ለአዲስ የግል የገንቢ መለያዎች የሚሆኑ የመተግበሪያ ሙከራ መስፈርቶች

ኖቬምበር 2023 ውስጥ ገንቢዎች መተግበሪያቸውን እንዲሞክሩ፣ ችግሮችን ለይተው እንዲያውቁ፣ ግብረመልስ እንዲያገኙ እና ከማስጀመራቸው በፊት ሁሉም ነገር ዝግጁ እንደሆነ እንዲያረጋግጡ ለማገዝ Google Play ላይ አዳዲስ መተግበሪያዎችን ለማተም መስፈርቶቹን እየለወጥን ነው። እነዚህ ለውጦች ከኖቬምበር 13 2023 በኋላ የተፈጠሩ የግል መለያዎች ያሏቸው ገንቢዎች መተግበሪያቸውን በGoogle Play ላይ እንዲገኝ ከማድረጋቸው በፊት የተወሰኑ የሙከራ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ ይጠይቃሉ።

ይህ ዘገባ Play Console ውስጥ ያሉትን የተለያዩ የሙከራ ትራኮች እና መተግበሪያዎቻቸው Google Play ላይ እንዲገኙ ለማድረግ የግል መለያዎች ያሏቸው ገንቢዎች መውሰድ የሚያስፈልጓቸውን እርምጃዎች የያዙትን አዳዲስ መስፈርቶች አጠቃላይ ዕይታ ያቀርባል።

አዲስ ለተፈጠሩ የግል መለያዎች የሚሆኑ የሙከራ መስፈርቶችን በማስተዋወቅ ላይ

ሙከራ የመተግበሪያ ግንባታ ሂደቱ እጉር አካል ነው። በወጥነት መተግበሪያዎ ላይ ሙከራዎችን በማሄድ እሱን በይፋ ከመልቀቅዎ በፊት የመተግበሪያዎን ትክክለኛነት፣ ተግባራዊ ባህሪ እና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይችላሉ። ይህ ማናቸውም ቴክኒካዊ ወይም የተጠቃሚ ልምድ ችግሮች የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ ይቀንሳል እና የመተግበሪያዎን ምርጥ ስሪት እንዲለቅቁ ያግዝዎታል። መተግበሪያዎቻቸውን ከማተማቸው በፊት የPlay Console የሙከራ መሣሪያዎችን በመደበኛነት የሚጠቀሙ ገንቢዎች በGoogle Play ላይ ከፍተኛ ደረጃ አሰጣጦች እና የበለጠ ስኬት ማስገኘት የሚችሉ ከፍተኛ ጥራት ያሏቸውን ተሞክሮዎችን ማቅረብ ይችላሉ።

ሁሉም ገንቢዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን መተግበሪያዎች እንዲያቀርቡ ለማገዝ አዳዲስ የሙከራ መስፈርቶችን እያስተዋወቅን ነው። ከኖቬምበር 13 2023 በኋላ የተፈጠሩ የግል መለያዎች ያሏቸው ገንቢዎች እነዚያ መተግበሪያዎች Google Play ላይ ለስርጭት እንዲታተሙ ብቁ ከመሆናቸው በፊት መተግበሪያዎቻቸውን መሞከር ያስፈልጋቸዋል። Play Console ላይ እንደ ምርት (ልቀት > ምርት) እና ቅድመ-ምዝገባ (ልቀት > ሙከራ > ቅድመ-ምዝገባ) ያሉ አንዳንድ ባህሪያት ገንቢዎች እነዚህን መስፈርቶች እስከሚያሟሉ ድረስ ይሰናከላሉ።

የሙከራ መስፈርቶች አጠቃላይ ዕይታ

አዲስ የተፈጠረ የግል የገንቢ መለያ ካለዎት ለመተግበሪያዎ ቢያንስ ላለፉት 14 ቀናት በቀጣይነት መርጠው የገቡ ቢያንስ 20 ሞካሪዎች ላይ ዝግ ሙከራ ማሄድ አለብዎት። እነዚህን መስፈርት ሲያሟሉ በመጨረሻ መተግበሪያዎን Google Play ላይ ማሰራጨት እንዲችሉ Play Console ላይ ባለው ዳሽቦርድ ውስጥ ለምርት መዳረሻ ማመልከት ይችላሉ። በሚያመለክቱበት ጊዜ መተግበሪያዎን፣ የሙከራ ሂደቱን እና የምርት ዝግጁነቱን ለመረዳት እንዲያግዘን አንዳንድ ጥያቄዎችን መመለስ አለብዎት።

