በChrome ውስጥ ኩኪዎችን ይሰርዙ፣ ይፍቀዱ እና ያስተዳድሩ

ነባር ኩኪዎችን ለመሰረዝ፣ ሁሉንም ኩኪዎች ለመፍቀድ ወይም ለማገድ እና ለተወሰኑ ድር ጣቢያዎች ምርጫዎችዎን ለማቀናበር መምረጥ ይችላሉ።

አስፈላጊ፦ የመከታተያ ጥበቃ የሙከራ ቡድን አባል ከሆኑ፣ «የመከታተል ጥበቃ» ተብሎ የሚጠራ የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለማስተዳደር አዲስ የChrome ቅንብር ያያሉ። ስለ መከታተል ጥበቃ የበለጠ ይረዱ

ኩኪዎች ምን እንደሆኑ

ኩኪዎች እርስዎ በሚጎበኟቸው ድር ጣቢያዎች የሚፈጠሩ ፋይሎች ናቸው። ስለ ጉብኝትዎ መረጃን በማስቀመጥ የመስመር ላይ ተሞክሮዎን ይበልጥ ቀላል ያደርጋሉ። ለምሳሌ ጣቢያዎች በመለያዎ እንደገቡ ሊያቆዩዎ፣ የጣቢያ ምርጫዎችዎን ሊያስታውሱ እና አካባቢያዊ አግባብነት ያለው ይዘት ሊያቀርቡልዎ ይችላሉ።

2 ዓይነት ኩኪዎች አሉ፦

  • የአንደኛ ወገን ኩኪዎች፦ በሚጎበኙት ጣቢያ የሚፈጠር። ይህ ጣቢያ በአድራሻ አሞሌው ላይ ይታያል።
  • የሦስተኛ ወገን ኩኪዎች፦ በሌሎች ጣቢያዎች የሚፈጠሩ። የሚጎበኙት ጣቢያ ከሌሎች ጣቢያዎች ይዘትን መክተት ይችላል፣ ለምሳሌ ምስሎች፣ ማስታወቂያዎች እና ጽሑፍ። ከእነዚህ ጣቢያዎች ውስጥ ማናቸውም ተሞክሮዎን ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን እና ሌላ ውሂብን ማስቀመጥ ይችላሉ።

ሁሉንም ኩኪዎች ሰርዝ

ጠቃሚ፦ ኩኪዎችን ከሰረዙ ከሚያስታውሱዎት ጣቢያዎች ዘግተው ሊወጡ ይችላሉ እና የተቀመጡ ምርጫዎችዎ ሊሰረዙ ይችላሉ። ይህ ኩኪ በሚሰረዝበት ማንኛውም ጊዜ ይተገበራል።

