በChrome ውስጥ ኩኪዎችን ይሰርዙ፣ ይፍቀዱ እና ያስተዳድሩ

ነባር ኩኪዎችን ለመሰረዝ፣ ሁሉንም ኩኪዎች ለመፍቀድ ወይም ለማገድ እና ለተወሰኑ ድር ጣቢያዎች ምርጫዎችን ለማቀናበር መምረጥ ይችላሉ።

አስፈላጊ፦ የሦስተኛ ወገን ኩኪዎችን በነባሪ የሚገድበው የሙከራ ቡድን አካል ከሆኑ የሦስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለማስተዳደር የተለዩ ቅንብሮችን ሊያገኙ ይችላሉ። ለሙከራ ቡድን ተጠቃሚዎች እንዴት የሦስተኛ ወገን ኩኪ ቅንብሮችን ማስተዳደር እንደሚቻል ይወቁ

ኩኪዎች ምን እንደሆኑ

ኩኪዎች እርስዎ በሚጎበኟቸው ድር ጣቢያዎች የሚፈጠሩ ፋይሎች ናቸው። ስለ ጉብኝትዎ መረጃን በማስቀመጥ የመስመር ላይ ተሞክሮዎን ይበልጥ ቀላል ያደርጋሉ። ለምሳሌ ጣቢያዎች በመለያዎ እንደገቡ ሊያቆዩዎ፣ የጣቢያ ምርጫዎችዎን ሊያስታውሱ እና አካባቢያዊ አግባብነት ያለው ይዘት ሊያቀርቡልዎ ይችላሉ።

2 ዓይነት ኩኪዎች አሉ፦

  • የአንደኛ ወገን ኩኪዎች፦ በሚጎበኙት ጣቢያ የሚፈጠር። ይህ ጣቢያ በአድራሻ አሞሌው ላይ ይታያል።
  • የሦስተኛ ወገን ኩኪዎች፦ በሌሎች ጣቢያዎች የሚፈጠሩ። የሚጎበኙት ጣቢያ ከሌሎች ጣቢያዎች ይዘትን መክተት ይችላል፣ ለምሳሌ ምስሎች፣ ማስታወቂያዎች እና ጽሑፍ። ከእነዚህ ጣቢያዎች ውስጥ ማናቸውም ተሞክሮዎን ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን እና ሌላ ውሂብን ማስቀመጥ ይችላሉ።

ጠቃሚ ምክር፦ አንዳንድ ጣቢያዎች ኩኪዎችን እንዲቀበሉ ወይም ውድቅ እንዲያደርጉ ሊጠይቁዎት ይችላሉ።

ኮምፒውተር AndroidiPhone እና iPad

ሁሉንም ኩኪዎች ሰርዝ

ጠቃሚ፦ ኩኪዎችን ከሰረዙ ከሚያስታውሱዎት ጣቢያዎች ዘግተው ሊወጡ ይችላሉ እና የተቀመጡ ምርጫዎችዎ ሊሰረዙ ይችላሉ። ይህ ኩኪ በሚሰረዝበት ማንኛውም ጊዜ ይተገበራል።

  1. በኮምፒውተርዎ ላይ Chrome ይምረጡ።
  2. ከላይ በቀኝ በኩል ተጨማሪ ተጨማሪ እና በመቀጠል ቅንብሮች Settings የሚለውን ይምረጡ።
  3. ግላዊነት እና ደህንነት እና ከዚያ የሦስተኛ ወገን ኩኪዎች የሚለውን ይምረጡ።
  4. ሁሉንም የጣቢያ ውሂብ እና ፈቃዶች አሳይ እና በመቀጠል ሁሉንም ውሂብ ሰርዝ የሚለውን ይምረጡ።
  5. ለማረጋገጥ ሰርዝ የሚለውን ይምረጡ።