ከታች ስለተለያዩ የሙከራ ትራኮች ዓይነቶች እና ለእያንዳንዳቸው መስፈርቶችን በዝርዝር ማንበብ እና ለምርት መዳረሻ ስለማመልከት ተጨማሪ ዝርዝሮችን ማግኘት ይችላሉ።

የተለያዩ የሙከራ ትራኮችን እና መስፈርቶቻቸውን መረዳት

Play Console ቀስ በቀስ ሙከራን ከፍ ለማድረግ እና መተግበሪያዎ Google Play ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ጋር ለመድረስ ዝግጁ ወደሚሆንበት ነጥብ ማሻሻል እንዲችሉ የተለያዩ የሙከራ ትራኮች ዓይነቶችን ያቀርባል።

  • ውስጣዊ ሙከራ፦ መተግበሪያዎን ማዋቀር ከመጨረስዎ በፊት ለራስዎ ታማኝ ሞካሪዎች ትንሽ ቡድን ግንቦችን በፍጥነት ማሰራጨት ይችላሉ። ይህ ችግሮችን ለይቶ ለማወቅ እና ቀደም ያለ ግብረመልስ ለማግኘት ሊያግዝዎት ይችላል። ግንቦች ወደ Play Console እንደታከሉ በሰከንዶች ውስጥ ለተጠቃሚዎች በመደበኛነት ይገኛሉ። ውስጣዊ ሙከራ አማራጭ ነው፣ ነገር ግን እዚህ እንዲጀምሩ እንመክራለን።
  • ዝግ ሙከራ፦ በዝግ ሙከራ መተግበሪያዎን እርስዎ ከሚቆጣጠሩት ሰፊ የተጠቃሚዎች ቡድን ጋር ማጋራት ይችላሉ። ይህ ከማስጀመርዎ በፊት ችግሮችን እንዲያስተካክሉ እና መተግበሪያዎ የGoogle Play መመሪያን እንደሚያከብር እንዲያረጋግጡ ያስችልዎታል። መተግበሪያዎ ለምርት እንዲታተም ማመልከት ከመቻልዎ በፊት ዝግ ሙከራ ማሄድ አለብዎት። ለምርት መዳረሻ በሚያመለክቱበት ጊዜ ቢያንስ 20 ሞካሪዎች ወደ ዝግ ሙከራዎ መርጠው መግባት አለባቸው። እነሱ በቀጣይነት ላለፉት 14 ቀናት መርጠው እንደገቡ መቆየት አለባቸው። አንዴ መተግበሪያዎን አዋቅረው ከጨረሱ በኋላ ዝግ ሙከራ መጀመር ይችላሉ።
  • ክፍት ሙከራGoogle Play ላይ የመተግበሪያዎን የሙከራ ስሪት እንዲያሳዩ ያስችልዎታል። ክፍት ሙከራ ካሄዱ ማንኛውም ሰው የሙከራ ፕሮግራምዎን መቀላቀል እና ለእርስዎ የግል ግብረመልስ ማስገባት ይችላል። ይህን አማራጭ ከመምረጥዎ በፊት የእርስዎ መተግበሪያ እና የመደብር ዝርዝር Google Play ላይ ለመታየት ዝግጁ መሆኑን ያረጋግጡ። ክፍት ሙከራ የምርት መዳረሻ ሲኖርዎት ይገኛል።
  • ምርት፦ መተግበሪያዎን Google Play ላይ በቢሊዮኖች ለሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች እንዲገኝ የሚያደርጉበት ቦታ። መተግበሪያዎ ለምርት እንዲታተም ማመልከት ከመቻልዎ በፊት መስፈርታችንን የሚያሟላ ዝግ ሙከራ ማሄድ ያስፈልግዎታል። በሚያመለክቱበት ጊዜ ስለ ዝግ ሙከራዎ አንዳንድ ጥያቄዎችን መመለስ ያስፈልግዎታል። ለምርት መዳረሻ በሚያመለክቱበት ጊዜ ቢያንስ 20 ሞካሪዎች ወደ ዝግ ሙከራዎ መርጠው መግባት አለባቸው። እነሱ በቀጣይነት ላለፉት 14 ቀናት መርጠው እንደገቡ መቆየት አለባቸው።
በየትራኩ ያሉ የሙከራ መስፈርቶች ማጠቃለያ