  1. በእርስዎ Android መሣሪያ ላይ Chromeን Chrome ይክፈቱ።
  2. ከላይ በቀኝ በኩል፣ ተጨማሪ ተጨማሪ እና በመቀጠል ቅንብሮች የሚለውን መታ ያድርጉ።
  3. ግላዊነት እና ደህንነት እና በመቀጠል የአሰሳ ውሂብ አጽዳ የሚለው ላይ መታ ያድርጉ።
  4. እንደ ያለፈው ሰዓት ወይም ሁሉም ጊዜ ያለ የጊዜ ክልልን ይምረጡ።
  5. ኩኪዎች እና የጣቢያ ውሂብ ላይ ምልከት ያድርጉ እና ሁሉም ሌሎች ንጥሎች ላይ ምልክት አያድርጉ።
  6. ውሂብን አጽዳ እና በመቀጠል አጽዳ የሚለውን መታ ያድርጉ።
ኩኪዎችን ከአንድ ጣቢያ ሰርዝ
  1. በእርስዎ Android መሣሪያ ላይ Chromeን Chrome ይክፈቱ።
  2. ወደ ድር ጣቢያ ይሂዱ።
  3. ከላይ በቀኝ በኩል፣ ተጨማሪ ተጨማሪ እና ከዚያ የገጽ መረጃ Default (Secure) እና ከዚያ ኩኪዎች እና የጣቢያ ውሂብ የሚለውን መታ ያድርጉ።
  4. በጥቅም ላይ ካሉ ኩኪዎች ቁጥር አጠገብ፣ ሰርዝ Remove የሚለውን መታ ያድርጉ።
የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ፍቀድ ወይም አግድ
አስፈላጊ፦ ጣቢያዎች ኩኪዎችን እንዲያስቀምጡ ካልፈቀዱ፣ ጣቢያዎች እርስዎ እንደሚጠብቁት ላይሰሩ ይችላሉ። የአንደኛ ወገን ኩኪዎችን ለማስተዳደር በመሣሪያ ላይ ስላለው የጣቢያ ውሂብ የበለጠ ይወቁ
ለማንኛውም ጣቢያ የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን መፍቀድ ወይም ማገድ ይችላሉ፦
  1. በእርስዎ Android መሣሪያ ላይ Chromeን Chrome ይክፈቱ።
  2. ከላይ በቀኝ በኩል፣ ተጨማሪ ተጨማሪ እና በመቀጠል ቅንብሮች የሚለውን መታ ያድርጉ።
  3. የጣቢያ ቅንብሮች እና በመቀጠል የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን መታ ያድርጉ።
  4. አንድ አማራጭ ይምረጡ፦
    • የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ይፍቀዱ
    • የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ማንነትን በማያሳውቅ ውስጥ ያግዱ
    • የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ያግዱ
      • የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ካገዱ፣ ጣቢያው በእርስዎ ለየት ያሉ ዝርዝር ውስጥ ካልተፈቀደ በስተቀር ሁሉም የሶስተኛ ወገን ኩኪዎች ታግደዋል።
የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለአንድ የተወሰነ ጣቢያ ይፍቀዱ

የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን በነባሪነት ካገዱ፣ አሁንም ለተወሰነ ጣቢያ መፍቀድ ይችላሉ።

  1. በእርስዎ Android መሣሪያ ላይ Chromeን Chrome ይክፈቱ።
  2. ከላይ በቀኝ በኩል፣ ተጨማሪ ተጨማሪ እና በመቀጠል ቅንብሮች የሚለውን መታ ያድርጉ።
  3. ግላዊነት እና ደህንነት እና በመቀጠል የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን መታ ያድርጉ።
    • ጠቃሚ ምክር፦ የመከታተል ጥበቃ የፍተሻ ቡድን አካል ከሆኑ፣ በምትኩ የመከታተል ጥበቃ የሚለውን ይምረጡ።
  4. + የጣቢያ ለየት ያለ አክል የሚለውን መታ ያድርጉ
  5. የድር አድራሻውን ያስገቡ።
    • ለአጠቃላይ ጎራው ለየት ያለ ለመፍጠር፣ ከጎራው ስም በፊት [*.] ያስገቡ። ለምሳሌ፣ [*.]google.com drive.google.com እና calendar.google.com ጋር ይዛመዳል።
    • እንዲሁም http:// በሚለው የማይጀምር የአይ ፒ አድራሻን ወይም የድር አድራሻን ማስቀመጥ ይችላሉ።
  6. አክልን መታ ያድርጉ።
ከአሁን በኋላ የማይፈልጉትን ለየት ያለን ለማስወገድ፣ ለየት ያለ የሚለውን መታ ያድርጉ እና አስወግድ የሚለውን መታ ያድርጉ።
የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለአንድ የተወሰነ ጣቢያ በጊዜያዊነት ይፍቀዱ
የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ካገዱ፣ አንዳንድ ጣቢያዎች እርስዎ እንደጠበቁት ላይሰሩ ይችላሉ። ለጎበኙት ጣቢያ የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለጊዜው መፍቀድ ይችላሉ።
  1. በእርስዎ Android መሣሪያ ላይ Chromeን Chrome ይክፈቱ።
  2. ከላይ ባለው የአድራሻ አሞሌ ውስጥ፡-
    • የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለመፍቀድ፡- የገጽ መረጃ Default (Secure) እና በመቀጠል ኩኪዎች እና የጣቢያ ውሂብ የሚለውን ይምረጡ እና የሶስተኛ ወገን ኩኪዎች የሚለውን ያብሩ።
    • የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለማገድ፡- የገጽ መረጃ Default (Secure) እና በመቀጠል ኩኪዎች እና የጣቢያ ውሂብ የሚለውን ይምረጡ እና የሶስተኛ ወገን ኩኪዎች የሚለውን ያጥፉ።

