ዕይታዎች

የእርስዎ ቅጽበታዊ ገጽ ዕይታዎች ሙከራ አጭር ማጠቃለያ እነዚህን ያቀርባል፦ 

  • የእርስዎ መተግበሪያዎች በተለያዩ ቋንቋዎች እንዴት በሙከራ መሣሪያዎች ላይ ሆኖ እንደሚታይ የሚያሳዩ ምስሎች።
  • ስለተሞከሩ መሣሪያዎች ያለ ዲበ ውሂብ (የሞዴል ስም፣ የAndroid ስሪት፣ ቋንቋ፣ የገጽ እይታ የምስል ጥራት እና ዲፒአይ ጨምሮ)።
  • ቅጽበታዊ ገጽ ዕይታዎች ያላቸው የመሣሪያዎች ብዛት።
  • በእርስዎ የAndroid መተግበሪያ ቅርቅብ ሊሞከሩ የማይችሉ መሣሪያዎች ብዛት፦
    • መሣሪያዎች አይገኙም፦ የእርስዎ የመተግበሪያ ቅርቅብ ከእነዚህ መሣሪያዎች ጋር ተኳሃኝ ነው ነገር ግን በሙከራ ጊዜ አንድ ችግር ነበር። የእርስዎ ሙከራ ማናቸውም የማይገኙ መሣሪያዎች ከነበሩት ሌላ የመተግበሪያ ቅርቅብ መስቀል እና እንደገና መሞክር ይፈልጉ ይሆናል።
    • ተኳሃኝ ያልሆኑ መሣሪያዎች፦ የእርስዎ የመተግበሪያ ቅርቅብ ከተወሰኑ የሙከራ መሣሪያዎች ጋር ተኳሃኝ አይደለም። እንደገና የሚሞክሩ ከሆነ ተኳሃኝ ላልሆኑ ማናቸውም መሣሪያዎች ውጤቶችን አይቀበሉም።

ማስታወሻ፦ እርስዎ የማሳያ ምልልሶችን በመጠቀም ሙከራ የሚያሄዱ ከሆነ በቅጽበታዊ ገጽ ዕይታዎች ትሩ ላይ ምንም ውሂብ አይመለከቱም።

ቅጽበታዊ ገጽ ዕይታዎችን የሚመለከቱባቸው መንገዶች

የቅጽበታዊ ገጽ ዕይታ ሙከራ ውጤቶችን በላይኛው ቀኝ ጥግ ላይ ያለውን ከቅጽበታዊ ገጽ ዕይታዎች አጠገብ ያለውንቦድን በ መራጭ በመጠቀም መቦደን ይችላሉ። የእርስዎን ቅጽበታዊ ገጽ ዕይታዎች ለመቦደን የሚያስችሉ ሁለት መንገዶች አሉ፦

  • የማያ ገጽ እጅብታዎች፦ ተመሳሳይ ቅጽበታዊ ገጽ እይታዎች እንዴት በተለያዩ መሣሪያዎች ላይ ሆነው እንደሚታዩ ለማየት የማያ ገጽ እጅብታዎችን ይመልከቱ። በዚህ ዕይታ አማካኝነት የቅድመ-ጅምር ሪፖርሩ ምስሎቹን በማያ ገጹ ላይ ባሉ ክፍለ-አባላት ወይም ንዑስ ፕሮግራሞች ላይ ተመስርቶ ይመድባቸዋል። የማያ ገጽ እጅብታዎች በነባሪነት ይመረጣሉ።
  • መሣሪያዎች፦ ከአንድ የተወሰነ መሣሪያ ጋር የተጎዳኙ ሁሉንም ቅጽበታዊ ገጽ እይታዎችን ለመመልከት መሣሪያዎች ይምረጡ። በዚህ ዕይታ አማካኝነት አንድ ሙከራ በሚደረግበት ጊዜ ቅጽበታዊ ገጽ ዕይታዎችን በተነሱበት የጊዜ ቅደም-ተከተል መሠረት ያያሉ።

የመሣሪያውን ዝርዝር መግለጫ እና ተጨማሪ መረጃ ለመመልከት ቅጽበታዊ ገጽ ዕይታን መምረጥ ይችላሉ።

የቋንቋ ምርጫዎች

የተወሰኑ የቋንቋዎች ቅጽበታዊ ገጽ ዕይታዎችን ለማየት በቅንብሮች ትር ላይ የቋንቋ ምርጫዎችን ማቀናበር ይችላሉ።

ደኅንነት እና እምነት

እያንዳንዱ የሙከራ ማጠቃለያ በእርስዎ የመተግበሪያ ቅርቅብ ውስጥ የሚገኙትን ማናቸውንም የደህንነት ስጋት ተጋላጭነቶች ስም እና መግለጫ ያካትታል።

ማስታወሻ፦ የእርስዎን የመተግበሪያ ቅርቅብ ወደ ምርት ከማተምዎ በፊት ማናቸውም የተዘረዘሩ የደኅንነት ተጋላጭነቶችን በተመለከተ እርምጃ እንዲወስዱ አጥበቀን እንመክርዎታለን።

በFirebase ሙከራ ቤተ-ሙከራ አማካኝነት ብጁ ሙከራ ይፍጠሩ

የእርስዎ መተግበሪያ ወይም ጨዋታ ተጨማሪ ልዩ ሙከራ የሚያስፈልገው ከሆነ የFirebase የሙከራ ቤተ-ሙከራን መጠቀም ከግምት ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። የእርስዎን የFirebase ፕሮጄክት ከፈጠሩ በኋላ ብጁ ሙከራዎችን ለመፍጠር ከብዙ ተጨማሪ መሣሪያዎች ውስጥ የመሣሪያዎን ዓይነት እና የሙከራ ዘዴዎችዎን መምረጥ ይችላሉ። ከዚያ በFirebase መሥሪያው ውስጥ የብጁ ሙከራ ውጤቶችን ማሄድ እና መመልከት ይችላሉ። እርስዎ በቀን የሚያሄዷቸው የመጀመሪያዎቹ 5-15 ሙከራዎች ነፃ ናቸው።

ተዛማጅ ይዘት

  • Play አካዳሚ ውስጥ ችግሮችን ለመለየት እንዴት የቅድመ-ጅምር ሪፖርትን መጠቀም እንደሚችሉ የበለጠ ይወቁ።

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?

ተጨማሪ እገዛ ያስፈልግሃል?

እነዚህን ቀጣይ እርምጃዎች ይሞክሩ፦

ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
4238402580182115127
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
92637
false
false