እያንዳንዱ ትራክ ለምን እንደሆነ እና እያንዳንዱን ትራክ ለመድረስ መስፈርቶቹ (ካሉ) ምን እንደሆኑ በፍጥነት ለመፈተሽ እና ዋቢ ለማድረግ ከታች ያለው ሰንጠረዥ አጋዥ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ።

የትራክ ዓይነቶች ዓላማ ይህን ትራክ ለመድረስ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
ውስጣዊ ሙከራ ችግሮችን ለይቶ ለማወቅ በፍጥነት ግንቦችን ለራስዎ ታማኝ ሞካሪዎች ትንሽ ቡድን ለማሰራጨት እና ቀደም ያለ ግብረመልስ (መተግበሪያዎን አዋቅረው ከመጨረሰዎ በፊት ወይም ከጨረሱ በኋላ) ለማግኘት። ምንም።
ዝግ ሙከራ ከማስጀመርዎ በፊት ችግሮችን ማስተካከል እና የመተግበሪያዎን የGoogle Play መመሪያዎች እንደሚያከብር ማረጋገጥ እንዲችሉ እርስዎ ለሚቆጣጠሩት ሰፊ የተጠቃሚዎች ቡድን መተግበሪዎን ለማጋራት። መተግበሪያዎን አዋቅረው መጨረስ አለብዎት።
ክፍት ሙከራ

Google Play ላይ የመተግበሪያዎን የፍተሻ ስሪት ለማሳየት — ማንኛውም ሰው የፍተሻዎን መቀላቀል እና ለእርስዎ የግል ግብረመልስ ማስገባት ይችላል።

ክፍት ሙከራን ለመድረስ የምርት መዳረሻን ማግኘት አለበት።
ምርት መተግበሪያዎን Google Play ላይ ላሉ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች እንዲገኝ ለማድረግ።

ለምርት መዳረሻ ማመልከት ከመቻልዎ በፊት ለ14 ቀናት ቢያንስ 20 ሞካሪዎች መርጠው የገቡበትን ዝግ ሙከራ ማሄድ አለብዎት።

አንዴ መስፈርቱን ካሟሉ በኋላ ስለ ሙከራዎ፣ መተግበሪያዎ እና Play Console ውስጥ ስላለው የምርት ዝግጁነት አንዳንድ ጥያቄዎችን በመመለስ ለምርት መዳረሻ ማመልከት ይችላሉ።

ለዝግ ሙከራ የሚሆን መመሪያ እና ምርጥ ልምምዶች

ከዚህ በታች ባሉት አጋዥ አገናኞች በኩል የAndroid መተግበሪያዎችዎን በGoogle ላይ እንዴት እንደሚነድፉ፣ እንደሚገነቡ እና እንደሚያሰራጩ ማወቅ ይችላሉ፦

ሞካሪዎችን መመልመል

ሞካሪዎችን ለመመልመል በጣም የተለመደው መንገድ የግል እና የባለሙያ አውታረመረቦችን መጠቀም ነው። ለምሳሌ፣ ከእርስዎ ጓደኞች ቤተሰብ፣ የሥራ ባልደረቦች ወይም የክፍል ጓደኞች ጋር መገናኘት እና ለመተግበሪያዎ የቅድመ-ይሁንታ ሞካሪዎች እንዲሆኑ መጠየቅ ይችላሉ። ተጠቃሚዎች ሊኖሩባቸው የሚችሉባቸውን ማህበረሰቦች ማግኘት እና መተግበሪያዎን ለመሞከር ገቢር በሆነ መልኩ ሊመለምሏቸው ይችላሉ። ለምሳሌ፣ ለCrossFit ከፍተኛ አድናቂዎች መተግበሪያ እየገነቡ ከሆነ ወደ አካባቢያዊ ክለብ መቅረብን ወይም በመስመር ላይ ቡድኖች ውስጥ ካሉ የዒላማ ተጠቃሚዎችዎ ጋር መገናኘትን ከግምት ውስጥ ያስገቡ። እንዲሁም ስለ መተግበሪያዎ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ መለጠፍ እና የእርስዎን ተከታዩች ለሙከራ እንዲመዘገቡ መጠየቅ ይችላሉ።

