በChrome ውስጥ ኩኪዎችን ይሰርዙ፣ ይፍቀዱ እና ያስተዳድሩ

ነባር ኩኪዎችን ለመሰረዝ፣ ሁሉንም ኩኪዎች ለመፍቀድ ወይም ለማገድ እና ለተወሰኑ ድር ጣቢያዎች ምርጫዎችን ለማቀናበር መምረጥ ይችላሉ።

አስፈላጊ፦ የሦስተኛ ወገን ኩኪዎችን በነባሪ የሚገድበው የሙከራ ቡድን አካል ከሆኑ የሦስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለማስተዳደር የተለዩ ቅንብሮችን ሊያገኙ ይችላሉ። ለሙከራ ቡድን ተጠቃሚዎች እንዴት የሦስተኛ ወገን ኩኪ ቅንብሮችን ማስተዳደር እንደሚቻል ይወቁ

ኩኪዎች ምን እንደሆኑ

ኩኪዎች እርስዎ በሚጎበኟቸው ድር ጣቢያዎች የሚፈጠሩ ፋይሎች ናቸው። ስለ ጉብኝትዎ መረጃን በማስቀመጥ የመስመር ላይ ተሞክሮዎን ይበልጥ ቀላል ያደርጋሉ። ለምሳሌ ጣቢያዎች በመለያዎ እንደገቡ ሊያቆዩዎ፣ የጣቢያ ምርጫዎችዎን ሊያስታውሱ እና አካባቢያዊ አግባብነት ያለው ይዘት ሊያቀርቡልዎ ይችላሉ።

2 ዓይነት ኩኪዎች አሉ፦

  • የአንደኛ ወገን ኩኪዎች፦ በሚጎበኙት ጣቢያ የሚፈጠር። ይህ ጣቢያ በአድራሻ አሞሌው ላይ ይታያል።
  • የሦስተኛ ወገን ኩኪዎች፦ በሌሎች ጣቢያዎች የሚፈጠሩ። የሚጎበኙት ጣቢያ ከሌሎች ጣቢያዎች ይዘትን መክተት ይችላል፣ ለምሳሌ ምስሎች፣ ማስታወቂያዎች እና ጽሑፍ። ከእነዚህ ጣቢያዎች ውስጥ ማናቸውም ተሞክሮዎን ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን እና ሌላ ውሂብን ማስቀመጥ ይችላሉ።

ጠቃሚ ምክር፦ አንዳንድ ጣቢያዎች ኩኪዎችን እንዲቀበሉ ወይም ውድቅ እንዲያደርጉ ሊጠይቁዎት ይችላሉ።

ሁሉንም ኩኪዎች ሰርዝ

ኩኪዎችን ካስወገዱ ከድር ጣቢያዎች ዘግተው ይወጣሉ እና የተቀመጡ ምርጫዎችዎ ሊሰረዙ ይችላሉ።

  1. በእርስዎ iPhone ወይም iPad ላይ Chromeን Chrome ይክፈቱ።
  2. ተጨማሪ More እና በመቀጠል ቅንብሮች Settings ላይ መታ ያድርጉ።
  3. ግላዊነት እና ደህንነት እና በመቀጠል የአሰሳ ውሂብን አጽዳ ላይ መታ ያድርጉ።
  4. ኩኪዎች፣ የጣቢያ ውሂብ ላይ ምልክት ያድርጉ።
  5. በሌሎቹ ንጥሎች ላይ ምልክት አያድርጉ።
  6. የአሰሳ ውሂብን ሰርዝ እና በመቀጠል የአሰሳ ውሂብን ሰርዝ መታ ያድርጉ።
  7. ተከናውኗል ላይ መታ ያድርጉ።

ተዛማጅ ግብዓቶች

ተጨማሪ እገዛ ያስፈልግሃል?

እነዚህን ቀጣይ እርምጃዎች ይሞክሩ፦

ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
7980472503117187862
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
237
false
false