ጠቃሚ ምክሮች፦

  • ይህ አማራጭ ጊዜያዊ ብቻ እና አሁን ላሉበት ጣቢያ ብቻ ነው።
  • ጣቢያዎች በራስ-ሰር ወደ ለየት ያለ ዝርዝር ውስጥ ይታከላሉ
  • እርስዎ በጣቢያ ላይ የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለጊዜው ከፈቀዱ፣ ይህ ቅንብር ወደ ማንነት የማያሳውቅ ሁነታ ይዛወራል እና ከማንነት የማያሳውቅ ሁነታ ዳግም ማስጀመር አይችሉም።
ተያያዥነት ያላቸው ጣቢያዎች እንቅስቃሴዎን እንዲደርሱ ይፍቀዱ

አንድ ኩባንያ እርስ በእርስ ተያያዥነት ያላቸውን የጣቢያ ቡድኖች መወሰን ይችላል። ለምሳሌ አንድ ኩባንያ acme-music.example እና acme-video.example በሚሉት መካከል በሚዘዋወሩበት ጊዜ እንደገቡ እንዲቆዩ ማድረግ ሊፈልግ ይችላል።

የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ከፈቀዱ፦ ተያያዥነት ያላቸው ጣቢያዎች ይዘትን ግላዊ ለማድረግ ወይም በጣቢያዎች ዙሪያ እንደገቡ ለማቆየት እንቅስቃሴዎን እንዲደርሱ ይፈቅዳሉ።

የሦስተኛ ወገን ኩኪዎችን ካገዱ፦ አብዛኛውን ጊዜ በጣቢያዎች መካከል እንደዚህ ዓይነት ግንኙነትን ይከለክላል። ተሞክሮዎን ለማሻሻል በተመሳሳይ ቡድን ውስጥ ያሉ ጣቢያዎችን በመፍቀድ የሦስተኛ ወገን ኩኪዎችን ማገድ ይችላሉ።

ተያያዥነት ያላቸው ጣቢያዎች ቡድኖችን የሚወስኑ ኩባንያዎችን ሙሉ ዝርዝር GitHub ላይ ማግኘት ይችላሉ። ስለ ተያያዥነት ያላቸው ጣቢያዎች እና የሶስተኛ ወገን ኩኪዎች የበለጠ ይወቁ

አስፈላጊ፦ «ሁሉንም ኩኪዎች ፍቀድ» የሚለውን ከመረጡ፣ ከዚያም ተያያዥነት ያላቸው ጣቢያዎች ቡድን እንደ ነባሪ በቡድኑ ውስጥ እንቅስቃሴዎን ማጋራት ይችላል።

ተያያዥነት ያላቸው ጣቢያዎች በቡድኑ ውስጥ እንቅስቃሴዎን እንዲያዩ ለመፍቀድ፦

  1. በእርስዎ Android መሣሪያ ላይ Chromeን Chrome ይክፈቱ።
  2. ከላይ በቀኝ በኩል፣ ተጨማሪ ተጨማሪ እና በመቀጠል ቅንብሮች የሚለውን መታ ያድርጉ።
  3. የግላዊነት እና ደህንነት እና በመቀጠል የሶስተኛ ወገን ኩኪዎች እና በመቀጠል የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን አግድ መታ ያድርጉ።
  4. ተያያዥነት ያላቸው ጣቢያዎች በቡድኑ ውስጥ እንቅስቃሴዎን እንዲያዩ ይፍቀዱ የሚለውን ያብሩ ወይም ያጥፉ።