የሚቻል ከሆነ ሳንካዎችን እና ለአንዳንድ የተጠቃሚዎች ወይም መሣሪያዎች ዓይነቶች የተወሰኑ ሊሆኑ የሚችሉ የተጠቃሚነት ችግሮችን ለይቶ ለማወቅ ብዝሃነት ያለው የሞካሪዎች ቡድን መመልመል ይኖርብዎታል። ለዚህ ተመሳሳይ ምክንያት የመተግበሪያዎን የወደፊት ተጠቃሚዎች ይወክላሉ በለው ያመኑባቸውን ሞካሪዎች መመልመል ይኖርብዎታል። ለምሳሌ፣ ለንግድ የምርታማነት መተግበሪያ እየገነቡ ከሆነ መተግበሪያዎ ታዋቂ ሊሆን ይችላል ብለው ከሚያምኑባቸው የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የመጡ የንግድ ባለሙያዎችን መመልመል ይኖርብዎታል። የሙከራ ተጠቃሚዎችዎ ወደ ዒላማ ተጠቃሚዎችዎ በቀረቡ ቁጥር የሚቀበሉት ግብረመልስ ይበልጥ ጠቃሚ ይሆናል።

ከሞካሪያዎች ጋር መሳተፍ

አንዴ የቅድመ-ይሁንታ ሞካሪዎችን ከመለመሉ በኋላ መተግበሪዎን እንዴት መሞከር እና ሳንካዎችን ሪፖርት ማድረግ እንዳለባቸው ለእነሱ ግልጽ መመሪዎችን ማቅረብ አስፈላጊ ነው። እርስዎ ምን ዓይነት ግብረመልስ እየፈለጉ እንደሆነ ሞካሪዎችዎ እንዲያውቁ ያድርጉ። ሁለገብ ግብረመልስ ለመቀበል ሞካሪዎች የተቻለውን ያህል ብዙ የመተግበሪያዎን ስሪቶች እንዲጠቀሙ ለማበረታታ ይሞክሩ።

የግብረመልስ ሰርጥ ያካትቱ ወይም ተጠቃሚዎችዎ እንዴት ለእርስዎ ግብረመልስ ማቅረብ እንደሚችሉ ያሳውቁ (ለምሳሌ በኢሜይል፣ በድር ጣቢያ ወይም በመልዕክት መድረክ)። እንዲሁም ሞካሪዎችዎ በGoogle Play በኩል ለእርስዎ የግል ግብረመልስ ማቅረብ ይችላሉ።

አስፈላጊ፦ ለሞካሪዎችዎ ቢያንስ ለ14 ቀናት ዝግ ሙከራዎ ውስጥ መርጠው እንደገቡ መቆየት እንደሚያስፈልጋቸው ትኩረት ይስጧቸው።

የተጠቃሚ ግብረመልስን መሰብሰብ እና ማየት

በሙከራ ውስጥ ያለ አንድ መተግበሪያ ካለዎት Play Console ውስጥ የተጠቃሚን ግብረመልስ መድረስ እና መልስ መስጠት ይችላሉ። ተጠቃሚዎች የመጣ ግብረመልስ የሚታየው ለእርስዎ ብቻ ነው እና Google Play ላይ መታየት አይችልም።