የተወሰኑ ኩኪዎችን ይሰርዙ

የእርስዎን የኩኪ ቅንብሮች ይለውጡ

አስፈላጊ፦ ጣቢያዎች ኩኪዎችን እንዲያስቀምጡ ካልፈቀዱ፣ ጣቢያዎች እንደሚጠበቀው ላይሠሩ ይችላሉ። የአንደኛ ወገን ኩኪዎችን ለማስተዳደር በመሣሪያ ላይ ስላለው የጣቢያ ውሂብ የበለጠ ይወቁ

ለማንኛውም ጣቢያ ኩኪዎችን መፍቀድ ወይም ማገድ ይችላሉ።

ለሙከራ ቡድን ተጠቃሚዎች የሦስተኛ ወገን ኩኪ ቅንብሮችን ያስተዳድሩ

ለተለዩ የተጠቃሚዎች ቡድን፣ Google በChrome ውስጥ ጣቢያዎች እርስዎ በሚያስሱበት ወቅት እርስዎን ለመከታተል የሦስተኛ ወገን ኩኪዎችን ከመጠቀም በጉልህ መልኩ የሚገድቡ ባህሪያትን እየሞከረ ነው። የሙከራ ቡድኑ አካል ከሆኑ የሦስተኛ ወገን ኩኪዎች መሠረታዊ የድር ጣቢያ አገልግሎቶች እንዲተገብሩ አስፈላጊ ካልሆኑ በስተቀር በነባሪ ይገደባሉ።

ከመረጡ፣ በቅንብሮችዎ ውስጥ የሦስተኛ ወገን ኩኪዎችን ሙሉ በሙሉ ማገድ ይችላሉ። የሦስተኛ ወገን ኩኪ ምርጫዎችዎን በእርስዎ «የግላዊነት እና ደህንነት» ቅንብሮች ውስጥ ማስተዳደር ይችላሉ።

  1. በእርስዎ ኮምፒውተር ላይ Chrome ይክፈቱ።
  2. ከላይ በቀኝ በኩል ተጨማሪ ተጨማሪ እና በመቀጠል ቅንብሮች Settings የሚለውን ይምረጡ።
  3. ግላዊነት እና ደህንነት እና በመቀጠል የሦስተኛ ወገን ኩኪዎች የሚለውን ይምረጡ።
  4. እንዲሁም የላቁ የግላዊነት ጥበቃዎችን መምረጥ ይችላሉ፦
    • ሁሉም የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን አግድ፦ ይህንን ሲያነቁ፣ በአንዳንድ ጣቢያዎች ላይ ያሉ ባህሪዎች ላይሰሩ ይችላሉ። Chrome እርስዎ ከጎበኟቸው ጣቢያዎች ተዛማጅ ጣቢያዎችን ጨምሮ ሁሉንም የሶስተኛ ወገን ኩኪዎችን ያግዳል።
    • በአሰሳ ትራፊክዎ የ«Do Not Track» ጥያቄን ይላኩ፦ ይህንን ሲቀይሩ፣ ጣቢያዎች እንዳይከታተሉዎት ይጠይቃሉ። ጣቢያዎች ጥያቄውን ለማክበር ወይም ላለማክበር የግል ምርጫቸውን ይጠቀማሉ። ስለ «Do Not Track» የበለጠ ይወቁ
    • የሦስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለመጠቀም ለየትኛዎቹን ጣቢያዎች እንደሚፈቅዱ ይምረጡ፦እንዲሁም የትኛዎቹን ጣቢያዎች የሦስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለመጠቀም እንደሚፈቅዱ በ«የሦስተኛ ወገን ኩኪዎችን ለመጠቀም የተፈቀደላቸው ጣቢያዎች» በሚለው ስር ማረጋገጥ ይችላሉ። እንዴት የሦስተኛ ወገን ኩኪዎችን መፍቀድ እንደሚችሉ ይወቁ

ተዛማጅ ግብዓቶች

ተጨማሪ እገዛ ያስፈልግሃል?

እነዚህን ቀጣይ እርምጃዎች ይሞክሩ፦

6870069744345942616
true
የእገዛ ማዕከልን ይፈልጉ
true
true
true
true
true
237
ፍለጋ
ፍለጋ አጽዳ
ፍለጋን ዝጋ
ዋናው ምናሌ
false
false
false