በተመሳሳይ ቡድን ውስጥ ተያያዥነት ያላቸውን ጣቢያዎች ለማሳየት፦

  1. በእርስዎ Android መሣሪያ ላይ Chromeን Chrome ይክፈቱ።
  2. ከላይ በቀኝ በኩል፣ ተጨማሪ ተጨማሪ እና በመቀጠል ቅንብሮች የሚለውን መታ ያድርጉ።
  3. የጣቢያ ቅንብሮች እና በመቀጠል ሁሉም ጣቢያዎች የሚለውን መታ ያድርጉ።
  4. አንድ ጣቢያ ይምረጡ።
  5. «የተዛመዱ ጣቢያዎች፣» ስር፣ በተመሳሳይ ቡድን ውስጥ ያሉ ጣቢያዎችን ያግኙ።

የመከታተል ጥበቃዎችዎን ያስተዳድሩ

ሲበራ፣ የመከታተል ጥበቃ መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲሰሩ ለማስቻል ውስን ጉዳዮችን ሳይጨምር እርስዎ ሲያስሱ ለመከታተል የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ከመጠቀም ጣቢያዎችን በእጅጉ ይገድባል። ከመረጡ፣ በቅንብሮችዎ ውስጥ የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ሙሉ በሙሉ ማገድ ይችላሉ። የመከታተል ጥበቃ ምርጫዎችዎን በ«ግላዊነት እና ደህንነት» ቅንብሮችዎ ውስጥ ማስተዳደር ይችላሉ።

  1. በእርስዎ Android መሣሪያ ላይ Chromeን Chrome ይክፈቱ።
  2. ከላይ በቀኝ በኩል፣ ተጨማሪ ተጨማሪ እና በመቀጠል ቅንብሮች የሚለውን መታ ያድርጉ።
  3. ግላዊነት እና ደህንነት እና በመቀጠል የመከታተል ጥበቃ የሚለውን መታ ያድርጉ።
  4. የመከታተል ጥበቃዎችዎን ለማበጀት፣ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፦
    • ሁሉም የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን አግድ፦ ይህንን እንዲበራ ሲቀይሩ፣ በአንዳንድ ጣቢያዎች ላይ ያሉ ባህሪዎች ላይሰሩ ይችላሉ። Chrome እርስዎ ከጎበኟቸው ጣቢያዎች ተዛማጅ ጣቢያዎችን ጨምሮ ሁሉንም የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ያግዳል።
    • በአሰሳ ትራፊክዎ የ«Do Not Track» ጥያቄን ይላኩ፦ ይህንን እንዲበራ ሲቀይሩ፣ ጣቢያዎች እንዳይከታተሉዎት ይጠይቃሉ። ጣቢያዎች ጥያቄውን ለማክበር ወይም ላለማክበር የግል ምርጫቸውን ይጠቀማሉ። ስለ «Do Not Track» የበለጠ ይወቁ
    • የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለመጠቀም የትኛዎቹን ጣቢያዎች እንደሚፈቅዱ ይምረጡ፦ እንዲሁም ከ«የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለመጠቀም የተፈቀደላቸው ጣቢያዎች» ስር የትኛዎቹን ጣቢያዎች የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን እንዲጠቀሙ እንደሚፈቅዱ ማረጋገጥ እና ማርትዕ ይችላሉ። እንዴት የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን መፍቀድ እንደሚችሉ ይወቁ

ተዛማጅ ግብዓቶች

ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
3416102402938011114
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
237
false
false