  1. Play Console ይክፈቱ እና ወደ የሙከራ ግብረመልስ ገፅ (የደረጃ አሰጣጦች እና ግምገማዎች > የሙከራ ግብረመልስ) ይሂዱ።
  2. የእርስዎን ግብረመልስ እንዴት ማሰስ እንደሚፈልጉ ይወስኑ።
    • ማጣሪያ:- የቅድመ ይሁንታ ግብረመልስን በተወሰነ መስፈርት (ለምሳሌ ቀን፣ ቋንቋ፣ የመልስ ሁኔታ፣ የመተግበሪያ ስሪት፣ መሣሪያ እና ሌሎችም) መሠረት ለመመልከት ከሚገኙት ማጣሪያዎች መካከል ይምረጡ።
    • ፍለጋ፦ በእርስዎ ግብረመልስ ውስጥ የተወሰኑ ቃላትን ለመፈለግ የፍለጋ ሳጥኑን ይጠቀሙ።
ጠቃሚ ምክር፦ የሚቀበሉትን ግብረመልስ መዝገብ ያስቀምጡ። ይህን ቆይተው እንደገና ማንበብ መተግበሪያዎን ለማሻሻል የተለመዱ የግብረመልስ ገጽታዎችን ወይም ለመፍታት የሚፈልጉትን አጭር ወይም የረዥም ጊዜ ችግሮችን ለይቶ ማወቅን ቀላል ሊያደርግ ይችላል። እንዲሁም ቆይተው ለምርት መዳረሻ በሚያመለክቱበት ጊዜ የሙከራ ግብረመልስዎን እንዲያጠቃልሉ እንጠይቅዎታለን።

በተጠቃሚ ግብረመልስ ላይ እርምጃ መውሰድ

በመላው የመተግበሪያዎ የሙከራ ጊዜ ላይ ለሞካሪዎችዎ ግብረመልስ ምላሽ ሰጪ መሆን እና የሚያገኟቸውን ማናቸውም ሳንካዎች ማስተካከልዎን ያረጋግጡ። ይህ የሚከተሉትን ያደርጋል፦

  • የመተግበሪያዎን የተጠቃሚ ልምድ ለማሻሻል ያግዛል፤
  • የተሳካ የምርት መዳረሻ ማመልከቻ የመኖር ዕድሉን ይጨምራል፤ እና
  • መተግበሪያዎን Google Play ላይ ማሰራጨት ሲጀምሩ አሉታዊ ግምገማዎችን ለማስወገድ የበለጠ ዕድል ይሰጣል

የላቀ ሙከራ

በዚህ ዘገባ ውስጥ ያለው መመሪያ የመጀመሪያ መተግበሪያዎን ለማሰራጨት በሚዘጋጁበት ጊዜ የሙከራ መሰረታዊ ነገሮችን ለመረዳት የሚያግዝዎ መነሻ ነጥብ ብቻ ነው። እንደ ገንቢ የበለጠ ልምድ እየጨመሩ የመተግበሪያዎን ጥራት ለማትባት ይበልጥ የላቁ የሙከራ ንብረቶችን እና ቴክኒኮችን ማሰስ ይችላሉ። ለምሳሌ፣ የAndroid ገንቢዎች ጣቢያው ላይ Android ላይ ያሉ የሙከራ መተግበሪያዎች እና የሙከራ መሰረታዊ ነገሮችን በተመለከት ማወቅ ሊፈልጉ ይችላሉ።

እንዲሁም Play Console መተግበሪያዎ ያሉትን ችግሮች ለይቶ ለማወቅ የሚያስችልዎትን የባህሪያት ክልል ያቀርባል። እርስዎ መመርመር እና መፍታት ሊፈልጉ የሚችሉት የዝርዝር ችግሮችን፣ ማስጠንቀቂያዎች እና ስህተቶች በመዘርዘር በተዘረዘረ ሪፖርት አማካኝነትመተግበሪያዎ ተጠቃሚዎችን ከመድረሱ በፊት በንቃት ችግሮችን ለይቶ ለማወቅየቅድመ-ጅምር ሪፖርት ማዋቀር እና ማሄድ ይችላሉ።

ዝግ መከራዎችን ማሄድ

ይህን የእገዛ ማዕከል ገፅ በመጠቀም ዝግ ሙከራን እንዴት ማዋቀር እና ማሄድ እንደሚችሉ ማወቅ ይችላሉ።

ለምርት መዳረሻ ያመልክቱ

አንዴ የዝግ ሙከራ መስፈርቶቹን ካሟሉ በኋላ የምርት መዳረሻ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ። ለመጀመር፦

  1. ወደ ዳሽቦርድ ይሂዱ።
  2. ለምርት ያመልክቱ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።

ከዚያ ስለ ዝግ ሙከራዎ፣ መተግበሪያዎ እና ምርቱ ዝግጁነት የሚከተሉትን ጥያቄዎች መመለስ አለብዎት። እነዚህ ጥያቄዎች በሦስት ክፍሎች ይከፋፈላሉ፦

  • ስለ ዝግ ሙከራዎ
  • ስለ መተግበሪያዎ/ጨዋታዎ
  • የምርት ዝግጁነት

ከታች ያሉትን ክፍሎች በመዘርጋት ለእያንዳንዱ ክፍል መረጃን ለማቀረብ መመሪያ ማግኘት ይችላል።

ክፍል 1፦ ስለ ዝግ ሙከራዎ ይንገሩን

«ስለ ዝግ ሙከራዎ» ክፍሉ ውስጥ የሚያቀርቡት መርጃ መተግበሪያዎች Google Play ላይ ከመታተማቸው በፊት በአጥጋቢ ሁኔታ እንደተሞከሩ ለማረጋገጥ ያግዘናል። ይህ ተጠቃሚዎችን ዝቅተኛ ጥራት ካላቸው መተግበሪዎች ለመጠበቅ፣ የተንኮል አዘል ዌር ስርጭትን ለመከላከል እና ማጭበርበርን ለመቀነስ ያግዘናል።

ይህን ክፍል ለማጠናቀቅ ማጋራት የሚያስፈልጉዎት ነገሮች እነሆ፦

  1. ከተዘረዘሩት አማራጮች አንዱን በመምረጥ ለመተግበሪያዎ ሞካሪዎችን መመልመል እንዴት ቀላል ሆኖ እንዳገኙት ያሳውቁን። ይህ ገንቢዎች እንዴት የGoogle Play ሙከራ መስፈርቶችን ተሞክሮ እያገኙባቸው እንደሆነ ለመረዳት ያግዘናል።
  2. በዝግ ሙከራዎ ወቅት ከሞካሪዎችዎ ስላገኙት ተሳትፎ መረጃ ያቅርቡ። እዚህ አግባብነት ያለው መረጃ ምሳሌዎች የሚከተሉትን ያካትታል፦
    • ሞካሪዎች ሁሉንም የመተግበሪያዎን ባህሪያት እንደተጠቀሙ
    • የምርት ተጠቃሚ መተግበሪያዎን እንዴት እንደሚጠቀም ከሚጠብቁት ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር የሞካሪዎችዎ አጠቃቀም ወጥ እንደነበር እና ካልሆነ ደግሞ ለማየት የሚጠብቋቸውን ልዩነቶች።
  3. በመጨረሻም ከሞካሪዎች የተቀበሉትን ግብረመልስ ያጠቃልሉ እና ይህን ግብረመልስ እንዴት እንደሰበሰቡ ያሳውቁን።
  4. ቀጣይ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።
    • አስፈላጊ፦ ቀጣይ የሚለውን ሳይመርጡ እና ለምርት መዳረሻ ማመልከቻዎን ሳይጨርሱ አሰናክል ወይም አቁም የሚለውን ጠቅ ካደረጉ ለውጦችዎ አይቀመጡም።
ክፍል 2፦ ስለ መተግበሪያዎ/ጨዋታዎ ይንገሩን

«ስለ መተግበሪያዎ/ጨዋታዎ» ክፍሉ ውስጥ የሚያቀርቡት መረጃ መተግበሪያዎን ወይም ጨዋታዎን በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ስለ መተግበሪያዎ ወይም ጨዋታዎ ይበልጥ አግባብነት ያለውን መረጃ እንድናውቅ ያግዘናል። መልሶችዎ Google Play ላይ አይታዩም እና Play Console ውስጥ መድረስ የሚችሏቸው ባህሪያት እና አገልግሎቶች፣ መተግበሪያዎ ወይም ጨዋታዎ እንዴት እንደሚታይ ወይም ለGoogle Play ገንቢ ፕሮግራሞች ባለዎት ብቁነት ላይ ተጽዕኖ አይፈጥሩም።

ይህን ክፍል ለማጠናቀቅ ማጋራት የሚያስፈልጉዎት ነገሮች እነሆ፦

  1. የመተግበሪያዎ ወይም ጨዋታዎ የታሰበው ታዳሚ ማን እንደሆነ ያሳውቁን። እባክዎ በተቻለ መጠን በዝርዝር ይግለጹ።
  2. ሁለተኛው ጥያቄ እርስዎ የመተግበሪያ ወይም የጨዋታ ገንቢ መሆንዎ ላይ በመመስረት በትንሹ ይለያያል፦
    • ለመተግበሪያዎች፦ መተግበሪያዎ እንዴት ለተጠቃሚዎች እሴት እንደሚያቀርብ ይግለጹ። ይህን ስንል ምን ማለታችን እንደሆነ እርግጠኛ ካልሆኑ ስለ Google Play ላይ ያለ የመተግበሪያ ጥራት በተመለከተ የበለጠ ለማወቅ የAndroid ገንቢዎች ጣቢያውን ይጎብኙ።
    • ለጨዋታዎች፦ ጨዋታዎ ጎልቶ እንዲታይ የሚያደርገውን ነገር ይግለጹ።
  3. መተግበሪያዎ ወይም ጨዋታዎ በመጀመሪያ ዓመቱ ውስጥ ስንት ጭነቶች ይኖሩታል ብለው እንደሚጠብቁ ያሳውቁን። የክልል አማራጮቹ ሰፊ ናቸው፣ ስለዚህ የመሆን ዕድሉ ከፍ ይላል ብለው የሚያስቡትን አማራጭ ይምረጡ። ይህ ያልተረጋገጠ ግምት ብቻ ቢሆንም ችግር የለውም።
  4. ቀጣይ የሚለውን ጠቅ ያድርጉ።
    • አስፈላጊ፦ ቀጣይ የሚለውን ሳይመርጡ እና ለምርት መዳረሻ ማመልከቻዎን ሳይጨርሱ አሰናክል ወይም አቁም የሚለውን ጠቅ ካደረጉ ለውጦችዎ አይቀመጡም።
ክፍል 3፦ ስለ እርስዎ ምርት ዝግጁነት ይንገሩን

«ስለ ምርትዎ ዝግጁነት» ክፍሉ ውስጥ የሚያቀርቡት መረጃ መተግበሪያዎ ወይም ጨዋታዎ ለምርት ዝግጁ መሆኑን ለመረዳት ያግዘናል።

ይህን ክፍል ለማጠናቀቅ ማጋራት የሚያስፈልጉዎት ነገሮች እነሆ፦

  1. በዝግ ሙከራዎ ወቅት በተማሩት መሰረት መተግበሪያዎ ወይም ጨዋታዎ ላይ ምን ለውጦችን እንዳደረጉ ያሳውቁን።
  2. እንዴት መተግበሪያዎ ወይም ጨዋታዎ ለምርት ዝግጁ እንደሆነ እንደወሰኑ ይግለጹ።
  3. ተግብርየሚለውን ጠቅ ያድርጉ።
    • አስፈላጊ፦ ለምርት መዳረሻ ሳያመለክቱ አሰናክል ወይም አቁም የሚለውን ጠቅ ካደረጉ ለውጦችዎ አይቀመጡም።

ለምርት መዳረሻ ካመለከቱ በኋላ

ምርት የመድረስ ጥያቄዎን ካጠናቀቁ በኋላ ግቤትዎን እንገመግማለን፣ ግምገማው ሲጠናቀቅ ዝማኔ በመያዝ ለመለያ ባለቤቱ ኢሜይል እንልካለን። ይህ አብዛኛውን ጊዜ 7 ቀናት ወይም ያነሰ ይወስዳል፣ ነገር ግን አልፎ አልፎ ከዚያ የበለጠ ሊወስድ ይችላል።

መተግበሪያዎ ለመታተም ዝግጁ ካልሆነ፣ መተግበሪያዎን መሞከሩን መቀጠል ሊኖርብዎ ይችላል። ምሳሌዎችም ወደ ዝግ ሙከራዎ መርጠው የገቡ 20 ሞካሪዎች አለመኖር ወይም በዝግ ሙከራዎ ወቅት በመተግበሪያዎ ላይ ያልተሳተፉ የእርስዎ ሞካሪዎችን ያካትታሉ።

መተግበሪያዎ ስኬታማ ከሆነ ምርት (ልቀት > ምርት) መድረስ ይችላሉ እና መተግበሪያዎ ዝግጁ ነው ብለው ሲያስቡ Google Play ላይ ላሉ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች እንዲገኝ ማድረግ ይችላሉ። እንዲሁም ክፍት ሙከራ (ልቀት > ሙከራ > ክፍት ሙከራ) መጠቀም ይችላሉ። ወደ ምርት ከማተምዎ በፊት መተግበሪያዎን በሰፊው እንዲሞክሩት እና የሚያደርጓቸውን ማናቸውም የወደፊት ዝማኔዎች መሞከርን እንመክራለን።

በተደጋጋሚ የተጠየቁ ጥያቄዎች

ለምርት ከማመልከቴ በፊት ሞካሪዎች ላለፉት 14 ቀናት በቀጣይነት መርጠው መግባት አለባቸው ሲባል ምን ማለት ነው?

ይህ ማለት መርጠው የገቡ፣ ከ14 ቀናት በታች ለሚሆን ጊዜ የሞከሩ እና ከዚያ መርጠው የወጡ ሞካሪዎችን አንቆጥርም ማለት ነው። እነሱ በድምሩ 14 ቀናት ለሚሆን ጊዜ ተመልሰው መርጠው ቢገቡም እንኳን ለ14 ተከታታይ ቀናት የሞከሩ 20 መርጠው የገቡ ሞካሪዎች እንደሚለው መስፈርት ለመቆጠር እነዚህ 14 ቀናት ተከታታይ መሆን አለባቸው።

ለሙከራ አጋዥ ሆነው የማገኛቸው ተጨማሪ ምርጥ ልምምዶች አሉ?

በተጠቃሚ ሪፖርት የተደረጉ ችግሮችን እና ሳንካዎችን እያስተካከሉ ሳለ ዝግ ሙከራን መጠቀም ይቀጥሉ። ወደ ምርት ከመሄደዎ በፊት መተግበሪያዎን በዝግ ሙከራ ውስጥ ማዘመን ዝቅተኛ ጥራት ያላቸውን ግምገማዎች እና የደረጃ አሰጣጦች ለመቀነስ አሪፍ መንገድ ነው።

ግብረመልሱ በሌሎች ሰዎች መታየት እንዲችል ዝግ ሞካሪዎችዎን ወደ አንድ መልዕክት ቡድን መጋበዝን ከግምት ውስጥ ያስገቡ። እንዲሁም ሞካሪዎችዎ ተጨማሪ ግብረመልስ እና ዓምድ ሊያቀርቡ ይችላሉ፣ ይህም የትኞቹን የመተግበሪያዎ ወይም ጨዋታዎ ገጽታዎች ለማሻሻል ቅድሚያ መስጠት እንዳለብዎት ይግዝዎታል።

ብልሽቶችን እና ሳንካዎችን ከማስተካከል በተጨማሪ የመተግበሪያዎን አጠቃላይ የተጠቃሚ ልምድ መሞከርዎን ያረጋግጡ።Google Play ላይ ስለ መተግበሪያ እና ጨዋታ ጥራት የበለጠ ለመረዳት

Google Play ላይ ስኬታማ እንድሆን እንዲያግዘኝ መማር ያሉብኝ ሌሎች የPlay Console ባህሪያት አሉ?

Google Play ጣቢያ ላይ ስለ የPlay Console ባህሪያት እና የቅርብ ጊዜው Play Console ዜና የበለጠ ማወቅ ይችላሉ። እንዲሁም Google Play አካዳሚ ላይ ላሉ አዲስ እና ፍላጎት ላላቸው የመተግበሪያ ገንቢዎች በGoogle ባለሙያዎች የተነደፈ ነፃ የመስመር ላይ ሥልጠና መውሰድ ይችላሉ።

ይሄ አጋዥ ነበር?

እንዴት ልናሻሽለው እንችላለን?

ተጨማሪ እገዛ ያስፈልግሃል?

እነዚህን ቀጣይ እርምጃዎች ይሞክሩ፦

true
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
574346050760387596
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
92637
false
false